TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቢሾፍቱ ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሣ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን አስጀምረዋል፡፡ በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም በርካታ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎችም ይህን መርሃ ግብር በማስኬድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሁለት መቶ ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር የመትከል ፕሮግራም በመላው ሀገሪቱ እየተካሄደ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ SELAMAWIT KASSAHUN #በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ/የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና 616 ያስመዘገበች ጀግኒት! #ኢትዮጵያዊት

#616 #ቢሾፍቱ

🗓የሌሎች #ጀግኒቶች ውጤት ይቀጥላል🔄
#ቢሾፍቱ

"በትላንትናው ዕለት የአምባ ፋርማሲዩቲካልና አኳርየስ አቪየሽን በመተባበር ለ2ኛ ጊዜ በቢሾፍቱ ሀይቅ ዳርቻ ከአካባቢው ሕብረተሰብ ጋር ዝናቡ ሳያመልጠን ችግኞች ስንተክል፤ የዛሬ ወር ገደማ የተከልናቸውንም ስንንከባከብ ዉለናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቢሾፍቱ የሚገኙ ቤተሰቦቻችን ደመራ እንዳልተደመረ ገልፀዋል። ለምን? የሚለውን በቦታው የነበሩ የቤተሰባችንን አባላት ያዩትን ተናግረዋል ይቀርባል። የሚመለከታቸውን አካላት ለማናገርም ጥረት እናደርጋለን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቢሾፍቱ የአይን እማኝ...

"ከኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን መንገድ ላይ ስንደርስ ያልተፈቀደ አርማ ያለበትን ልብስ ለብሳችኃል/ይዛችኃል/ በሚል አታልፉም አሉን/የፀጥታ አካላት/። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የለበሱም ነበሩ እሱን እንዲህ ሆነን ማለፍ እንደማንችል ተነገረን። መዘምራንም ጭምር። ይሄን አርማ ይዛችሁ እና ለብሳችሁ ማለፍ አትችሉም አሉን። እዛው የነበርነው ሰዎች እንደዛ ከሆነ እዛው ኪዳነ ምህረት እናበራለን ብለን ተመለስን። ወደኪዳነ ምህረት ስንመለስ ወደአዳባባይ የሄዱት ሰዎች አንድ ደብር ጎሎ #አናበራም ብለው ሁሉም ተሰብስቦ ወደ ኪዳነ ምህረት እየተመለሰ ነበር #አደባባይ ያለውን ሳያበሩ ቀርተው። ግማሹ ኪዳነ ምህረት ከሄደ በኃላ እላይ ያለውን ወደታች እንዳይወርድ ታች ያለውን ወደ ላይ እንዳይወጣ ከለከሉ። ሰዎች ወደቤት አንሄድም አሉ። ሰዎችን አሳምነውም ወደአደባባይ ለመውሰድ እና ደመራው እንዲበራ ለማድረግ ጥረት አድርገው ነበር ግን ሰው አልተስማማ። እየዘመርን ወደቤታች እንመለሳለን ብሎ እኛ ወደቤታችን ሄደናል።"

ቢሾፍቱ ስለተፈጠረው ጉዳይ ምላሽ ለማግኘት ጥረት አድርጌ ነበር አልተሳካም። #BISHOFTU #ቢሾፍቱ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Irreechaa2019 ኢሬቻ ሆራ አርሰዲ! #ቢሾፍቱ

PHOTO: OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቢሾፍቱ -- ኡኬ ደንካካ!!

የአደጋው ምንክንያት ምን እንደሆነና ስለደረሰው ጉዳት ተጨማሪ መረጃዎችን እንዳገኘን እናጋራለን!

PHOTO: kira Dibenedetto/TIKVAH-ETH/
@tsevabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቢሾፍቱ ከተማ/ኡኬ ደንካካ የሚባለው አካባቢ በደረሰው የጦር አውሮፕላን መከስከስ አደጋ የሁለት አብራሪዎች ህይወት እንዳለፈ ለጉዳዩ ቅርብ ነኝ ያሉ የቤተሰባችን አባል ከቢሾፍቱ መረጃ ሰጥተዋል። Via DIN/TIKVAH ETH FAMILY/ VIDEO: ሮብኤል/TIKVAH ETH FAMILY/ ተጨማሪ መረጃዎች ይፋ ሲደረጉ እናቀርባለን! @tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቢሾፍቱ

በልምምድ ላይ የነበረ አንድ የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል። አውሮፕላኑ ዛሬ ጠዋት ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአየር ሃይል ካምፕ በመነሳት በልምምድ ላይ እያለ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ ኡኬ ደንካካ በተሰኘ ቦታ መከስከሱን የምስራቅ ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አበራ ያሚ ለዶቸ ቨለ አረጋግጠዋል።

በአደጋው የሁለት አብራሪዎች ህይወት ማለፉንም አቶ አበራ ገልጸዋል። ከሟቾች መካከል የአንደኛው አስክሬን አውሮፕላኑ ከተከሰከሰበት ከ100 ሜትር በላይ ርቆ መገኘቱንም ተናግረዋል። የአደጋው መንስኤ ገና በመጣራት ላይ መሆኑንም ነው አቶ አበራ የተናገሩት።

«በደረሰን መረጃ መሰረት የተከሰከሰው አውሮፕላን የጦር መለማመጃ አውሮፕላን ነው። ሁለት ሰዎች በልምምድ ላይ እንደነበሩም ነው ያጣራነው። ከሁለቱ ሰዎች የአንደኛው አስክሬን ሲገኝ የሌላኛው ከአውሮፕላኑ ጋር ቃጠሎ ደርሶበታል። አደጋው የደረሰው ከምሳ ሰአት በፊት ሲሆን እስካሁን የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ነው የምናውቀው» ብለዋል።

Via #DW

PHOTO: TIKVAH-ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዶዶላ #ቢሾፍቱ #ሀረር

በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ትናንት እና ዛሬ በነበሩ ግጭቶች በጠቅላላው 6 ሰዎች መገደላቸውን ታውቋል። ዛሬ በነበረ ግጭት 4 ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ተናግረዋል። ትናንት ደግሞ ሁለት ሰዎች ተገድለው ነበር። በአካባቢው ከጠዋት ጀምሮ ሠልፍ እንደነበር የተናገሩት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ከሰዓት በኋላ ግን ይህ ሠልፍ መልኩን መቀየሩን ይናገራሉ። ሁኔታው አስፈሪ ስለነበር ለሕይወታቸው የሰጉ ሰዎች በአካባቢው በምትገኘው ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው አንደሚገኙ ተናግረዋል። በሐረር ከተማ በትናንትናው ዕለት 3 ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ከነዋሪዎች ሰምቻለሁ ብሎ ዘግቧል። በቢሾፍቱ ከተማ ዛሬም በቀጠለው አለመረጋጋት የሰዎች ህይወት ማለፉን የቢሾፍቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ተናገርዋል። ዛሬ ከተማይቱ በተኩስ ስትናጥ እንደዋለች፣ በየቦታው መንገዶች ሲዘጉ እንደነበርና ወታደሮች መንገድ ለማስከፈት ሲንቀሳቀሱ መዋላቸውን ገልፀዋል። አመሻሹን ግን ሁኔታዎች ረገብ ብለዋል።

#BBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ADAMA #BAHIRDAR ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በባሕር ዳር እና በአዳማ ከተሞች ጀምሯል። ይህ የደንበኞች ሙከራ ከድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሐረማያ በመቀጠል የሳፋሪኮምን ኔትወርክ ለመሞከር ባሕር ዳርን እና አዳማን 4ኛ እና 5ኛ የኢትዮጵያ ከተሞች አድርጓቸዋል። የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች…
#Bishoftu #Mojo #Debrebrihan

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በቢሾፍቱ፣ ሞጆ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች መጀመሩን አሳውቋል።

ይህ የደንበኞች ሙከራ የሳፋሪኮምን ኔትወርክ እየሞከሩ ያሉትን ከተሞች ቁጥር #ስምንት የሚያደርሰው ሲሆን ባለፉት ሦስት ሳምንታት ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐረማያ፣ ባሕር ዳር እና አዳማ ላይ ሙከራው መጀመሩ ይታወቃል።

ደንበኞች የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፦

#ቢሾፍቱ 📍

በቢሾፍቱ ሁለት የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች (ከኦዳ ነቤ ሆቴል ጎን እና ከመዘጋጃው ፊትለፊት)፤

#ሞጆ📍

በሞጆ አንድ መናኸሪያ አካባቢ የሚገኝ የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈበት መደብር፤

#ደብረብርሃን 📍

ከዘርዕ ያዕቆብ አደባባይ ወረድ ብሎ ባለው ኖክ ማደያ አካባቢ የሚገኝ የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈበት መደብር ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት መሆኑን ገልጿል።

በቢሾፍቱ፣ በሞጆ እና በደብረ ብርሃን ከተሞች አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳውቆናል።

#SafaricomEthiopia

@tikvahethiopia
#ቢሾፍቱ

ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የመከላከያ ሪፈራል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዛሬ ተመርቆ ወደ ስራ ገብቷል።

ሆስፒታሉ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በተገኙበት ነው የተመረቀው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆስፒታሉ ፦
- እጅግ ዘመናዊ የሆነ የሞሎኪዩላር ላብራቶሪ፣
- የአጥንት ምርመራ ማዕከል፣
- ባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ ክፍል
- እንደ የኩላሊት እጥበት፣ የነርቭ፣ የሳምባ እና መተንፈሻ አካላት የህክምና አገልግሎቶችን የሚሰጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

" በሀገራችን ውስጥ ካሉ ግምባር ቀደም ዘመናዊ ሆስፒታሎች አንዱ ነው " ብለውታል።

ፊ/ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በበኩላቸው " ሆስፒታሉ ለሰራዊቱ ብቻ ሳይሆን ለህዝባችንም ትልቅ ጠቀሜታ ይዞ መጥቷል " ብለዋል።

" ታካሚዎችን ውጭ አገር ሲላኩበት የነበረውን የአሰራር ሂደት ይቀይራል ፤ በሀገር ወስጥ ከፍተኛ ሕከምና መሰጠት ስለሚያስችል የውጭ ምንዛሬ ወጪን ያስቀራል " ብለዋል።

ሆስፒታሉ 425 የህሙማን ተኝቶ መታከሚያ አልጋ አለው ተብሏል።

@tikvahethiopia