TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንድሙ #የተገደለበት ሁሉ የገዳዮቹን ወንድሞች #ልግደል ካለ ሁላችንም ያለ ወንድም እንቀራለን!!
.
.
.

"በክልላችን በነበረው ብልሹ አስተዳደር ብዙ ችግሮች ተፈጥረዋል። ሁላችንም ተበድለናል። የተፈጸሙትን በደሎችና ችግሮች እንቁጠራቸው ብንል አንችልም። ይቅርታ አድርጉልኝና ማን ማንን እንደሚያጽናና አላውቅም። በደሎቹን ማስታወስና ቁስላችንን መቆስቆስ አያስፈልግም። አልሃምዱሊላህ አሁን ሁሉም አልፏል። ወገኖቼ እምባ ይብቃን፥ ማቃችንን እንጣል፥ በአዲስ መንፈስ እንነሳ። የጥላቻን እና ብቀላን ጦስ እስኪበቃን አይተናል። ወንድሙ የተገደለበት ሁሉ የገዳዮቹን ወንድሞች ልግደል ካለ ሁላችንም ያለ ወንድም እንቀራለን፥ ሁላችንም እንጠፋለን። ጥላቻ #በፍቅር እንጂ በበቀል አይሸነፍም። ስለዚህ #ካለፈው ተምረን #በፍቅር እና #በይቅርታ፥ በአዲስ ሞራል እጅ ለእጅ ተያይዘን ለጋራ ሰላም፥ ዲሞክራሲና ልማት እንረባረብ"

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር (#ሙስጠፈ_መሀመድ_ኡመር)

©Yoseph Legess
@tsegabwolde @tikvahethiopia