TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አቶ ጌታቸው ከሀገር ወጡ??❗️

ይህ የአንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ዘገባ ነው...

"ሰበር ዜና-ከአዲስ አበባ ለአዋዜ የደረሰው ትኩስ ዜና። የቀድሞው ተፈሪ የብሄራዊ ስለላና ደህንነት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ ከኢትዮጵያ #ጠፍተው ሱዳን መግባታቸው በይፋ #ተረጋገጠ። አንድ ከፍተኛ ውስጥ አዋቂ ምንጭ ምሽቱን ለአዋዜ እንደተናገሩት ከሆነ ፌደራል መንግስቱ በህግ ይፈልጋቸው የነበሩ ባለስልጣን ናቸው ጌታቸው አሰፋ።

ማዕከላዊ መንግስቱ በይፋ በህግ #ሊጠይቃቸው እና #ሊፋረዳቸው የሚፈልጋቸው ባለስልጣን ሆነው ሳሉ በትግራይ ፖሊስ ሽፋን ወደ ሱዳን እንዲወጡ አድርጓል ብለዋል ለአዋዜ። በዚህ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።"

ጋዜጠኛ አለምነህ ጨምሮ እንደገለፀው ከሆነ እየተደረገ በሚገኘው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ አቶ ጌታቸው አሰፋ አልተገኙም። ይህም የሆነው ከሀገር በመውጣታቸው ነው ብሏል ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮ ከምንጮች አገኘሁት ባለው መረጃ እንዲህ ብሎ በሰበር ዜናው ዘግቧል⬇️

"የእስር ማዘዣ የተቆረጠባቸው የቀድሞ የደህንነት ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ወደ ሱዳን #መሸሻቸው ተነገረ።"

◾️ውድ የተከባራቹ የቻናላችን ቤተሰቦች ይህን ዜና #እስካሁን ድረስ ከሌሎች የመንግስትም ሆነ የግል የሚዲያዎች #ማረጋገጥ አልተቻለም።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የገዋኔው ጥቃት...

/በትግራይ ዋልታ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን/

√የትግራይ ክልል ፀጥታ እና አስተዳደር ጽህፈት ቤት የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ #ሀፍታይ_መለስ ጥቃቱ በዛሬው ዕለት ጠዋት 3 ሰዓት ተኩል ገደማ ላይ መፈፀሙን ተናግረዋል።

√በጥቃቱ ከቆሰሉ ስድስት ሰዎች መካከል የአንዱ ሕይወት #ማለፉንም ተገልጿል።

አቶ ሀፍታይ መለስ ስለጥቃቱ ይህ ብለዋል...

«የትግራይ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን ከጨዋታ እየተመለሰ መንገድ ላይ ማንነታቸው #እስካሁን ድረስ ማንነታቸው በግልፅ ማን እንደሆኑ ያላወቅናቸው ታጣቂዎች ጥቃት አድርሰዋል። በደረሰው ጥቃት ወደ ስድስት የቡድኑ አባላት ቆስለዋል። ከቆሰሉት ሁለቱ #ከበድ ያለ ጉዳት ደርሶባቸው ነበር። አንደኛው ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል። በጣም #የሚያሳዝን እና እጅግ የሚያስቆጭ አደጋ ነው»

እንዲሁም...

√የትግራይ ክልል የጸጥታ እና አስተዳደር ጽህፈት ቤት ጥቃቱን "በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለው #አረመኒያዊ ድርጊት ነው" ሲል #አውግዞታል። የጥቃቱ ፈፃሚዎች ማንነት እንደማይታወቅ የገለጸው ጽህፈት ቤቱ "ማንም ሽፍታ እየተነሳ በአውላላ ሜዳ ላይ ዜጎችን ለአደጋ እንዲያጋልጥ እያደረገው ያለው የፌዴራል እና የክልል መንግስታት የዜጎችን በነፃ የመንቀሳቀስ መብት ላይ #ብቁ ስራ መስራት በሚችሉበት ቁመና ላይ አለመገኘታቸው ነው" ሲል #ወቅሷል

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እጅግ_በጣም_አሳሳቢ

የዛሬ መጋቢት 9 ሁኔታ ፦

- 600 ከፍተኛ ክትትል እና ፅኑ ሕክምና የሚፈልጉ ወገኖች

- በአንድ ቀን በቫይረሱ የተያዙ 2,057 ይህ 26% ሀገራቀፍ በበሽታ የመያዝ ምጣኔ ነው (#እስካሁን_ከፍተኛው) በማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ (COMBAT) ወቅት እንኳን ይህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር አስመዝግበን አናውቅም ፤

- 10 ሕይወታቸው ያጡ ዜጎች

በዛሬው ቀን ከተመረመሩት ዉስጥ 8 ክልሎች ከፍተኛ (ከ20% በላይ) የበሽታ ስርጭት ታይቶባቸዋል ፦

1. ሲዳማ-45%
2. ድሬዳዋ-40%
3. አዲስ አበባ-26%
4. ኦሮሚያ- 31%
5. ደቡብ- 20%
6. አማራ- 20%
7. ቤንሻንጉል-29%
8. ሐረር- 23%

ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ስለ ወቅታዊ የሰሜን ኢትዮጵያ ምን አዲስ ነገር አለ ?

1. ህወሓት ከሰሞኑን የአማራ ክልል ፤ ሰሜን ወሎን በመልቀቅ መውጣቱን እና የወጣውም የቦታ ማሻሻያ ለማድረግ መሆኑን በመግለፅ አስፈላጊ በሆነ ሰዓት ተመልሶ ሊገባ እንደሚችል ባወጣው በመግለጫ አሳውቋል።

ህወሓት በራሴ ስለመውጣቴ በላጎ፣  ቃሊም፣ ወርቄ፣ ተኩለሽ ጎብየ ፣ ቆቦ ያለው ህዝብ በደንብ ያውቀዋልም ብሏል።

ምንም እንኳን ህወሓት የሰሜን ወሎ አካባቢያዎችን በራሴ ለቅቄ ወጣሁኝ ቢልም የቆቦ አስተዳደር የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል ፣ ፋኖ ፣ የሚሊሻ / በጥምር ጦሩ ህወሓትን " አይቀጡ ቅጣት በመቀጣት " አካባቢውን ነፃ እንዳደረጉ በይፋ አሳውቋል። በፌዴራል መንግስት ሆነ በአማራ ክልል መንግስት በኩል #እስካሁን የተሰጠ አስተያየት ሆነ የተባለ ነገር የለም።

2. የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ህወሓት በቆቦ በጤና ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶችንና የህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ ውድመት ማድረሱን ከከተማው ነዋሪ ቤትም ገንዘብ ጨምሮ የተለያዩ ቁሳቁሶችን መዝረፉን ገልጿል። በተጨማሪ በተለያዩ የዞኑ አካባቢዎች ሴቶች መደፈራቸውን የገለፀው ዞኑ ህወሓት በህብረተሰቡ ላይ ያደረሰውን ሰብዓዊ፣ ቁሳዊና አካላዊ እንዲሁም ስነ ልቦናዊ ጉዳት በዝርዝር እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

3. ህወሓት ዛሬ በትግራይ ክልል ፤ አዲዳይሮ ከተማ ላይ የድሮን ድብደባ ተፈጽሞ በርካታ ህፃናት እና አረጋውያን ንፁሃን ሰለባ መሆናቸውን ገልጿል። የድሮን ጥቃቱ ሰለባ ያደረጋቸው ተፈናቃዮች መሆናቸውንና እነዚህ ተፈናቃዮች አዲስ ባገረሸው ጦርነት ሳቢያ በቅርቡ ከአዲያቦ የተፈናቃዮች መጠለያ ተፈናቅለው የነበሩ መሆኑን ገልጿል።

NB. ከቀናት በፊት ህወሓት ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ባለችው " አዲ ዳዕሮ "  ላይ የኤርትራ ኃይል የአየር ጥቃት ሰንዝሮ ንፁሃን ሰለባ እንደሆኑ ገልጾ ነበር። ለዚህ የህወሓት ክስ በኤርትራ በኩል የተሰጠ ምላሽ አልነበረም።

ነገር ግን ይኸው ክስ ከ " ህወሓት " በተሰማ ሰሞን በኢትዮጵያ መንግስት ስር ያለው የ " ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ " በትግራይ ክልል ' ዓዲ ዳዕሮ ' የኢትዮጵያ አየር ኃይል በተመረጡ ዒላማዎች ወታደራዊ ቁሳቁስና ተተኳሾች ያሉበትን ቦታ ዒላማ አድርጎ እርምጃ መውሰዱን አሳውቆ ነበር።

መረጃ ማጣሪያው የሀገር መከላከያ ሠራዊት በንጹሃን ላይ ጉዳት ሳያደርስ በከፍተኛ ጥንቃቄና የዒላማ ጥራት የህወሓትን ወታደራዊ አቅሞች ነጥሎ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ነበር በወቅቱ አሳውቆ የነበረው።

4. ዳግም ባገረሸው ግጭት ተፈናቅለው የነበሩ እና በተለያዩ ከተሞች የነበሩ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው መመለስ ጀምረዋል ሲል ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። ወደ ቆቦ ከተመለሱ መካከል ኔትዎርክ ወደ ሚሰራበት ቦታው ወጥተው የደወሉ ከተፈናቀሉበት ወደ ቀያቸው ሲመለሱ አንድም ንብረታቸው እንደሌለ ገልፀዋል። በቤት ውስጥ የነበሩ ንብረቶች አንድም ሳይቀር እንደተወሰደባቸው ፤ ከብቶች ፣ ፍየሎች እና በጎችም ሁሉ ታርደው ተበልተው እንደጠበቋቸው አንድ ግለሰብ ተናግረዋል።

5. የመርሳ ከተማ አስተዳደር ፤ በከተማው ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች አካባቢያቸው ነፃ መውጣቱን ተከትሎ ወደቄያቸው እየተመለሱ መሆኑን ዛሬ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል  አሳውቋል። ወንዶች ከትላንት ማታ ጀምረው መውጣታቸውን ፣ ህፃናት ፣ እናቶች ፣ ሴቶች ደግሞ ከጥዋት ጀምሮ ወደ ቄያቸው እየተመለሱ መሆኑን አመልክቷል። በመርሳ ከተማ እስከ 40 ሺህ የሚደርሱ የራያና ቆቦ ወረዳ ተፈናቃዮች በመጠለያዎችና ከህብረተሰቡ ጋር ተጠግተው ይኖሩ እንደነበር ከተማው አመልክቷል።

6. የአውሮፓ ፓርላማ ነገ ረቡዕ ስብሰባ እንደሚያደርግ የተነገረ ሲሆን በዚህ ስብሰባው በአፍሪካ ቀንድና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ይወያያል ተብሏል። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመወያየት የያዘው አጀንዳ ፤ " በትግራይ ክልል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ እና የሰብዓዊ መብት ሁኔታ በተለይ የህጻናት ሁኔታ "  እንደሆነ ተሰምቷል።

7. የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሃፊና የአስቸኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ በዝርዝር ሳያብራሩ የድርጅታቸው የሰብአዊ እርዳታ ባልደረቦች ከበርካታ ሳምንታት እገዳ በኋላ ዛሬ ከትግራይ ክልል በሰላም መውጣት መቻላቸውን ገልፀው በዚህ "በጣም እፎይታ" እንዳገኙ ገልፀዋል።

" ይህ አበረታች ዜና ነው " ያሉት ግሪፊትስ " ተጨማሪ እንቅስቃሴዎች ያለችግር እንደሚሄዱ አምናለሁ " ብለዋል። ይህ #አስከፊ_ግጭት ማብቂያ እንዲኖረው ውይይት ብቸኛው መንገድ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ግሪፊትስ ለሁሉም ወገኖች ፦ ድርድሩን እንዲቀጥሉ ፤ ሁሉንም ሰላማዊ ሰዎች እንዲጠብቁ ፤ የሰብአዊ ሰራተኞችን ደህንነት እና ለተቸገሩ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መዳረሻ እንዲያረጋግጡ ፤ ፈጣን እና ያልተቋረጠ የሰብአዊ አቅርቦቶች ወደ ክልሉ (ትግራይ ክልል) እንዲገቡ እንዲፈቅዱ እጠይቃለሁ ብለዋል።

@tikvahethiopia
የት ገቡ ?

(በባይሽ ኮልፌ)

#እስካሁን_አልተገኙም !

👉 ወጣት አብርሀም በየነ ከ3 ዓመት በፊት ከሚኖርበት ሀዋሳ ወደ ወልቂጤ ሚቄ የሚባል ቦታ መጥቶ ወረዳ ውስጥ ስራውን እየሰራ መስከረም 25 " እናቴ ናፍቃኛለች አይቻት ልምጣ " ብሎ ለጓደኞቹ ነግሮ ከቢሮና ከተከራየበት ቤት ቢወጣም እናቱ ጋር ሳይደርስ ወደ ቤቱም ሳይመለስ የት እንደገባ ጠፍቶ 2 ወር አልፎታል። በየቀኑ ይደውልላት የነበረው እናት " የምሄድበት ግራ ገባኝ ምን ልሁን? " እያለች ቤተክርስቲያን እየዞረች በፀሎት እያነባች ነው 😭 ስልኳ-0985132283 (እልፍነሽ-እናት)

👉 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግራውንድ ቴክንሽያን ዳዊት ምትኩ ከሚኖርበት አምባሳደር ኮንዶሚኒየም አካባቢ ድንገት እንደወጣ ሳይመለስ 24 ቀናት ተቆጥረዋል። እናትና አባት እንዲሁም እህቱ እያለቀሱ መንገድ ለመንገድ እየተንከራተቱ ነው። (0941213747-የእህቱ ስልክ)

👉 የ2 ህፃናት አባት በሙያው ጎበዝ ሼፍ የሆነው ዘሪሁን ቢሰጥ ሀያት አካባቢ የሚከፈት አዲስ ሆቴል ውስጥ ስራ ሊጀምር እንደሆነ ለባለቤቱ ነግሯት ሰኞ ህዳር 12 ዓ/ም በስራው ዙሪያ ለመነጋገር ቀጠሮ እንዳለውና በዛውም ኬጂ የምትማረው የመጀመሪያ ልጁን ኮተቤ የሚገኘው አፕል አካዳሚ ላድርሳት ብሎ እንደወጣ ሳይመለስ ቀርቷል። 18 ቀናት ተቆጥረዋል ፤ ባለቤቱ "መቋቋም አቃተኝ፣ አመመኝ ድፍን ያለነገር ሆነብኝ " እያለች ነው። (0920181284-ሰብለ ባለቤቱ)

መልዕክቱን ሼር በማድረግ ያፋልጉን !

(ባየሽ ኮልፌ)

@tikvahethiopia
#Amhara

#እቅድ፦ 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ

#እስካሁን_የተመዘገቡት ፦ 2,937,556 ተማሪዎች

በአማራ ክልል ለዘንድሮ ዓመት ትምህርት ይመዘገባሉ ተብለው ከታሰቡት 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎች መመዝገብ የተቻለው 2,937,556 ተማሪዎችን እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ይህ ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ሲሆን ካለፉት ዓመታት ሲነፃፀር እቅዱ አጥጋቢ እንዳልሆነ አመልክቷል።

የሚጠበቀውን ያህል ተማሪዎች እንዳይመዘገቡ ከሆነበት ምክንያቶች አንዱ በክልሉ ውስጥ በልዩ ልዩ ቦታዎች ያለው የትጥቅ ግጭት መሆኑ ተነግሯል።

አንዳንድ ዞኖች እስካሁን ጭራሽ ምዝገባም ያልጀመሩ ሲሆን እነዚህም የምዕራብ አማራ አካባቢዎች ፣ ምስራቅ ጎጃም ፣ ምዕራብ ጎጃም ደብረማርቆስ ፣ ሰሜን ጎጃም እንደሆኑ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በክልሉ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ተፅእኖ አሳድሮብናል ያለው ትምህርት ቢሮ አንፃራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች ላይ የተማሪ ምዝገባ መከናወኑን አመልክቷል። አንዳንድ ዞኖችም የተሻለ አፈፃፀም አስመዝግበዋል ሲል አክሏል።

አሁንም የምዝገባ ቀኑ ያልተገደበ ሲሆን ዞኖች ጎን ለጎን የመማር ማስተማር ስራውን እና ምዝገባውን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው ማለቱን ቪኦኤ ዘገቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia