TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፈው አርብ ሀዋሳ ከተማ ላይ ተፈፅሟል ስለተባለ አንድ የወንጀል ድርጊት ጥቆማ ደርሶት ተመልክቷል። ጉዳዩን በተመለከተ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን እንዲሁም ድርጊቱ ተፈፅሞበታል የተባለውን ክ/ከተማ ፖሊስ ኃላፊዎችን አነጋግሯል። 👉 ተጎጂ የራስሰው ገዛኸኝ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፦ " ሀዋሳ ላይ ቀን ነው በሚባልበት 12:30 የምናሽከረክረውን ' ላንድሮቨር…
#Hawassa

የራስሰው ገዛኸኝ የተባሉ ግለሰብ ሀዋሳ ላይ የተደራጀ ዝርፊያ እና ሳንጃ በማውጣት የግድያ ሙከራ እንደተፈፀመባቸው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈው አሰራጭተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህ መልዕክት በውስጥ ደርሶት ተመልክቷል። የሀዋሳ ፖሊስንም ስለጉዳዩ ደውሎ ጠይቋል።

" በሀዋሳ ከተማ ላይ የተደራጀ የዝርፊያ እና የግድያ ሙከራ ተፈፅሞብናል " ያሉት የራሰው ገዛኸኝ ፅፈው ባሰራጩት ፅሁፍ መሰረት ፦

- ድርጊቱ የተፈፀመው ሀዋሳ፣ በተለምዶ ከአቶቴ ወደ ፉራ በሚወስደው መንገድ " ቦሌ መንደር " አካባቢ በሚገኘው የትራፊክ መብራት ጋር ነው።

- ቀኑ 12/04/2016 ዕለተ #አርብ ከምሽቱ 12:30 ላይ ነው።

- ሲያሽከረክሩት የነበረው ላንድ ሮቨር መኪና ሲሆን ውስጥ እንግዶቻቸው ከሆኑ 3 የመንግስት አካላት ጋር ሆነው ሲጓዙ ነበር።

- በተለምዶ " ቦሌ መንገደር  " የትራፊክ መብራቱ ጋር ሲደርሱ የሚያሽከረክሩት መኪና ከጎን በኩል በከፍተኛ ምት ይመታባቸዋል። አደጋ ያደረሱ ስለመሰላቸው መኪናውን ዳር በማስያዝ ያቆማሉ።

- በመኪናው ውስጥ ከነበሩት አንዱ ከመኪና ፈጥነው በመውረድ የተመታውን መኪና ዙሪያውን ቢመለከቱም የደረሰ አደጋ የለም። ግን ሰዎች ተሰብስበዋል።

- የወረደው ሰው ከመኪናው ኃላ የተሰበሰቡ ወጣቶች የደረሰውን ግጭት ምንነት እየጠየቃቸው በነበረበት ወቅት የራስሰው ገዛኸኝም ከመኪናቸው ወርደው ወደ ወጣቶቹ በመሄድ ምን ተፈጠረ ? ማለት ጥያቄ ይጀምራሉ።

- በዚህ ሁኔታ አስፓልቱ ዳር ከሚገኝ 2 ፑል ቤት አንድ ግሮሰሪ ተጨማሪ ወጣቶች ወጥተው ከበባ ያደርጋሉ፤ ወዲያው አንድ ወጣት በተለምዶ በአከባቢው አጠራር " ባንጋ " የተባለ የሚጠራውን ሳንጃ ይዞ ማሳደድ ይጀምራል።

- በተፈጠረው ሁኔታው #ተደናገጠው ቢያፈገፍጉም ወጣቱ ሊተዋቸው ባለመቻሉ ወደ መኪናው ለመግባት ሲሞክሩ እዛው ጋር የነበሩት ሌሎች ወጣቶች በሩን እንዳይገቡ ይይዙታል።

- ሁኔታው በተደራጀ መልኩ #ዘረፋ መሆኑ ስለገባቸው በሳንጃው ላለመወጋት ይሸሻሉ።

- በዚህ መካከል ከመኪና ውስጥ ያልወረዱት ሰዎች መኪናውን ሎክ ለማድረግ ቢሞክሩም ሌሎች ወጣቶች ከኃላ በር በመክፈት፦
* ላፕቶፕ የያዘ ሻንጣ
* ከአንድ ፕሮግራም ቀረፃ እየተመለሱ በመሆኑ ብላክ ማጂክ ካሜራ ፣
* መቅረፀ ድምፅ የያዘ ቦርሳ ይዘው ተሰውረዋል።

- አካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች ዘራፊዎቹ ከአከባቢው መሰወራቸውን ተመልክተው " ስፍራውን ቶሎ ለቃችሁ ካልሄዳችሁ አሁን ከመጡ #ይገሏችኋል " በማለት አከባቢውን ለቀው እንዲሸሹ ያስፈራሯቸዋል።

- በተጠና ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ የዘረፋ ኦፕሬሽን በመሆኑ ከአከባቢው ለመሄድ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው የፓሊስ አካል እስኪመጣ ጠበቁ።

- በዚህ መካከል አንድ የፓሊስ አባል ይመጣል። ቀርቦ ምንድነው ? ሲል ይጠይቃል። እነሱም የደረሰባቸውን የዘረፋ ወንጀልና የግድያ ሙከራ አስረድተው የህግ ከለላ ቢጠይቁም። ፓሊሱ " በቃ አሁን ከዚህ ሂዱ ልጆቹ ከላልታወቁ ምን ማድረግ ይቻላል ? " በማለት መልሷል።

- የፖሊስ አባሉ ቢያንስ እንኳን #ፓትሮል ደውሎ ኃይል እንዲያስጨምርላቸው ቢነግሩትም ፤ " እኔ የናንተ ጠባቂም ተላላኪም አይደለሁም " የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው ገልጸዋል።

- ወደ አንድ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን ዘንድ ደውለውም እንዲደርሱላቸው ፤  የደረሰባቸውን በደል ቢያስረዱም ከባለስልጣኑ ዘንድ ምንም አይነት እርዳታ አላገኙም።

- ወደ ተለያዩ የህግ አካላት በመደወል #ከ40_ደቂቃ በኃላ አንድ የፓሊስ ፓትሮል ሊመጣ ችሏል።

- የመጡት የፖሊስ አባላት ችግሩን ለመስማት የሞከሩ ሲሆን " የዘራፊዎችን ማንነት እና ስም " ከተፈራፊዎች ይጠይቃሉ። እነሱም መንገደኛ በመሆናቸው ገልጸው የዘራፊዎቹን ማንነት በስምና በአድራሻ ለይቶ ለፓሊስ መናገር የሚችሉበት መንገድ ስላልገባቸው ቢያንስ የተወሱ ወጣቶች የወጡበትን ግሮሰሪ እና ፑል ቤት አሳዩ።

- ከፍተኛ #ክርክር እና አለመግባባት ከተፈጠረ በኃላ የፖሊስ አባላቱ የተፈፀመውን ነገር የዕለት መዝገብ ላይ እንዲያስመዘግቡ በማለት ወደ ታቦር ክፍለ ከተማ ፓሊስ ማዘዣ ጣቢያ እንዲሄዱ አድርገዋል።

- ፖሊስ " የፑል ቤቱ ባለቤቶች  " አንዳንድ ነገር ሲናገሩ በመስማታቸው አስረዋቸዋል። ነገር ግን ዋናዎቹ የተደራጁትን የዘራፊ ቡድኖች የያዘም ሆነ በወቅቱ ለመከታተል የሞከረ አካል የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መልዕክት ከተመለከተ በኃላ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን ለማነጋገር ጥረት አድርጓል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ፤ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ አሁን ላይ በከተማዋ ዉስጥ በተሰሩ በርካታ ስራዎች በኢትዮጵያ ካሉ ከተሞች በጅጉ የተሻለ ሰላም ያላት ከተማ ሀዋሳ መሆኗን ጠቅሰዋል።

ተፈፅሟል የተባለውን ጉዳይ በሶሻል ሚዲያ ሲያዩት #ማዘናቸዉን ገልጸዋል።

ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ፤ ችግር ተፈጥሮ ከሆነ በተዋረድ ለሚመለከተዉ አካል ማቅረብ እንደሚቻልና በተለይ እንዲህ ያለዉን ጉዳይ እንኳን ፖሊስ የትኛዉም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ከማስቆም ወደኋላ እንደማይል ገለጸዋል።

አሁንም " ችግሩ ተፈጽሞብን ፍትህ አጣን " የሚሉ አካላት በየትኛዉም ጊዜ ማመልከት ቢፈልጉ ቢሯቸዉም ሆነ ስልካቸዉ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ብዙዎች ሰላሟን የሚመሰክሩላትን ሀዋሳ ከተማን በትንሹ መገመት አግባብ አይደለም ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ተጎጅዎች እንዲያመለክቱና ቃላቸውን እንዲሰጡ የተደረጉበትን የታቦር ክ/ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር ወንድዬ ከበደን አነጋግሯል።

እሳቸው በሰጡት ምላሽ በወቅቱ መኪናችን ተመታብን ያሉት አካላት ወደፖሊስ ጣቢያዉ በመምጣት ባስመዘገቡት መሰረት በአካባቢዉ ላይ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ተይዘዉ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢ/ር ወንድዬ ፤ የተጠቀሱት ንብረቶች መሰረቃቸዉን በወቅቱ አለመስማታቸውን እና አለመመዝገባቸዉን አስታውሰዉ አሁንም ቢሆን ጉዳዩን በአግባቡ ወደሚመለከተዉ የህግ አካል በማቅረብ በተያዘዉ ምርመራ እንዲካተት ማድረግ እንደሚቻል ገልጸዋል።

ተጎጅዎች " በተደራጀ ዝርፊያ ጥቃት ተፈጽሞብናል " የሚሉት የተሳሳተ መሆኑን የሚያነሱት ኢንስፔክተሩ በወቅቱ ' ግጭት ውስጥ የነበሩ ወጣቶች ' ውስጥ በመግባታቸዉ ለስርቆት ተዳርገዉ ሊሆን ይችል እንደሆነ እንጅ በከተማዉ የተባለዉ አይነት ዝርፊያ በፖሊስና በማህበረሰቡ ትብብር #ታሪክ_የሆነ ጉዳይ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

@tikvahethiopia