TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአገር መከላከያ ሚኒስቴር‼️

በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተግባር ላይ የነበሩ ወታደሮች ኮንቮይ ላይ #የአልሸባብ ታጣቂዎች #ጥቃት_መፈጸማቸውን የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

#የአገር_መከላከያ_ሚኒስቴር ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ‹‹በሠራዊቱ ላይ ጥቃት የደረሰው ኮንቮዩ ከቡራሃካባ ወደ ባይዶአ በመጓዝ ላይ እያለ ሲሆን፣ ሠራዊታችን ጥቃቱን በጽናት በመመከት ኮንቮዩን ባይዶአ ይዞ ገብቷል፤›› ብሏል፡፡

ሠራዊቱ ካሁን ቀደም በርካታ የአልሸባብ ጥቃቶችን #በመመከት አልሸባብን ያዳከመው መሆኑን ያስታወሰው መግለጫው፣ በአሁኑ ጥቃትም አልሸባብ በቀቢፀ ተስፋ የሠራዊቱን ንቅናቄ ለመግታት ሙከራ እንዳደረገ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ሠራዊቱ የአልሸባብን ጥቃት ተከትሎ ጠንካራ የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ በስምሪት ላይ እንደሚገኝም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ዓርብ ጥር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. የአገር መከላከያ ሠራዊት አራት መኪኖች ላይ ጥቃት ተፈጽሞ በርካታ የሠራዊቱ አባላት ተገድለዋል የሚል ዘገባ የወጣ ቢሆንም፣ የመከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ ጥቃቱ ምን ያክል ጥፋት እንዳደረሰ አልገለጸም፡፡ ሆኖም የመከላከያ ሠራዊት በአሚሶም ተልዕኮ በሶማሊያ ሰላም በማስፈን ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስታውሷል፡፡

ምንጭ:- ሪፓርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia