TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ ኢብራሂም ኡስማን የሶማሊ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ። አዲሱ የሶማሊ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው የመጀመሪያ አመት ጉባኤው ላይ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፋራህን የሶማሊ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል። አቶ ኢብራሂም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አማካኝነት ቃለመሃላ ፈፅመዋል። Photo Credit : SMMA @tikvahethiopia
#SomaliRegion : የሶማሊ ክልል ም/ቤት ሁለተኛ ቀን ውሎውን እያካሄደ ይገኛል።

ትላንት የክልሉ ፕሬዜዳንት ፣ ምክትል ፕሬዜዳንት ፣ አፈጉባኤ እና የምክትል አፈጉባኤ ሹመት በምክር ቤት ፀድቋል።

በመቀጠልም 2 የኦብነግ (ONLF) አባላት ያሉበት 27 የክልሉ ስራ አፅፈፃሚ አካላት ሹመት ፀድቆ ነበር።

በዛሬው የሁለተኛ ቀን ውሎ ምክር ቤቱ በክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ አቅራቢነት የተለያዩ ሹመቶችን አፅድቋል።

* አጠቃላይ በሶማሊ ክልል ምክር ቤት የፀደቁ ሹመቶች ከላይ ተያይዟል።

Credit : Somali Communication & SMMA

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

የሶማሊ ክልል መንግሥት ለ12ተኛ ጊዜ ፣ በጀረር ዞን ብርቆት ወረዳ ያለው ሻለቃ ከድር የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸው ልዩ ኃይል አባላት የሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በተገኙበት አስመርቋል።

ፎቶ፦ SRTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዳዋ ዞን ነዋሪዎች ያሉበት ሁኔታ ፦ በሶማሊ ክልል ዳዋ ዞን (የቦረና አጎራባች) በተከሰተው ድርቅ የሞቱት የቁም እንስሳት 47,215 መድረሳቸውን ከአንድ ሪፖርት መመልከት ችለናል። ሪፖርቱ የተዘጋጀው ከጥቅምት 25 እስከ 29 ቀን 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ በተካሄደ ዳሰሳ ሲሆን ይህም የተመራው በዳዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ፣ በዳዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት፣ ከዞኑ የአደጋ ስጋት አስተዳደር እና…
#SomaliRegion

በሶማሊ ክልል በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች እገዛ እንዲደረግ ተጠየቀ።

የሶማሊ ክልል የሰላም እና አንድነት ምክር ቤት በክልሉ የተከሰተውን ድርቅ አሰመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው ፦

1. የክልሉ ህዝብ በተፈጥሮ ድርቅ አደጋ ምክንያት ከቀያቸዉ የተፈናቀሉ ወንድሞቻቸዉን ባላቸዉ ነገር በማገዝና ከጎናቸዉ በመቆም።

2. የክልሉ ማህበረሰብ ባላቸዉ ነገር በድርቅ የተጎዱና አቅመ ደካማ የሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎችን በመረዳት።

3. ዲያስፖራው ማህበረሰብ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው የተፈጥሮ ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ የበኩላቸዉን ድርሻ እንዲወጡ።

4. ግብረሰናይ ድርጅቶች በድርቅ የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደረገው ድጋፍ የበኩላቸዉን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

#SomaliRegionCommunication

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚካኤል ደንፎርድ ጋር ተወያይተዋል።

አቶ ሙስጠፌ በውይይቱ ፤ በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል።

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመከላከል እና ህይወትን ለማዳን ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገውን የምግብ እርዳታን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተውበታል።

ምንጭ፦ የአቶ ሙስጠፌ የተረጋገጠ የትዊተር አካውንት

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሶማሌ ክልል የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ ተፈናቃዮች ድጋፍ ከሚያደርጉ በርካታ ማኅበረሰቦች መካከል አንዱ የሚገኝበትን ቀብሪበያን ዛሬ ማለዳ መጎብኘታቸውን አሳውቀዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ " በጊዜያዊነት የውኃ አቅራቢ ተሽከርካሪዎችን ፣ የምግብ፣ የእንስሳት መኖ እና እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችን አቅርቦት እናሳድጋለን " ብለዋል።

" ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የጀመርናቸውን የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን " ሲሉም ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅ ከተከሰተባቸው ክልሎች አንዱ የሶማሌ ክልል ሲሆን ድርቅ በተከሰተባቸው የክልሉ ዞኖች አስከፊ ሁኔታ መኖሩ በተደጋጋሚ መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፦

" በሱማሌ ክልል በድርቅ ለተፈቀሉት በርካታ ወገኖቻችን ውሃ በአስቸኳይ ይደርስ ዘንድ ለአንድ ወር በቀን 5 ቦቴ ድጋፍ ጀምረናል።

በቀብሪ በያ ያየኽቸው ሁሉ በተለይም ሴቶች ጥያቄ አንድ ብቻ ነበር 'ውሃ' ፤ ለዘላቂ ጉድጏድ ቁፋሮም ከክልሉ ጋር እንተባበራለን። "

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

ድርቅ ወገኖቻችን ክፉኛ እየጎዳበት ካለው የሀገራችን ክፍል አንዱ የሶማሌ ክልል ነው።

የክልሉ ካቢኔ የድርቁን አደጋ ምላሽ ለመስጠት 500 ሚልየን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲፀደቅ ውሳኔ አሳልፏል።

ተጨማሪ በጀቱ በተለይም ለተለያዩ ምግቦች መግዣ ፣ ለውሃ ፣ ለጤናና ለእንሰሳት መኖ አቅርቦት የሚመደብ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ካቢኔው በተለያዩ ደንቦችና ረቂቅ አዋጆች ላይ ውሳኔ በማሳለፍ ለክልሉ ምክር ቤት መርቷል።

ካቢኔው ያፀደቀው ተጨማሪ በጀት፣ ደንቦችና አዋጆች ቅዳሜ የክልሉ ምክር ቤት በሚያደርገው ጉባኤ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃው የክልሉ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

የሶማሊ ክልል ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ፤ የሶማሊኛ ቋንቋን ያሳድጋል ፤ ይጠብቃል የተባለውን በሶማሊኛ የተዘጋጁ የወራት ስያሜዎች ስራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል።

የክልሉና ሌሎች ባለሞያዎች በሶማለኛ የወር ስያሜዎች ላይ ያካሄዷቸው ጥናቶች ላይ ትላንት ውይይት ተካሂዶ ነበር።

በውይይቱ ላይ ባለሞያዎቹ በሶማሊኛ ቋንቋ በቀን ፤ በወርና በአመት ላይ የተከናወነውን ጥናት የሚያሳይ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል።

የክልሉ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ፤ በሶማሊኛ ቋንቋ የተዘጋጀው የወራት ስያሜዎችን እንዳደነቀና ይህም የሶማለኛ ቋንቋን ለማሳደግና ለመጠበቅ ጠቀሜታ እንዳለው መግለፁ ተመላክቷል።

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከታች የተዘረዘሩትን የሶማሊኛ ቋንቋ የወር ስያሜዎች ከትላንት ጀምሮ የክልሉ መንግስት ስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል።

1. ኮድሂን / መስከረም / September
2. ዲሪር / ጥቀምት / October
3. ጉድባ / ህዳር / November
4. ሆሬይ / ታህሳስ / December
5. ደርበለይ / ጥር / January
6. አሪር / የካቲት / February
7. ኡር / መጋቢት / March
8. ዱጋቶ / ሚያዚያ / April
9. ሚአድ / ግንቦት / May
10. አጋሊ / ሰኔ / June
11. አፍጋል / ሀምሌ / July
12. ነፍ / ነሀሴ / August

#SRTVAmharic

@tikvahethiopia
#ONLF #SOMALIREGION

ከሰሞኑን ተቃዋሚው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ' የሶማሌ ክልል የዜጎች መብት የሚጣስበት እየሆነ ነው " ሲል ከሷል።

ፓርቲው ክልሉ ሶማሌዎች ማንነታቸውን እንዲክዱ የሚገደዱበት እየሆነ ነው ብሏል።

የክልሉን ስያሜና ሰንደቀላማ የመቀየር እቅድ እንዳለ ከአሉባልታ ከፍ ያለ መረጃ አለን ሲሉም፣ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አብዲራህማን መሀዲ ተናግረዋል።

ባለፉት 6 አመታት በክልሉ የጎሳ ግጭቶች ጨምረዋል ሲሉም ወቀሳ አቅርበዋል።

የክልሉ ርዕሰመስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በበኩላቸው፣ የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች " እኛ ሶማሌዎች እንጂ ሶማሊያውያን አይደለንም " ማለታቸው ማንነትን እንደመካድ ሊወሰድባቸው አይገባም ብለዋል።

በቀድሞው አስተዳደር ህግን ባልተከተለ መንገድ ተቀይሮ የነበረውን ስያሜና ሰንደቅ አላማ በመተው በህገመንግስቱ የተቀመጠውን ስያሜ መጠቀም የጀመረው የእርሳቸው አስተዳደር መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ሙስጠፋ የኦብነግ ሊቀመንበር የሚመሩት ቡድን ይህንን መግለጫ ያወጣው በክልሉ ችግር ስላለ ሳይሆን " ሰሞኑን በአፍሪካ ቀንድ እየተስተዋለ ያለውን ጂኦፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ ጥቅም በመፈለግ ነው " ሲሉ ተችተዋል። #ቪኦኤ

@tikvahethiopia