TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#CRRSA

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ፤ በጥር ወር አገልግሎትን በገንዘብ በመሸጥ እንዲሁም ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ላይ የተሰማሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

ኤጀንሲው ፥ በሃሰተኛ ሰነድ ዝግጅት  ላይ የተሰማራ ህገ-ወጥ ደላላ እና አንድ የሌላ ተቋም ሰራተኛ  እንዲሁም ላልተገባ ግለሰብ በገንዘብ አገልግሎት የሰጠ የተቋሙ ሰራተኛ እና ተገልጋዮችን በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን ነው ገለጸው።

ኤጀንሲው በሰጠን ማብራሪያ ፤ የአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የስራ ዕድል ፈጠራ ጽ/ቤት #ሰራተኛ የሆነ ተጠርጣሪ 30 ሺህ ብር በመቀበል በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ ከጽ/ቤቱ ያልወጣ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ እና  የጋብቻ ሰርትፍኬት ማዘጋጀቱ ተደርሶበር በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ፤ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ ከጽ/ቤቱ ያልወጣ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የልደት ሰርተፍኬት እና የመሸኛ ማስረጃ /Clearance / በ10 ሺ ብር  ያዘጋጀውን ግለሰብ ከየካ ከፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር በየካ ወረዳ 10  አካባቢ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር አውሎታል።

ኤጀንሲው፤ ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በደረሰው ጥቆማ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 4 እና አዲስ ከተማ ወረዳ 9 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት ምዝገባ ጽ/ቤት ሰራተኛ የሆኑ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ግለሰቦች የነዋሪነት መታወቂያ እና የልደት ማስረጃ በመስጠታቸው በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በዚህ ጥር ወር በኤጀንሲው ስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት በተመራው ክትትል እና ኦፕሬሽን ፦
- ሰባት በተቋሙ ስም የተሰሩ ሃሰተኛ ማስረጃ የያዙ ግለሰቦች፣
- ሶስት የተቋሙ ሰራተኞች ፣
- አንድ የሌላ ተቋም ሰራተኛ እና አንድ በሃሰተኛ ሰነድ ዝግጅት ላይ የተሰማሩ በድምሩ 12 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረግ መቻሉን አሳውቋል።

ኤጀንሲው ፤ " በመዋቅሬ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትል በማድረግ ከሌብነት የፀዳ ተቋም ለመገንባት ጥረት እያደረኩ ነው " ያለ ሲሆን ህብረተሰቡ  በተቋሙ ስም ከሚያጭበረብሩ ህገ-ወጥ ግለሰቦች እራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።

" በተቋሙ ጥቂት ሰራተኞች የሚፈፀሙ ህገ-ወጥ ተግባራት በቅንነት እና ታማኝነት የሚያገለግሉ ሰራተኞችንም አይወክልም " ብሎ " በህዝብ የሚታመን አገልጋይ ተቋም ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ነዋሪው አጋዥ እንዲሆን " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia