TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሱማሊያ ጫት ነጋዴዎች ከኬንያ ጫት ማስገባታቸውን ትተው #የኢትዮጵያን_ጫት ለመግዛት መወሰናቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል፡፡ ኬንያ የሞቃዲሾው መንግሥት በቅርቡ ያወጣው ዐለም ዐቀፍ የነዳጅ ቁፋሮ ጨረታ ሉዓላዊ የባህር ግዛቴን አጠቃሏል በማለቷ ከቅዳሜ ጀምሮ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን አቋርጠዋል፡፡ ሱማሊያ ግን ውንጀላውን ታስተባብላለች፡፡ የሱማሊያዊያኑ ጫት ነጋዴዎች ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ የኢትዮጵያን ጫት የምናስገባው ከሀገራችን ሉዓላዊነት ጎን መቆም ስላለብን ነው ብሏል፡፡ ሱማሊያ በቀን ከኬንያ የምታስገባው 50 ቶን ጫት 100 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ይገመታል፡፡

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 12/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን 82ኛ ዓመት የመታሰቢያ ስነ ስርዓት በዛሬው እለት ተካሂዷል። መታሰቢያ ስነ ስርዓቱ በተለይ 6 ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰማእታት አደባባይ ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ነው የተካሄደው።
.
.
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጣልያኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ ኤሬአ ጋር የነበረውን ስምምነት ቀይሮ ከእንግሊዙ አምብሮ ኩባንያ ጋር የአራት አመት የትጥቅ ልብስ ማቅረብ ስምምነት ተፈራርሟል።
.
.
በአማራ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም የክልሉ መንግስት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ #ጥረት_ኮርፖሬሽን የ10 ሚሊዮን ብር የመጀመሪያ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
.
.
ግሎባል አልያንስ ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር #ለተፈናቀሉ 46ሺ ለሚሆኑ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይንም በኢትዮጵያ 6 መቶ ሺ ብር #መለገሱን አስታውቋል።
.
.
በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከማንም ጋር #ለድርድር እንደማይቀመጥ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) አስታውቋል። ፓርቲው በትናነትናው እለት ባወጣው መግለጫው፥ ኦዲፒ በአጀንዳነት ይዞ ከሚታገልባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው የፌደራል ስርዓቱ ነው ብሏል።
.
.
በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን #ያአበሎ_ወረዳ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
.
.
“ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር” የሽኝት መርሃ ግብር ከነገ በስቲያ በይፋ እንደሚካሄድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።
.
.
ከነገ በስቲያ/ሀሙስ የካቲት 14/2011 ዓ.ም. የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በሀዋሳ ከተማ የጠራው #ሰላማዊ_ሰልፍ በመንግስት ፍቃድ አግኝቷል።
.
.
ጥቅምት 4/2011 ዓ/ም ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (#ቴዲ_አፍሮ) በሚሊኒየም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ዝግጅት ደረጃውን በጠበቀ የድምፅ እና የምስል ጥራት #በዲቪዲ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 16 ለገበያ ይቀርባል ተብሏል።
.
.
#የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ አባላት #ከሀዋሳ_ከተማ ነዋሪዎች ጋር #ተወያይተዋል
.
.
ድሬዳዋ ውስጥ በዓመት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ፋብሪካ #ሊገነባ መሆኑን የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ተገልጿል።
.
.
#ቂሊንጦ_ማረሚያ_ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል በሚል የተጠረጠሩ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሁለተኛ ዙር የ100 ቀን ዕቅድ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ አስታውቀዋል።
.
.
የሱማሊያ ጫት ነጋዴዎች ከኬንያ ጫት ማስገባታቸውን ትተው #የኢትዮጵያን_ጫት ለመግዛት መወሰናቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል፡፡
.
.
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባደሳደር ዶ/ር #አላስቴይር_ዲቪድ ማክፌይል በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው #አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች #ተመለሱ። በዞኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውም ተገልጿል።
.
.
የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል ያላቸውን መኖሪያቤቶች ማፍረስ ጀምሯል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦነግ አባላት ህዝቡን #እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ በዞኑ፣ መነ ሲቡ ወረዳ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።
.
.
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሄራዊ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጋራ የተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ካርቱም

በትናንትናው ዕለት ሱዳናውያን ወጣቶች በካርቱም ጎዳናዎች ላይ #የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለቡ ታይተዋል፡፡ ወጣቶቹ ይህን ያደረጉት በሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች መካከል በተደረሰው ወሳኝ ስምምነት ሂደት ኢትዮጵያ ለተጫወተችው ቁልፍ ሚና አድናቆታቸውን ለመግለፅ ነው፡፡ ወጣቶቹ በሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ስልጣን ለመጋራት በተፈረመው ገንቢ ስምምነት የተሰማቸውን ታላቅ ደስታም ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሰሞኑን ተከታትለው የወጡት የተኩስ አቁም ጥሪዎች !

በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከጀመረ ሰዓት አንስቶ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ተኩስ እንዲቆም ጥሪ ሲያቀርቡ እንደነበር አይዘነጋም።

ከሰሞኑን ደግሞ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት በተከታታይ የተኩስ አቁም እና የድርድር ጥሪዎችን ሲያቀርቡ ተስተውሏል።

1ኛ. #ሩሲያ፦ በድጋሚ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ጠይቃለች።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ሩሲያ የኢትዮጵያን ጉዳይ እየተከታተለች እንደሆነ ገልፃለች ፤ ሰሞኑን በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተሞች የተካሄዱት ጦርነቶች የሲቪል ዜጎችን ህይወት ጎድቷል ብለዋል።

ሩሲያ #የኢትዮጵያን_ግዛት_አንድነት መከበር ለድርድር የማይቀርብ እና ግጭቱን መፈቻ መንገድ ሊሆን እንደማይችል ታምናለች ብለዋል።

2ኛ. #ኬንያ ፦ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም ኢትዮጵያውያን እንዲወያዩ አሳስበዋል።

ኬንያታ የኢትዮጵያ ተፋላሚ ወገኖች ድርድር ይጀምሩ ሲሉ ጠይቀዋል።

ህወሓት እና ኦነግ ሸኔ የፌደራል መንግስቱን ለመውጋት ቅንጅት መፍጠራቸው ጦርነቱ ሌላ መልክ እንዲኖረው እና እንዲራዘም እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፌደራል መንግስቱ እና በህወሃት መካከል እስካሁን ትርጉም ያለው ድርድር አለመጀመሩ ጦርነቱ ከአንድ ዓመት በላይ እንዲቀጥል አድርጎታል ብለዋል ኡሁሩ።

ኬንያን ጨምሮ አፍሪካ እና ዓለም ሰላማዊ ኢትዮጵያን ማየት ይፈልጋል ያሉም ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተመካክሮ ለአገሩ ሰላም መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቀዋል።

3ኛ. #ኢጋድ ፦ የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጦርነት እንዲቆምና አስቸኳይ ተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶ/ር ወርቅነህ ፥ እየከረረ መጥቷል ያሉትን የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በከፍተኛ ስጋት እየተከታተሉ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ኢጋድ ጦርነቱ በተጀመረበት ወቅት ባለፈው ዓመት ሁኔታውን በማስመልከት ጥሪ ማቅረቡን ያስተወሱት ዶ/ር ወርቅነህ ጦርነቱ እንዲቆምና በአስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች ከግጭት ተቆጥበው በመካከላቸው ያለውን መካረር እንዲያረግቡ እና ልዩነቶቻቸውን ለሃገሪቱ ብሎም ለቀጠናው በሚበጅ መልኩ በውይይት እና እርቅ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል።

4ኛ. #ዩጋንዳ ፦ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አባል ሐገራት መሪዎች ጦርነቱ ሥለሚቆምበት ሁኔታ ለመነጋገር እንዲሰበሰቡ ጠይቀዋል።

5ኛ. #አሜሪካ ፦ ዛሬም (ጥቅምት 26) አሜሪካ በድጋሚ በኢትዮጵያ ተኩስ ይቆም ዘንድ ጥሪ አቅርባለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ያለው ግጭት ማብቃት አለበት ፤ አሁኑኑ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሰላም ድርድር መጀመር አለበት ብለል፤ ተኩስ እንዲቆምም ጠይቀዋል።

6ኛ. #AU ፦ የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በኢትዮጵያ ያለው ወታደራዊ ግጭት መባባስ እንዳሳሰባቸውና በቅርበትም እየተከታተሉት እንደሆነ ገልፀዋል።

ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት ሰሞን ያወጡትን መግለጫ በማስታወስ የጦርነቱ ተሳታፊ ሁሉም ወገኖች የኢትዮጵያን ግዛት አንድነት፣ ብሄራዊ ሉዓላዊነት እንዲጠብቁ በድጋሚ አሳስበዋል።

በአገር ጉዳይ ላይ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ ሁሉም ወገኖች ወደ ውይይት እንዲገቡም አሳስበዋል።

ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የዜጎች ህይወትና ንብረት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር፣ እንዲሁም የመንግስት መሠረተ ልማት እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል።

የጦርነቱ ተሳታፊ ወገኖች ደጋፊዎቻቸው በማንኛውም ማህበረሰብ ላይ የበቀል እርምጃ እንዳይወስዱ እንዲሁም ከጥላቻ ትርክቶች፣ ክፍፍልንና ግጭቶችን ከሚያበረታቱ ሁኔታዎች እንዲቆጠቡ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

በሌላ መረጃ ፦

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውንና ለድርድር የሚሆን ማንኛውንም ድጋፍ እንደሚሰጡ እንደገለጹላቸው አሳውቀዋል።

ምንጭ፦ UN ፣ AU ፣ ኢጋድ ፣ አል አይን ኒውስ ፣ Daily Nation ፣ António Guterres (Twitter) ፣ BBC ፣ Antony Blinken (Twitter)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጎረቤት ሱዳኖች የጦርነት ጉሰማ ላይ ናቸው ! የሱዳን ጦር አዛዥ እና የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር መጎብኛታቸው ተነግሯል። ቡርሀን ትንሹ ፋሻጋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙት አል ዑስራ እና ዋድ ኮሊ አካባቢዎች የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር ነው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ/ም የጎበኙት፡፡…
" የሱዳን ጦር የሚነዛው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው " - የኢትዮጵያ 🇪🇹 ሀገር መከላከያ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የምርኮኞችን አያያዝ ባልጠበቀ መንገድ ወታደሮቼን ገድሏል በሚል የሱዳን ጦር የሚነዛው መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በቦታው እንዳልነበርና #የኢትዮጵያን_ግዛት_ዘልቆ የገባው የሱዳን ኃይል ከአካባቢው ሚሊሻዎች ጋር መጋጨቱ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ ሕወሓት ሰሜን ዕዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት በፈፀመበት ወቅት የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ላይ ወረራ መፈጸሙን አስታውሶ፤ ጦሩ በተለያየ ጊዜ ውስጣዊ ችግሮች ባጋጠሙ ቁጥር በኢትዮጵያ ላይ ትንኮሳዎችን ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

ሰሞኑ ደግሞ የሱዳን ኃይል ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ በመግባት በአካባቢው በነበሩ የኢትዮጵያ ሚሊሻዎች ላይ ጥቃት ማድረሱንና ከሁለቱም ወገን ጉዳት መድረሱን ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።

ነገር ግን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በስፍራው ባልነበረበት ሁኔታ " ምርኮኞችን ገደለ " በሚል የሱዳን ጦር ክስ ማቅረቡ ተቀባይነት የሌለውና መሰረተ ቢስ መሆኑ አስገንዝቧል።

የደረሰውን ጥቃት በተመለከተ ማጣራት የሚፈልግ አካል ካለ ከሁለቱ ሀገራት መከላከያ ሠራዊት ተወካዮች የተውጣጣ ኮሚቴ ተዋቅሮ እንዲጣራ ለመተባበር የኢትዮጵያ ሠራዊት ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አረጋግጧል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከ20 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው። በዛሬው ዕለት በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ። ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ፦ - ጅማ ዩኒቨርሲቲ - ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ ካምፓስ) - ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ) - አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ (ዋናው ግቢ) - ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ - ጂንካ ዩኒቨርሲቲ - ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ…
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመቄዶንያ መስራች አቶ ቢንያም በለጠ እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ ፤ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ( #ጂጂ ) የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክተዋል።

አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ ላከናወኗቸው በጎ ስራዎች የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል። በሰሩት ስራ በሰው ልጆች ደህንነት ላይ ለሀገር የማይተካ አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው አርቲስት ደበበ እሸቱ በኪነጥበብ ዘርፍ ላበረከቱት ውለታ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል።

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

ዕውቅናው ሁለገቧ አርቲስት #የኢትዮጵያን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነ ጥበብ #የአዊን_ሕዝብ_ቋንቋ እና #ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ነው የክብር ዶክትሬት የተበረከተላት።

የክብር ዶክትሬቱን የእጅጋየሁ ሽባባው ወላጅ እናት ተቀብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Puntland #Somalia ፑንትላንድ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ይፋ አድርጋለች። ከፊል ራስ ገዝ የሆነችው #ፑንትላንድ በሞቃዲሾ ለሚገኘው ለሶማሊያ የፌደራል መንግሥት ከዚህ ቀደም ሰጥታው የነበረውም ዕውቅና አንስታለች። የፑንትላንድ መንግሥት ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ ፑንትላንድ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ተቋማት ላይ የነበራትን መተማመን በማጣቷ ትሰጥ የነበረውን ዕውቅና…
#Somalia

° " ስለዚህ ጉዳይ መረጃው የለኝም " - አቶ ነብዩ ተድላ

ሶማሊያ ፥ በሶማሊያ #የኢትዮጵያን_አምባሳደር የሆኑትን ሙክታር ሞሃመድ ዋሬን ወደ ሀገራቸው #እንዲመለሱ ማድረጓን ሁለት ከፍተኛ የሶማሊያ ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ #ሮይተርስ ዘግቧል።

ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ያደረገችበት ምክንያት ከሶማሊላንድ ጋር የገባቸው የወደብ መግባቢያ ስምምነት እንደሆነ ተነግሯል።

ከዚህ ባለፈ ሶማሊያ በፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ያሉ የኢትዮጵያን ቆንስላ ጽህፈት ቤቶችን ዘግቻለሁ ብላለች።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በጉዳዩ ዙሪያ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው እንደነገሩት ሮይተርስ አስነብቧል።

የፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ነገር ?

ፑንትላንድ ከሕገ-መንግስት ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ከቀናት በፊት ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።

ከአሁን በኃላም ማንኛውም ፍላጎቷን ለማስጠበቅ ከማዕከላዊ የሶማሊያ መንግሥት እውቅና ውጪ በራሷ የውጭ ግንኙነትም እንደምታደርግ ገልጻለች።

ሶማሌላንድም ምንም እንኳን እስካሁን ሶማሊያ ' የራሴ ግዛት ነሽ ' ብትላትም ራሷን እንደ ነጻ ሀገር መቁጠር ከጀመረች አመታት አልፈዋል። የውጭ ግኝኑነቶችንም ታደርጋለች።

የሰሞኑን የፑንትላንድ ነገር ለሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት " በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ " ሆኖበታል።

ከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድ ሰሞኑን ፥ " ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ተቆራጠናል ፤ እውቅናም አልሰጥም " ካለች በኃላ ከፍተኛ ባለስልጣናቷ ኢትዮጵያ / አዲስ አበባ ለውይይት መግባታቸው መነጋገሪያ ሆኗል።

እዚህ አዲስ አበባ የመጣው በገንዘብ ሚኒስትሯ ሞሃመድ ፋራህ ሞሀመድ የተመራ ልዑክ ነው።

ልዑኩ ከኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ጋር መክሯል።

በዚህም ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ጋር ያላትን ዘርፍ ብዙ ትብብሮች ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗ ተገልጿል።

የፑንትላንድ ልዑክም ፥ ኢትዮጵያ በፑንትላንድ በጸጥታና በትምህርት ዘርፍ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን ገልጾ የፑንትላንድ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት የማሳደግ ፍላጎት እንዳለው አረጋግጧል።

በዚህ ወቅት የፑንትላንድ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ መምጣታቸው ግጥምጥሞች ወይስ ከወቅታዊ ሁኔታው ጋር የተያያዘ ነው ?

" ጉብኝቱ የቆየ ቀጠሮ ነው " - አቶ ነብዩ ተድላ

ዛሬ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፑንትላንድ በገንዘብ ሚንስትሯ መሀመድ ፋራህ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ አ/አ ጉብኝት ማድረጉን ገልጸዋል።

ይህ ጉብኝት ከሰሞነኛው የፑንትላንድ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር #የማይገናኝ እንደሆነ እና የጉብኝት ፕሮግራሙም የቆየ ቀጠሮ መሆኑን አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ኢትዮጵያ ጎረቤታችን ናት፤ ከእነሱ ጋር ቢዝነስ መስራት እንፈልጋለን " - ሰኢድ ሀሰን አቡዱለሂ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች / #UAE / ንብረት የሆነው ' ዲፒ ወርልድ ኩባንያ ' የሚያስተዳድረው የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ የሶማሌላንድ ባለስልጣናት ማቀዳቸው ተሰምቷል። ለዚህ የወደብ አጠቃቀምና የጉምሩክ ሥርዓቶችን የተመለከተ ስምምነት በኢትዮጵያና ሶማሌላንድ…
" ወደቡ ዝግጁ ነው፤ መንገዱም ከሞላ ጎደል ዝግጁ ነው " - ሰዓድ አሊ ሽሬ

ሶማሌላንድ የበርበራ ወደብ #የኢትዮጵያን 30% ጭነት እንዲያስተናግድ ትፈልጋለች።

ለዚህ ደግሞ አስፈላጊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልጸለች።

አሁን ላይ ስምምነት እንዲፈረም እየተሰራ ነው ተብሏል።

የሶማሌላንድ የፋይናንስ ሚኒስትር ሰዓድ አሊ ሽሬ ምን አሉ ?

" አካላዊ መሰረተ ልማትን በተመለከተ ወደቡን ገንበተናል።

አንድ ኪሎሜትር የሚሰፋ የመርከብ ማቆሚያ፤

ኮንቴነሮችን መጫንና ማውረድ የሚችሉ ክሬኖች ያሉት ዓለም አቀፍ ወደብ አለ፤

ከበርበራ ወደብ ድንበር ላይ እስከምትገኘው #ውጫሌ ያለውን መንገድ ገንብተናል፤

ስለዚህ ወደቡ ዝግጁ ነው። መንገዱም ከሞላ ጎደል ዝግጁ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በበርበራ ነጻ የኢኮኖሚ ዞኖች አሉን።

የነዳጅ ማጠራቀሚያ ጋኖች ከነዳጅ ጫኝ መርከቦች ማራገፊያ አዘጋጅተናል። አካላዊ ክፍል ከሞላ ጎደል አልቋል።

ለምሳሌ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል የወደብ አጠቃቀም ስምምነት (Transit Agreement) ሊኖረን ይገባል። የጉምሩክ ስርዓቶቻችን ማገናኘት ወይም ማስተሳሰር ይኖርብናል ይህ አሁንም በስራ ላይ ነው። የመጓጓዣ ስምምነትም ማባጀት አለብን ይሄም ሂደት ላይ ነው።

ከስርዓት አኳያ በሂደት ላይ የሚገኙ የተወሰኑ ጉዳዮች አሉ " ብለዋል።

እንደ ሶማሌላንድ የወደቦች አስተዳደር ዳይሬክተር ሰኢድ ሀሰን አብዱላሂ ማብራሪያ ደግሞ ፥
ህጋዊው ጉዳይ በመንግስታት መካከል የሚፈርም እንደሆነ
ስምምነቱ እየተጠናቀቀ ስለመሆኑ
በአንድ እና ሁለት ቀሪ ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን
በመጪው 60 ቀናት ስምምነቱ ሊጠናቀቅ እንደሚችልን ከ60 ቀናት በኃላ እንደሚፈረምና ኮሪደሩ ጥቅም መስጠት ይጀምራል።

በተጨማሪ ፦
° የUAE ዲፒ ወርልድ እና ሶማሌላንድ ከበርበራ ወደብ 15 ኪ/ሜ ርቀት ነጻ የኢኮኖሚ ቀጣራ ማበጀታቸውን
° ነጻው የኢኮኖሚ ቀጠና ከወደቡ ወደ ኢትዮጵያ በሚያመራው መንገድ ላይ እንደሚገኝ
° ነጻው የኢኮኖሚ ዞን 300 ሺህ ካሬ ጫማ የሚሰፋ ከማብሰያ ዘይት ማሸጊያ ፋብሪካ ጭምር አለው።

ከ6 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ከሶማሌላድ እና ዲፒ ወርልድ ጋር በተፈራረመችው ስምምነት በበርበራ ወደብ ልማት 19% ድርሻ ነበራት ግን አልዘለቀችበትም። ግን አሁን ኢትዮጵያ ወደቡ ላይ ድርሻ እንዲኖራት ትፈልጋለች።

የበርበራ ወደብ ያለበት ቀጠና ለዓለም አቀፍ የመርከብ እንቅስቃሴ ወሳኝ በመሆኑ ሶማሌላንድ እና ዲፒ ወርልድ አሁንም ማስፋታ ይፈልጋሉ።

ግዙፍ የኮንቴነር ተርሚናል ለመገንባት ሙከራ እየተደረገ መሆኑ፣ ተጨማሪ 600 ሜትር የሚሰፋ የመርከብ ማቆሚያ ፣ 7 ግዙፍ የእቃ መጫኛና ማውረጃ ለመጨመር እቅድ እንዳለ ታውቋል።

ይህን ተከትሎ የበርበራ ወደብ መርከብ መቆሚያ 1650 ሜርት እንደሚሆን 2 ሚሊዮን ኮንቴነርም ማስተናገድ እንደሚችል ለኢትዮጵያም ትልቅ አማራጭ መሆኑ በሶማሌላንድ ባለስልጣናት ተገልጿል።

Credit - DW (Eshete Bekele)

@tikvahethiopia