TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና!

በድሬዳዋ ከትናንት በስተያ ምሽት አንስቶ እስከ ትላንት በቀጠለ #ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የሆስፒታል ምንጮች እና የዓይን ምስክሮች ለዶቼቬለ/ለጀርመን ድምፅ ራድዮ/ ተናገሩ። በዚሁ በተለምዶ ደቻቱ እና 5ተኛ ተብለው በሚጠሩ ሰፈሮች ወጣቶች መካከል ተፈጠረ በተባለው ግጭት #በጥይት ተመተው ቀላል እና መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው 3 ሰዎች እንዲሁም የአንዲት ወጣት #አስከሬንም ሆስፒታላቸው መምጣታቸውን የድል ጮራ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አብዱራህማን አቡበከር ለዶቼቬለ ተናግረዋል። የዓይን ምስክሮች ደግሞ በግጭቱ ወቅት የሌላ አንድ ወጣት ህይወት በተባባሪ ጥይት ማለፉን ተናግረዋል። በሰፈሮቹ ዛሬ አንጻራዊ #ሰላም መስፈኑ ተዘግቧል።

🗞ቀን 13/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ከሰሞኑን

(ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት)

- በኢህአዴግ ዘመን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ፤ " የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር " ሆነው ሰሞኑን ተሹመዋል።

በሌላ የሹመት መረጃ ፤ የቀድሞ የ " ብአዴን " ከፍተኛ አመራር ዶ/ር አለምነው መኮንን የኢትዮጵያ ልማት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል። ሹመቱ ተቋሙን ለ10 ወራት በዋና ዳይሬክተርነት የመጡር አቶ ብሩ ወልዴ ከኃላፊነት በመልቀቃቸው ነው።

- ሰሞኑን አሜሪካ ፣ ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ አውስትራሊያ ፣ ዴንማርክ እና ኔዘርላንድስ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እና ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም እና የሰላም ድርድር እንዲጀመር በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።

በመግለጫው ፦

• ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ወታደራዊ ግጭት እንዲቆም ፤ ይህንን ለማድረግ ስምምነት እንዲደረስ፣ 

• የሰብዓዊ እርዳታ እንዲቀርብ

#የኤርትራ_ሠራዊት ከግጭት ተሳትፎው እንዲታቀብ እና ከኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር መለስ ዓለም ፥ " መግለጫው ከዚህ በፊት ከወጡት መግጫዎች የተለየ ነገር የለውም " ብለዋል።

ቃል አቀባዩ ፤  " መንግሥት ሰላም እንዲመጣ ቀደም ሲል የወሰዳቸው የመተማመን ምንፈስ የሚፈጥሩ እርምጃዎች አሉ። " ያሉ ሲሆን " መንግሥት ለሰላም ዝግጁ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ሞኢቦን በቀለ ከትላንት በስቲያ በቡራዩ ከተማ እና አዲስ አበባ አዋሣኝ (ልዩ ቦታው ሳንሱዚ) ቤታቸው አካባቢ ምሽት 1 ሰዓት ገደማ " ማንነታቸው ባልታወቀ " ሰዎች #በጥይት_ተመተው መገደላቸውን ፓርቲው ገልጿል። አቶ ሞኢቦን በቀለ በጥይት ከተመቱ በኃላ ሆስፒታል ቢገቡም ህይወታቸው ሊተርፍ አልቻለም።  ኦነግ ግድያው ፤ " በገለልተኛ አካል " ይጣራሊኝ ሲል ጠይቋል።

- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፤ መተከል ዞን፤ ማንዱራ ወረዳ #በታጣቂዎች_ጥቃት የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ ሂስ ሄጮን ጨምሮ ስድስት (6) ሰዎች ተገድለዋል። ከሟቾች መካከል ሹፌራቸው እና አንድ የመከላከያ ፤ ሶስት የፌዴራል ፖሊስ ይገኙበታል።

- የኢትዮጵያ መንግስት #ለአይርላንድ በፃፈው ደብዳቤ ሀገሪቱ " በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ደባ እየፈፀመች " መሆኑን በመገልፅ ከዚህ አይነት ድርጊቷ እንድትታቀብ አስጠንቅቋል። ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያያዞ አየርላንድ " ህወሓትን በመደገፍ በተመድ ፀጥታ ም/ቤት ውስጥ ያላትን የተለዋጭ መቀመጫ በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲፈጠር ግፊት እያደረገች ነው " ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላት ግንኙነት እንዲሻክር እየተንቀሳቀሰች ነው ሲል ገልጿል። ሀገሪቱ ከዚህ ድርጊቷ እንድትታቀብ አስጠንቅቋል።

NB. አየርላንድ ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ በተመድ ፀጥታ ም/ቤት ውይይት እንዲደረግ በተደጋጋሚ ለም/ቤቱ ጥያቄ ከሚያቀርቡ አገራት መካከል ዋነኛዋ ናት።

#ከሰሞኑን ፦ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የተሰባሰቡ እና በአጭሩ የቀረቡ።

@tikvahethiopia