TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ዶክተር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የዶክተር መቅደስ ዳባ ሹመትን አጽድቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዶክተር መቅደስ ዳባን የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ማፅደቁን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (etv) ዘግቧል። …
#DrMekdesDaba

ዛሬ ዶ/ር ሊያ ታደሰን በመተካት የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ዶክተር መቅደስ ዳባ እ.ኤ.አ በ2021 በማኅጸንና ጽንስ ሕክምና ዘርፍ ባደረጉት ምርምር እና አስተዋጽዖ በሴቶች ዘርፍ በዓለም የጽንስና የማኅፀን ፌዴሬሽን ከመላ ዓለም ከተመረጡት ሃኪሞች አንዷ በመሆን የ #FIGO አዋርድ / ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ትውልድ እና እድገታቸው በአዲስ አበባ ሲሆን የተወለዱት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ውስጥ ነው።

የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን (ከነርሰሪ እስከ 12ኛ ክፍል) በአዲስ አበባ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት ነው የተከታተሉት።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመግባት የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ትምህርታቸውን ተከታትለዋል ፤ ልክ እንደጨረሱ በዛው ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አገልግለዋል።

የህብረተሰብ ጤና ማስተርስ ትምህርታቸውንም እዛው ዩኒቨርሲቲ ተምረዋል።

የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተከታትለዋል።

ዶክተር መቅደስ ዳባ በስራው ዓለም በዓለም የጤና ድርጅት (WHO) የምክትል ዳይሬክተር ረዳት ፣ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሃኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ፣ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በጽንስና ማህጸን ትምህርት ክፍል ውስጥም ሰርተዋል።

ዛሬ በይፋ የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

@tikvahethiopia