TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SPHMMC

ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ሀገር ቨርጅኒያ የሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ አንተነህ ብርሀኑ እና ጓደኞቻቸው ለቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ግምቱ አንድ ሚሊዮን ብር(1,000,000 ብር) የሚያወጣ ለቀዶ ሕክምና የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለግሰዋል፡፡ አንተነህ ብርሀኑ በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ ወደ ኮሌጁ አምጥተው አስረክበዋል፡፡ የሕክምና ቁሳቁሶቹ ለቀዶ ህክምና ክፍሉ በጣም አስፈላጊ የሆኑና እና አንዳንዶቹ በኮሌጁ የሌሉ ናቸው፡፡ አንተነህ ብርሀኑ እና በዚህ በጎ ተግባር የተሳተፉ ወገኖቻችንን ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

(SPHMMC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SPHMMC

የዱከም ነዋሪ የሆኑት 65 ዓመት ሴት በሌላ ተጓዳኝ ሕመም ምክንያት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ለአንድ (1) ቀን ቆይተው ነበር፡፡

ይሁን እንጂ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] በሽታ ምልክት በማሳየታቸው የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ቫይረሱ አንዳለባቸው ተረጋግጧል፡፡ ታማሚዋ በአሁኑ ሰዓት በኮተቤ ኤካ ሆሰፒታል ቀጣይ ሕክምናቸውን አንዲከታተሉ ተልከዋል፡፡

ለታማሚዋ የሕክምና አገልግሎትን ሲሰጡ ከነበሩ በርካታ የጤና ባለሙያዎች መካከል በወቅቱ አስፈለጊውን አልባሳት (PPE) አልተጠቀምንም ወይም አጠቃቀማችን በቂ አይደለም ያሉ ሰባት (7) ባለሙያዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ባለሙያዎች መካከል ሁለቱ (2) ታማሚዋን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩ ናቸው፡፡

እኝሁ ሴት በዛሬው የጤና ጥበቃ ሚኒስትርዋ ዶ/ር ሊያ ታደሰ መግለጫ የተገለጹት 44ኛዋ ታማሚ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

(ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
👏የጤና ባለሙያዎቻችንን እናመስግናቸው👏

በዛሬው ዕለት 'በሚሌኒየም ማገገሚያ ማዕከል' ውስጥ ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ 87 ታካሚዎች አገግመው ወጥተዋል፡፡

ማዕከሉ ከተከፈተ በኋላ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ናቸው፡፡ የህክምና ባለሙያዎቻችንን የዛሬው ቀን በእጅጉ የተደሰቱበት ነበር፡፡ እንኳን ደስ ያለችሁ!

በአሁኑ ወቅት ማዕከሉ ውስጥ 656 ታካሚዎች ህክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

#HAKIM #SPHMMC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SPHMMC

የቅዱስ ዻውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ (SPHMMC) ለ3 ወር ያህል አቋርጦት የነበረውን ህክምና መስጠት እንደጀመረ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

ሆስፒታሉ የኮሮና ወረርሽኝን በመከላከል ረገድ ምርመራዎች ማካሄድና ታካሚዎችን ከመንከባከብ ጋር ተያይዞ ወደ 25 ሺህ የሚጠጉ ምርመራዎችን እንዳከናወነ ነው የገለፀው።

270 አልጋዎችንም በማዘጋጀት ከኮሮና በሽታ ጋር ተያይዞ የተለየ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ታካሚዎች በመቀበል አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር ተጠቅሷል።

ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ እስከ 900 ሰዎችን በመቀበል 640 ድነው መውጣታቸውና አሁን ላይ ደግሞ 150 ሰዎች በህክምና ላይ የሚገኙ እንደሆኑ ተጠቁሟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SPHMMC

የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ 140 ፣ በድህረ ምረቃ 340 በአጠቃላይ 480 ተማሪዎችን በስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ አስመርቋል።

ከዕለቱ ተመራቂዎች 141 ሴቶች መሆናቸው ታውቋል።

የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ በክብር እንግድነት በተገኙበት ተካሂዷል።

መረጃውን ያደረሰን የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#SPHMMC

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በጭንቅላት ውስጥ አላስፈላጊ ውሃ መጨመር (Hydrocephalus ) እና የጀርባ የአፈጣጠር ችግር (spina bifida)ችግር ያለባቸውን ሕጻናት ከየካቲት 9 ቀን ጀምሮ ነጻ ህክምና እንደሚሰጥ ገልጿል።

ለህክምናው ወላጆች ልጆቻቸውን በ976 በመደወል አንዲያስመዘግቡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

#መልዕክቱን_ለሌሎች_ያድረሱ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Attention😷 በሀገራችን ኮቪድ-19 በእጅጉ እያሻቀበ ነው። በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 7,065 የላብራቶሪ ምርመራ 1,332 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 17 ሰዎች ሞተዋል። ትላንት 805 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። በአጠቃላይ 171,210 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,483 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤…
የዛሬ እውነታዎች (መጋቢት 2/March 11) ፦

የኮቪድ ነገር እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው። ዛሬ በተደረገው ምርመራ እንደ ሀገር በሽታው የመገኘት ምጣኔ 19 በመቶ ሲሆን በሽታው የመግኘት ዕድል በጣም ከፍተኛ የሆነበቸው አራት ከተሞች ፦
1. ሐዋሳ - 42%
2. ድሬዳዋ - 27%
3. አሶሳ - 23.5%
4. አዲስ አበባ - 20%

ሁሉም (17) ሞቶች ከአዲስ አበባ ናቸው።

እነዚህ ቁጥሮች በዓለም ጤና ድርጅት መመዘኛ ወደ complete shutdown የሚወስዱ እና እጅግ ከፍተኛ የጥንቃቄ እርምጃ የሚያስፈልጋቸው ናቸው::

አሁንም ፦

1. የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ መጠቀም
2. የእጅ ንፅህና መጠበቅ
3. አላስፈላጊ መሰባሰብ መተው
4. ርቀትን ጠብቆ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል።

ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር

#SPHMMC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Attention😷 በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 5,895 የላብራቶሪ ምርመራ 1,413 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 10 ሰዎች ሞተዋል። ትላንት 1,669 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። በአጠቃላይ 175,467 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,550 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 143,710 ሰዎች አገግመዋል። በአሁን ሰዓት…
የዛሬ መጋቢት 5 ሁኔታ ፦

24% national positivity rate.The higest so far!

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአራት ሰው አንድ ሰው በኮቪድ ተይዞዋል ወይም ኮቪድ ሊኖርበት ይችላል እንደማለት ነው።

ከ20% በላይ የበሽታው ስርጭት የሚታይባቸው ክልሎች/ከተማ አስተዳደሮች ፦
1. ሲዳማ-39%
2. ኦሮሚያ-38%
3. ድሬዳዋ-25%
4. ሐረር-25%
5. አዲስ አበባ-24%

እነዚህ ቁጥሮች ምን ማለት እንደሆኑ አለመገንዘብ በእራስ እና በሀገር ላይ ሞት እንደማወጅ ይቆጠራል።

ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር

#SPHMMC
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#SPHMMC

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ የ75 ዓመት ክብረ በዓል እና የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8 ) ቀንን ምክንያት በማድረግ የካቲት 29 ቀን ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት የሚሰጠው በሴቶች የቀዶ ሕክምና ቡድን አባላት #ብቻ እንደሚሆን አሳውቆናል።

ኮሌጁ በላከል መልዕክት ፤ በተለያዩ የሕክምና ዘርፍ የሰለጠኑ እና ልምድ ያላቸው ቀዶ ሐኪሞቹ በልዩ ልዩ የባለሙያዎች ቡድናቸው ታግዘው አገልግሎት ይሰጣሉ ብሏል።

ይህም የኮሌጁን ሴት ባለሙያዎች የላቀ አገልግሎት እንደሚሰጡ ይህ ጥሩ ማሳያ እንደሆነም አሳውቆናል።

@tikvahethiopia
#SPHMMC

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሕክምና ትምህርት ለመማር መስፈርቶች የሚያሟሉ አመልካቾች ተቀብሎ ማሰልጠን እንደሚፈልግ ገልጿል።

ለማመልከት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች ፦

1. በ2014ዓ.ም በመደበኛ ትምህርት ፕሮግራም 12ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀ/ያጠናቀቀች

2. በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና 1) ሲቪክስ ውጤት ለተያዘላቸዉ ከ700 ያገኙትን ወደ 600 ከቀየሩ በኋላ 2) ሲቪክስ ውጤት ያልተያዘላቸው የሲቪክስ ውጤቱን ቀንሠው በሚያገኙትን ዉጤት መሠረት
• ከስር ከተዘረዘሩት ክልልና ዞኖች ውጪ ያሉ ሁሉም ክልሎች -
👉 ለወንድ 475 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው
👉 ለሴት 460 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላት
• ለአፋር ክልል ፣ ለቦረና ዞን (ኦሮሚያ ክልል) ፣ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ለጋምቤላ ክልል ፣ ለሱማሌ ክልል፣ለደቡብ ኦሞ ዞን(ደቡብ ክልል)፣ ለዋግ እምራ ዞን(አማራ ክልል)ና ለምእራብ ኦሞ ዞን(ደቡብ ክልል)
👉 ለወንድ 450 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው
👉 ለሴት 440 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላት

3. ከ9ኛ-12ኛ ክፍል አማካይ የትራንስክሪፕት ውጤት 80% እና ከዚያ በላይ የሆነ

ማሳሰቢያ፦

1. ማመልከት የሚቻለው Online ብቻ ነው፡፡
2. የማመልከቻ ጊዜው ከመጋቢት 5 - መጋቢት 11 / 2014ዓ.ም ድረስ ብቻ ነው

www.sphmmc.edu.et

ምንጭ፦ SPHMMC

@tikvahethiopia