TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ቀውስ በአንድ ቀን 96 ሰዎች መገደላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል #ዘይኑ_ጀማል ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ሰዎቹ የተገደሉት ቀውሱ በተነሳበት የመጀመርያው ቀን #ሐምሌ 27፣ 2010 ዓ. ም. ሲሆን፤ በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች #ግድያው መፈጸሙን ተናግረዋል።

ሰዎቹ የተገደሉት #በአሰቃቂ ሁኔታ መሆኑን ተናግረው፤ ሀይማኖትና ብሔርን ለይቶ የተሰነዘረ ጥቃት እንደሆነ አክለዋል።

"ከዘር #ጭፍጨፋ አይተናነስም" ብለዋል። መነሻው የክልሉ አመራሮች አቅደው፤ ተግባሩን የሚፈጽሙ ሰዎች አሰልጥነውና አሰማርተው መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

እስከ አሁን የክልሉን የቀድሞ ፕሬዘዳንት አቶ አብዲ ሞሀመድ ኡመርን ጨምሮ ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

'ሄጎ' በመባል የሚታወቀው ቡድን በግድያው እጁ ስለመኖሩ ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ፤ "በዋናነት በግጭቱ ተሳትፈዋል የሚባሉት #ሄጎ በሚባለው ቡድን አባላት ናቸው። ሄጎ የሚባለውን #የፈጠሩ፣ እቅዱን ያቀነባበሩ የክልሉ የፖለቲካ #አመራሮች፣ የክልሉ የካቢኔ አባላትና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ #ባለስልጣኖችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየሰራን ነው" ብለዋል።

ልዩ ፖሊስ በግድያው ተሳትፎ ስለመሆኑ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ማን በምን ደረጃ ተሳተፈ የሚለው ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል" ሲሉ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

በጅግጅጋ የሚኖሩ የተለያዩ አካባቢዎች ተወላጆች ስጋት እንዳላቸው የሚናገሩት ጄኔራል ዘይኑ፤ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት የክልልሉን ዋና ዋና ከተማዎች መቆጣጠሩ አንጻራዊ ሰላም ማስፈኑን ገልጸዋል።

በአሁን ወቅት አዲሱ የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፋ ኡመር በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ህብረተሰቡን እየጎበኙ መሆኑን ተናግረዋል።

የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ አካባቢው መመለስ ቀጣዩ ስራ መሆኑን ተናግረው፤ በዚህ ረገድ የአካባቢው ማህበረሰብ እየተባበራቸው እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሐምሌ_22

ኢትዮጵያ ቡና

ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ ሰኞ በሙሉ ኢትዮጵያ ከተማዎች እንደሚተከል ይጠበቃል። ሁላችንም የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ማልያ በመልበስ ከጠዋቱ 1:00–1:30 በተመደበልን ቦታ በሰአቱ በመገኘት ቀጥታ የክለባችንን አሻራ ለሀገራችን እናሳርፍ።

የመሳፈርያ ቦታዎች፦

#ፒያሳ_መዘጋጃ
#ሜክሲኮ_ቡና_እና_ሻይ
#መስቀል_አደባባይ
#ጀሞ
#ሳሪስ_አደይ_አበባ
#ሰባተኛ_ቶታል

#ኢትዮጵያ_ቡና @BUNA_GEBEYA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ ክትባት!

በአሁን ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ100 በላይ ኮቪድ-19 #ይከላከላሉ የተባሉ ክትባቶች ሙከራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ይታወቃል።

ዛሬ ደግሞ በአውስትራሊያ የመጀመሪያ የሆነው በሰዎች ላይ የሚደረግ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙከራ በሜልቦርን ተጀምሯል።

ሙከራ እየተደረገበት ያለው ክትባት 'NVX-CoV2373' የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን ክትባቱ 'ኖቫቫክስ' በተባለው የአሜሪካ ኩባንያ የተመረተ ነው።

ተመራማሪዎች የሚሞክሩት በ130 አዋቂ ጤነኛ ሰዎች ላይ ነው። እንደ #BBC መረጃ የክትባቱ ሙከራ ውጤት #ሐምሌ ወር ላይ ይታወቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

#ሐምሌ_19 የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ይከበራል።

ከመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም (ቤተመንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል) በደረሰን መልዕክት የፊታችን ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል በዓል በደመቀ መልኩ ይከበራል።

"በዓመት 2 ጊዜ ታህሳስ እና ሐምሌ 19 ብቻ" እንደሚነግስ የተገለፀልን ሲሆን የዛሬ ዓመት በኮሮና ወረርሽኝ እና በአንዳንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት ለምዕመናን ውስን ሆኖ ነበር የተከበረው።

በዚህ ዓመት ግን ምዕመናን ራሳቸውን ጠብቀው ከተሟላ ፓርኪንግ ጋር እንዲሁም መንገዱም ስለተከፈተ መጥተው ማክበር ይችላሉ ተብሏል።

በዚህ አጋጣሚ አንዳንድ ገዳሙ እንደተዘጋ ተደርጎ የሚናፈሱ መረጃዎች ፍፁም #ሀሰተኛ ናቸው።

የ124 ዘመን እድሜ ያለው የመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በዳግማዊ ንጉሰ ነገሥት አፄ ምንሊክ መታነጹ ይነገራል።

አድራሻ ፦ ታላቁ ቤተመንግሥት (አንድነት ፓርክ) ጎን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ 📈 ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህ መሰረት ፦ 👉 ቤንዚን በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም 👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም 👉 ኬሮሲን በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም 👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 53 ብር ከ10 ሳንቲም 👉 ከባድ…
ነዳጅ ምን ያህል ጨመረ ?

ከሚያዚያ 30 / 2014 ዓ/ም አስንቶ ይኸው ያለንበት ሰኔ ወር ማብቂያ ድረስ የነበረው የነዳጅ ችርቻሮ ዋጋ መሸጫ ይህ ይመስል ነበር (ጭማሪ የተደረገው ሚያዚያ 30 እንደነበር እና በሰኔ ወር ባለበት መቀጠሉ አይዘነጋም) ፦

👉 ቤንዚን በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ፣
👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣
👉 ኬሮሲን በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣
👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 52 ብር ከ45 ሳንቲም፣
👉 ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 51 ብር ከ78 ሳንቲም

ከዛሬ #ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ #ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ፦

👉 ቤንዚን በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም
👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም
👉 ኬሮሲን በሊትር 49 ብር 02 ሳንቲም
👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 53 ብር 10 ሳንቲም
👉 ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 52 ብር 37 ሳንቲም

#ልብ_ይበሉ ፦ ከዛሬ በኃላ ባለው ጭማሪ የቤንዚን ፣ የኬሮሲን እና የነጭ ዋጋ ላይ ለህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ወይም የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች 15 % በመንግስት እንዲደጎሙና ቀሪውን 10 % እንዲከፍሉ በማድረግ የድጎማ መጠኑን በቴሌ ብር ተመላሽ እንዲሆንላቸው ይደረጋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ 📈 ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህ መሰረት ፦ 👉 ቤንዚን በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም 👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም 👉 ኬሮሲን በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም 👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 53 ብር ከ10 ሳንቲም 👉 ከባድ…
#ነዳጅ

ከነገ #ሐምሌ_23 ቀን 2014 ዓ.ም - #ነሐሴ_30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የአውሮፕላን ነዳጅን በሚመለከት ግን በወቅታዊ የዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ በመጣው አዲስ አበባ ላይ በሊትር 84 ብር ከ42 ሳንቲም እንዲሸጥ መወሰኑንም ገልጿል።

ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ የአሠራር ሥርዓት በነሐሴ ወር በተመሳሳይ እንደሚቀጥልም የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ከ2.5 ቢልየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ሀይሌ ግራንድ አዲስ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል በይፋ ስራ ጀመረ።

በመዲናችን አዲስ አበባ በየካ ክፍለ ከተማ ላም በረት መናኽሪያ አካባቢ በ15 ሺህ ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈውና ባለቤትነቱ የሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ የሆነው የሀይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ስምንተኛ መዳረሻ " ሀይሌ ግራንድ አዲስ አበባ " ሙሉ በሙሉ ስራ መጀመሩ ዛሬ ተገልጿል።

2.5 ቢልየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት "ሃይሌ ግራንድ አዲስ አበባ" እ.ኤ.አ ከጥቅምት 01/2022 ጀምሮ በሙከራ ደረጃ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።

ሆቴሉ ለ450 ሰራተኞች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ለ120 #አዲስ_ተመራቂ ሰራተኞች ስልጠና በመስጠት ስራ እንዱጀምሩ መደረጉ ተገልጿል።

ሆቴሉ በውስጡ ፦

- 130 ክላሲክ ፤ 14 ስዊት ፤ 12 ፕሪሚየር እና 1 ፕሬዝዳንሻል ባጠቃላይ 175 አልጋዎችን የያዘ 157 ምቹና ሰፊ የመኝታ ክፍሎችን
- 4 ሬስቶራንቶች እና 2 PDR ፤
- 4 ባር፤
- 1pastery & coffe shop፤ 
- 1 የተሟላ የባህል ምግብ አዳራሽ፤
- 8 የስብሰባ አዳራሾች እና 2 ትላልቅ Ballrooms
- የጤና እና የውበት መጠበቂያ ማዕከል
- ጂም እንዲሁም 200 ተሽከርካሪዎችን የሚይዝ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ይዟል።

ሆቴሉ የተገነባው በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ብቻ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በቀጣይ #ሐምሌ ወር ላይ #የወላይታ_ሶዶው ሆቴል እንደሚመረቅ፤ #የሻሸመኔው ሪዞርትም ጥገና ላይ እንዳለ ተገልጿል።

Tikvah Family (Addis Ababa)

@tikvahethiopia
#MoE

" የመውጫ ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና ወስዶ መቀጠል እንዲችል የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

250 ሺ ለሚጠጉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በመጪው #ሐምሌ_ወር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተጠናቀቅ እንደሚገኝ በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሐመድ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት ከመንግሥት እና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ወስደው ማለፍ ያልቻሉ ተማሪዎች ደጋግመው መፈተን የሚችሉበት ዕድል መኖሩን ኃላፊው አመልክተዋል።

ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና ወስዶ መቀጠል እንዲችል የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ በትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በመዘጋጀት ላይ ይገኛል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ተፈታኙ ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብሎ ባሰበ ጊዜ ፈተናውን መውሰድና ማለፍ ከቻለ የዲግሪ ማረጋገጫ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።

የመውጫ ፈተናው በ #ኦንላይን እንደሚሰጥ ያመለከቱት ኃላፊው፤ ለዚህ ያመች ዘንድም የሶፍትዌር ማዘጋጀትን ጨምሮ ፈተናውን በስኬት መስጠት የሚያስችሉ ሥራዎች በመሠራት ላይ ናቸው ብለዋል።

ተማሪዎች ዋናውን ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ሞዴል ፈተናዎች እንደሚወስዱ ጠቅሰዋል፡፡ 

#ኢፕድ

@tikvahuniversity @tikvahethiopia