TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update በተቃዉሞ ምክንያት ለሳምንት ያህል #ተዘግቶ የነበረዉ የአማራ ክልልንና የትግራይ ክልልን የሚያገናኘዉ አውራ ጎዳና ለአገልግሎት ዳግም ክፍት መሆኑን የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከድሬዳዋ ደወሌ ጅቡቲ መንገድ በሱማሊ ክልል ሲቲ ዞን በተቀሰቀሰ #ተቃውሞ ዛሬ #ተዘግቶ ውሏል። ተቃውሞ የተቀሰቀሰው በአፋር ክልል በሚኖሩ የሱማሊ ዒሳ ጎሳ አባላት ላይ ጥቃት ደርሷል የሚል መረጃ መሰራጨቱን ተከትሎ ነው።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንገዱ እስካሁን ዝግ ነው!

"መንገዱ እስካሁን ዝግ ነው የህዝብ ባስ እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች በችግር ላይ ናቸው ምክንያቱም በቂ ምግብ እና ውሃ የለም በተለይ ህጻናት የያዙ እናቶች ያሳዝናሉ! ለዛሬ እዛው ማደራቸው ነው please ቢያንስ ነገ ጠዋት መንገዱ የሚከፈትበትን መንገድ መንግስት ቢፈልግ እላለሁ።"

በተጨማሪ...

📞ከደቂቃዎች በፊት በስልክ ያነጋገርኩት #በስፍራው የሚገኝ አንድ ሰው ዛሬ በአካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ችግር ውድ የሆነው የሰው ልጅ ህይወት ማለፉንና የተጎዱ መኖራቸውን ነግሮኝ ከ5 ሰዓት ጀምሮ መንገዱ #ተዘግቶ መቆማቸውን ገልፆልኛል። መንገድ በመዘጋቱ የቆመው የመኪና ቁጥርም እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ አስረድቶኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbebaUniversity

ለዕድሳት #ተዘግቶ የነበረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ መኮንን አዳራሽ ሙዚየም ዕድሳቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ከዛሬ ጀምሮ ለጉብኝት ከፍት እንደሆነ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም አስታወቀ። ለሙዚየሙ ዕድሳት 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን የዕድሳት ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያና በጃፓን መንግስት መካከል በተደረገ ስምምነት የተካሄደ መሆኑ ታውቋል።

Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia