TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንኳን_አደረሳችሁ

"የአረፋ በዓልን አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ማክበር ይገባል" - ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር ኢድሪስ 1 ሺህ 440ኛውን የአረፋ በዓል አስመልክተው ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዚሁ መልዕክታቸው በዓሉን የተቸገሩትን በማሰብና በማካፈል ማሳለፍ እንሚገባ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አንገብጋቢው ጉዳይ አንድነትና ሠላምን ማስጠበቅ መሆኑን የጠቀሱት ሃጅ ኡመር “በሀገርም ሆነ በውጭ ያለን ሁሉ አንድነታችንንና ሠላማችንን ልንጠብቅ ይገባል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እንኳን_አደረሳችሁ

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እሁድ የሚከበረውን 1440ኛው የኢድ አል አድሃ (#አረፋ) በዓልን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሰይድ መሐመድ ኡመር 1440ኛው ሂጂራ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ሲከበር የተቸገሩትን በመርዳት እና ለሀገር ሰላም ፀሎት በማድረግ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ሙስሊሙ ማኅብረተሰብ አቅም የሌላቸው እና የተቸገሩ የኃይማኖቱ ተከታዮች በአሉን ተደስተው እንዲያከብሩ የማድረግ ኃማኖታዊና ማኅበራዊ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ነው ፕሬዝዳንቱ ያስገነዘቡት፡፡

የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች በሀገሪቱም ሆነ በአማራ ክልል በተከሰተው አለመረጋጋት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና ወደ ቀድሞው ህይወታቸው እንዲመለሱ በመርዳት በዓሉን እንዲያከብሩም ሺህ ሰኢድ መሃመድ ኡመር ጠይቀዋል፡፡

ምእመኑ በዓሉን ከሌሎች የኃይማኖት ተከታይ ወገኖቻቸው ጋር በማክበር ለዘመናት የዘለቀውን የአብሮነትና የመተሳሰብ እሴት ማጎልበት ላይ እንዲያተኩሩም ነው ያሳሰቡት፡፡ በዓሉ በባሕር ዳር አለም አቀፍ ስታዬም የሚከበር ይሆናል፡፡ የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባን ጨምሮ ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችም በሥፍራው ተገኝተው መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እንኳን_አደረሳችሁ !

ዐቢይ ፆም በዛሬው ዕለት ጀምሯል።

ፆሙን የጀመራችሁ ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ወርሃ ፆሙ በችግር ፣ በእጦት ፣ በአስከፊ ድርቅ ከምንም በላይ በሰላም እና ፀጥታ ችግር እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖችን የምናስብበት ፣ አቅም በፈቀደ ሁሉ ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ የምናደርግበት እንዲሆን እንማፀናለን።

በተጨማሪም ስለኢትዮጵያና ስለዓለም ደህንነት እና ሰላም ፈጣሪን አጥብቀን የምንማፅንበት ሊሆን ይገባል እንላለን።

መልካም የዐቢይ ፆም ይሁንላችሁ።

(Tikvah - Family)

@tikvahethiopia