TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በዓመት 44,000 በላይ የሚሆኑ የካንሠር ሕሙማን ሕይወታቸውን ያጣሉ " - ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ

በኢትዮጵያ የካንሠር በሽታ #የከፋ_ደረጃ ላይ እየደረሰ በመሆኑ ማኅበረሰቡ ልዩ ትኩረት እንዲያደርግ ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ አሳስቧል።

የማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " በእኛ አገር ሕሙማን ራሳቸውን ስለሚደብቁና ታክሞ መዳን አይቻልም ስለሚባል በሽታው በጣም እየከፋ ነው " ብለዋል።

ማኅበረሰቡ ወደ ሕክምና ተቋም በወቅቱ በመምጣት ከሕመሙ መዳን እንደሚችል ሊያውቅና ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባም ተጠይቋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ " በአሜሪካን አገር ግን ወደ 15 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ታክመው ድነው ሕይወታቸውን እየመሩ ነው " በማለት ከበሽታው መዳን እንደሚቻል አስረድተዋል።

አክለውም፣ " በኢትዮጵያ ሕሙማን ወደ ሕክምና ተቋም አለመምጣታቸውና ታክሞ መዳን እይቻልም የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ በመኖሩ ወደ 75 በመቶ የሚሆኑት ሕሙማን ሕይወታቸው ያልፋል " ነው ያሉት።

የድርጅቱ ሜዲካል ዳይሬክተር ናትናኤል አለማየሁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ " ባለፉት ዓመታት ውስጥ የካንሠር ሕሙማን ወደ ሕክምና የመምጣት ቁጥራቸው የመጨመር ሁኔታ ይታያል " ብለዋል።

አክለውም፣ " በየዓመቱ ከ60,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በካንሠር በሽታ ይያዛሉ። ከእነዚህ ውስጥ 44,000 በላይ የሚሆኑት የካንሠር ሕሙማን ሕይወታቸውን ያጣሉ " ነው ያሉት።

"ከካንሠር ሕመም መዳን ይቻላል ተገቢዉን ምርመራ እና ህክምና በተገቢዉ ጊዜ በማድረግ መዳን ይቻላል" ያሉት ናትናኤል (ዶ/ር)፣ የካንሠር ሕሙማን ሕይወታቸው የሚያልፍበትን ምክንያት ሲያስረዱ፣ " ሕሙማን ወደ ሕክምና ማዕከል የሚመጡት የሕመም ደረጃቸው ከፍ ካለ፣ ሥር ከሰደደ፣ መዳን የሚቻልበት ደረጃ ካለፈ በኋላ ነው " ብለዋል።

በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ያለበት ምክንያት ምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ናትናኤል (ዶ/ር)፦
- ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ መስፋፋት፣ በቂ ያልሆነ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ እና የአኗኗር ዘይቤ መቀየር
- የሲጋራ፣ ሽሻ አጫሾች መበራከት የአልኮል መጠቀም
- ለተለያዩ ኬሚካሎች መጋለጥ
-ከተለያዩ ኢንᎊክሽኖች ጋር የሚያያዙ የካንሰር አይነቶች መበራከት
- በወቅቱ ሕክምና ሳያገኙ የኖሩ ሰዎች አሁን አሁን ወደ ሕክምና እየመጡ በመሆኑና ሌሎች መሰል ምክንያቶችን ጠቅሰዋል።

ወደ ሕክምና የሚመጡት 70 በመቶ የሚሆኑት የካንሠር ሕሙማን የህመሙ ደረጃ ከፍ ካለ እና ስር ከሰደደ መሆኑን ተናግረዋል። ለህሙማን ሁለንተናዊ የሆነ እንክብካቤ እና ድጋፍ ሁሉም ካለዉ ቀንሶ እንዲያደርግ፣ ማህበረሰቡም በካንሰር ላለመያዝ አጋላጮቹን መከላከል እና ቅድመ ምርመራ ላይ እንዲያተኩር አሳስበዋል።

ድርጅቱ የ20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በዛሬው ዕለት በማሪዮት ሆቴል ያከበረ ሲሆን፣ ድርጅቱ እስካሁን ከ3,000 ሺሕ በላይ የካንሠር ሕሙማን እንዳከመ፣ በአሁኑ ወቅት ከ150 በላይ ሕክምና የሚጠባበቁ እንዳሉ ተነግሯል።

መረጃው የአዲስ አበባ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ይነበብ

ኢትዮጵያ ውስጥ የካንሠር በሽታ #የከፋ_ደረጃ ላይ እየደረሰ በመሆኑ ማኅበረሰቡ ልዩ ትኩረት እንዲያደርግ ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ አሳስቧል።

የካንሠር ሕሙማን ቁጥር እየጨመረ ያለው ለምንድነው ?

የድርጅቱ ሜዲካል ዳይሬክተር ናትናኤል አለማየሁ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ የዓመቱ ወደ ከ60,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በካንሠር በሽታ ይያዛሉ። ከእነዚህ ውስጥ 44,000 በላይ የሚሆኑት የካንሠር ሕሙማን ሕይወታቸውን ያጣሉ።

በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ያለበት ምክንያት ፦

- ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ መስፋፋት፣

- በቂ ያልሆነ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ እና የአኗኗር ዘይቤ መቀየር

- የሲጋራ ፣ ሽሻ አጫሾች መበራከት ፣ የአልኮል መጠቀም

- ለተለያዩ ኬሚካሎች መጋለጥ፣

- ከተለያዩ #ኢንᎊክሽኖች ጋር የሚያያዙ የካንሰር አይነቶች መበራከት

- በወቅቱ ሕክምና ሳያገኙ የኖሩ ሰዎች አሁን አሁን ወደ ሕክምና እየመጡ በመሆኑና ሌሎች መሰል ምክንያቶች ናቸው።

ወደ ሕክምና የሚመጡት 70 በመቶ የሚሆኑት የካንሠር ሕሙማን የህመሙ ደረጃ ከፍ ካለ እና ስር ከሰደደ በኃላ ነው።

ዶ/ር ናትናኤል ፤ " ከካንሠር ሕመም መዳን ይቻላል " ያሉ ሲሆን ይህም ተገቢዉን ምርመራ እና ህክምና በተገቢዉ ጊዜ ማድረግ ሲቻል ፣ ስር ሳይሰድ ህክምና ካገኘ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ለህሙማን ሁለንተናዊ የሆነ እንክብካቤ እና ድጋፍ ሁሉም ካለዉ ቀንሶ እንዲያደርግ ፣ ማህበረሰቡ በካንሰር ላለመያዝ አጋላጮቹን መከላከል እና ቅድመ ምርመራ ላይ እንዲያተኩር አሳስበዋል።

@tikvahethiopia