TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ቀውስ በአንድ ቀን 96 ሰዎች መገደላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል #ዘይኑ_ጀማል ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ሰዎቹ የተገደሉት ቀውሱ በተነሳበት የመጀመርያው ቀን #ሐምሌ 27፣ 2010 ዓ. ም. ሲሆን፤ በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች #ግድያው መፈጸሙን ተናግረዋል።

ሰዎቹ የተገደሉት #በአሰቃቂ ሁኔታ መሆኑን ተናግረው፤ ሀይማኖትና ብሔርን ለይቶ የተሰነዘረ ጥቃት እንደሆነ አክለዋል።

"ከዘር #ጭፍጨፋ አይተናነስም" ብለዋል። መነሻው የክልሉ አመራሮች አቅደው፤ ተግባሩን የሚፈጽሙ ሰዎች አሰልጥነውና አሰማርተው መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

እስከ አሁን የክልሉን የቀድሞ ፕሬዘዳንት አቶ አብዲ ሞሀመድ ኡመርን ጨምሮ ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

'ሄጎ' በመባል የሚታወቀው ቡድን በግድያው እጁ ስለመኖሩ ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ፤ "በዋናነት በግጭቱ ተሳትፈዋል የሚባሉት #ሄጎ በሚባለው ቡድን አባላት ናቸው። ሄጎ የሚባለውን #የፈጠሩ፣ እቅዱን ያቀነባበሩ የክልሉ የፖለቲካ #አመራሮች፣ የክልሉ የካቢኔ አባላትና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ #ባለስልጣኖችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየሰራን ነው" ብለዋል።

ልዩ ፖሊስ በግድያው ተሳትፎ ስለመሆኑ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ማን በምን ደረጃ ተሳተፈ የሚለው ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል" ሲሉ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

በጅግጅጋ የሚኖሩ የተለያዩ አካባቢዎች ተወላጆች ስጋት እንዳላቸው የሚናገሩት ጄኔራል ዘይኑ፤ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት የክልልሉን ዋና ዋና ከተማዎች መቆጣጠሩ አንጻራዊ ሰላም ማስፈኑን ገልጸዋል።

በአሁን ወቅት አዲሱ የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፋ ኡመር በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ህብረተሰቡን እየጎበኙ መሆኑን ተናግረዋል።

የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ አካባቢው መመለስ ቀጣዩ ስራ መሆኑን ተናግረው፤ በዚህ ረገድ የአካባቢው ማህበረሰብ እየተባበራቸው እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#April6RWANDA "...እ.ኤ.አ ሚያዝያ 6/1994 በጊዜው የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት የነበሩትን ጁቬናል ሃብያሪማናንና የቡሩንዲውን አቻቸውን ሲፕሬን ንታርያሚራን የያዘ አውሮፕላን ተመትቶ 2ቱን ፕሬዚዳንቶች ጨምሮ በአውሮፕላኑ ውስጥ የተሳፈሩት ሁሉም ሰዎች አለቁ፡፡ ፕሬዚዳንት ሃብያሪማና የሁቱ ጎሳ ተወላጅ መሆናቸው በወቅቱ ስልጣን ይዘው የነበሩት ሁቱዎች ለረጅም ዓመታት በሩዋንዳ የመንግሥትን ስልጣን…
#ሩዋንዳ

ዛሬ የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ (ጄኖሳይድ) 30ኛ ዓመት መታሰቢያ ነው።

በ1994 እ.አ.አ ሩዋንዳ ውስጥ በቱትሲ ጎሣ ላይ የደረሰው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በሰው ልጆች ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ከደረሱት አሰቃቂ የዘር ጭፍጨፋዎች አንዱ ነው።

በ100 ቀናት ገደማ ውስጥ ብቻ ከ800,000 እስከ 1,000,000 የሚሆኑ ሰዎች እንዳለቁ ይገመታል።

ከተገደሉት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ቱትሲዎች ናቸው፤ ሆኖም በጭፍጨፋው ለመካፈል ፈቃደኛ ያልሆኑ የሁቱ ጎሣ አባላትም የግድያው ሰለባ ሆነዋል።

በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ተደፍረዋል።

የሩዋንዳ ጄኖሳይድ እንዴት ተፈፀመ ?

- በ10 ሚሊዮን የሚቆጠሩ የሩዋንዳ ዜጎች ለዘመናት እራሳቸውን እንደ #አንድ ነው ሲያዩ የኖሩት።

- በ1916 (እ.አ.አ) ቤንጂየም ሩዋንዳን በቅኝ ግዛት ትይዛታለች። በኃላም በቁጥር የሚበዙትን ሁቱዎች በቁጥር ከሚያንሱት ቱትሲዎች የሚለዩበትን አዲስ ሲስተም የመታወቂያ ወረቀት በመስጠት ዘረጋች። (የብሄር መታወቂያ አከፋፈለች)

- ቱትሲዎቹ በቤልጂየምዎቹ ፦
° በትምህርት ፣
° በስራ፣
° በስልጣን ከፍ ያለ ቦታ እንዲሰጣቸው ተደረገ። ሁቱዎቹ ግን ብዙ ቁጥር ኖሯቸው የትምህርት ፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ተነፈጋቸው።

- ቤንጂየሞቹ ቱትሲዎቹ ከብዙሃኑ ሁቱዎቹ የተሻሉ አድርገው እንዲሳሉ አደረጉ።

- በ1959 ሩዋንዳ ነጻነቷን ስታገኝ ሁቱዎች በማመፅ እና የመንግሥትን ስልጣን በመያዝ #ቱትሲዎችን ገደሉ ፣ ከሀገር እንዲሰደዱ አደረጉ። በዚህ ወቅት በመቶ ሺዎች ወደ ጎረቤት ሀገር ተሰደዋል።

- በ1990 በቱትሲ የሚመራው የRwanda Patriotic Front (RPF) ከኡጋንዳ በመሆን በሁቱ በሚመራው መንግሥት ላይ ጥቃት ከፈተ። ይህም የእርስ በእርስ ጦርነት መጀመሪያ ሆነ። በዚህ ወቅት ፈረንሳይ የሩዋንዳን መንግሥት ታስታጥቅ፣ ታሰለጥን ፣ ትደግፍ ነበር። ሩዋንዳም በፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አማካኝነት በፖል ካጋሚ የሚመራውን ኃይል ትደግፍ ነበር።

- በሩዋንዳ መንግሥትና በRPF ኃይል መካከል የነበረው ጦርነት በ1993 የሰላም ስምምነት እንዲቆም ተደረገ። የUN ኃይልም ስምምነቱ እንዲከበር ለማመቻቸት ዘንድ ወታደራዊ ኃይሉን ላከ።

- በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ በሁቱ እና በቱስቲዎች መካከል ያለው ውጥረት እጅግ በጣም እየከፋ ነበር የሄደው። የጥላቻ ፕሮፖጋንዳውን ከፍ ብሎ ነበር። በእርስ በእርስ ጦርነቱ ወቅት የሩዋንዳ መንግሥት RPFን እንደ ጠላት፣ እንደ ሀገር ካጅ፣ ባንዳ፣ እያደረገ ፕሮፖጋንዳ ሲሰራ ነበር።

-  ሚያዚያ 6 ቀን 1994 የሁቱ ጎሳው ፕሬዜዳንት ጁቬናል ሃብያሪማና ተሳፍረውበት የነበረው አውሮፕላን ኪጋሊ በሚገኝ ኤፖርት አካባቢ ተመትቶ ወደቀ። ፕሬዜዳንቱም ህይወታቸው አለፈ። በወቅቱ የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ሳይፕሪን ንታያሚራ አብረዋቸው ነበሩ እሳቸውም ሞቱ።

- ፕሬዚዳንቱን የገደላቸው ማን እንደሆነ በግልጽ ባይታወቅም ሁቱዎቹ የቱትሲ አማፂ ቡድን ነው የፈፀመው ብለው በሚዲያ አስወሩ። ሁቱዎች እየወጡ ቱትሲዎችን እንዲገድሉ በሚዲያ ጥሪ አቀረቡ።

... በቃ #ግድያው ተጀመረ። ከ800 ሺህ እስከ 1,000,000 ቱትሲዎች እና ለዘብተኛ ሁቱዎች አለቁ። ከ100 ቀን በኃላ የRPF ኃይል ወደ ኪጋሊ ሲቃረብ ግድያው አቆመ ሁቱዎቹም መሸሽ ጀመሩ፣ በተለይ ሲገድሉ ሲያስተባብሩ የነበሩት ሀገር ጥለው ወጡ።

ሚዲያዎች ? የውጭ ሀገር ኃይሎች ? ተመድ በዚህ ውስጥ ምን ሚና ነበራቸው ? በቀጣይ  ፅሁፍ እንዳስሳለን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
Rwandan genocide
Apr 7, 1994 – Jul 15, 1994

@tikvahethiopia