TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሳውላ ከተማ #ረብሻ ሁለት ሰዎች ተገደሉ አምስት ቆሰሉ‼️
.
.
በትናንትናው ዕለት በጋሞ ጎፋ ዞን #ሳውላ_ከተማ በተካሔደ ስብሰባ ላይ በተቀሰቀሰ ኹከት ሁለት ሰዎች #መገደላቸውን እና አምስት መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የሳውላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር #ብስራት_አንበርብር በከተማዋ ሊካሔደ በታቀደው ስብሰባ ላይ የተፈጠረውን ረብሻ ለመቆጣጠር የጸጥታ ኃይሎች በተኮሱት ጥይት ሁለት ሰዎች መገደላቸውን እና አምስት ሰዎች
መቁሰላቸውን ለ«DW» አረጋግጠዋል።

በስብሰው የተካፈሉ አንድ የአይን እማኝ በዞኑ ጉዳይ ላይ ለመመካከር የተጠራውን ስብሰባ "የሚቃወሙ ብዙ ወጣቶች ወጥተው ነበር። መጨረሻ ላይ እኛን ሊወክሉ የማይችሉ ሰዎች ወደ ስብሰባው መምጣት የለባቸውም በሚል ይመስለኛል" ሲሉ የኹከቱን ምንጭ ተናግረዋል። ስብሰባው እንደታቀደው ሳይካሔድ መቋረጡን የተናገሩት የአይን እማኙ የድንጋይ መወራወር ድርጊት መመልከታቸውም ገልጸዋል።

ኮማንደር ብስራት አንበርብር በበኩላቸው "እንግዶችም ወደ አዳራሹ ሊመጡ አልቻሉም። [ወጣቶቹ] ዙሪያውን ከበቡ። እኛ ስንከላከል በድንጋይ መስታወቶችን መስኮቶችን እየመቱ በአጥር ላይ ዘለው ለመግባት ጥረት ሲደረግ ነው የጸጥታው ኃይል በተኩስ አካባቢውን በተኩስ ለማስለቀቅ ጥረት ያደረገው። ሁለት ሰው እዚያ አካባቢ ሞቷል። አምስት የሚሆኑ ሰዎች ቆስለዋል" ሲሉ አስረድተዋል።

ፖሊስ ግጭቱን በማነሳሳት የተጠረጠሩ ያላቸውን 78 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ኮማንደሩ ጨምረው ተናግረዋል። በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የሚገኘው የሳውላ አካባቢ ባለፈው ጥቅምት ወር በዞን ደረጃ እንዲዋቀር ከተነሳ ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተነሳ ግጭት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን DW ዘግቧል።

የክልሉ ምክር ቤት በቅርቡ ባካሔደው መደበኛ ጉባኤ አካባቢው ቀደም ሲል ከነበረበት የጋሞ ጎፋ ዞን በመውጣት ራሱን ችሎ በዞን ደረጃ እንዲዋቀር ወስኗል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ(ሸዋንግዛው-ሀዋሳ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia