TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአርጆ ዲዴሳ ምን ሆነ ?

የገንዘብ ሚኒስቴር ለግል ባለሀብቶች በጨረታ ለመሸጥ የፍላጎት መግለጫ ካወጣባቸው 8 የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ አንዱ በሆነው አርጆ ዲዴሳ ባለፈው ማክሰኞ በታጣቂዎች ጥቃት ተፈፅሞበት ነበር።

ታጣቂዎቹ የፋብሪካውን ተሽከርካሪዎች እንዳቃጠሉና ጥቃቱን ከፈጸሙ በኋላ ከአካባቢው መውጣታቸውን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታውቋል፡፡

የግሩፑ የሕዝብ ግንኙነትና ተሳትፎ ክፍል ዋና ኃላፊ አቶ ረታ ዘለቀ ለሪፖርተር የተናገሩት ፦

" በተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰውን ትክክለኛ ጉዳት ለማጣራት ጥናት እየተደረገ ነው።

እስካሁን ፋብሪካው ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የደረሰ መረጃ የለም።

አንድ ሠራተኛ ላይ ከደረሰ ድብደባ በስተቀር በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

በግቢው ውስጥ የሸንኮራ ማሳ ማሽነሪዎች፣ ትራክተሮችና የፋብሪካው ተሽከርካሪዎች አሉ በየትኞቹ ላይ ምን ያህል ጉዳት ደርሷል የሚለው እየተጣራ ነው።

በፋብሪካው ላይ የደረሰው ጥቃት በሰሜን ኢትዮጵያ በድጋሚ ካገረሸው ጦርነት ጋር የሚያያዝ ነው ፤ ታጣቂዎቹ በጦርነቱ ምክንያት አካባቢው ላይ የተፈጠረውን #ክፍተት ተጠቅመዋል፡፡

ኦነግ ሸኔ ተብሎ በዚያ ደረጃ የሚጠቀስ አይደለም ግርግር ተጠቅመው ታጣቂዎች ሊገቡ ይችላሉ ወለጋ አካባቢ ስለሆነ ግን እንደዚያ [ኦነግ ሸኔ] ተብሎ ነው የሚታወቀው።

በክረምት ወራት ላይ ሁሉም የስኳር ፋብሪካዎች የስኳር ምርት አቁመው ሙሉ ማሽነሪ ጥገና ላይ ነው የሚሰማሩት ጥቃቱ ሲደርስ የፋብሪካው ሠራተኞች በማሽነሪ ጥገና ላይ ነበሩ።

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ለምን ያህል ጊዜ በፋብሪካው ቅጥር ጊቢ ውስጥ እንደቆዩ አልታወቀም። ነገር ግን የፋብሪካው ሠራተኞች ወደ ፋብሪካው ተመልሰው የጥገና ሥራውን እያከናወኑ ነው። "

Via ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

ወላጆች ስለ ት/ቤት ክፍያ ጭማሪ ምን አሉ ?

----

የካ አባዶ አካባቢ በሚገኝ አንድ ትም/ ቤት ልጃቸውን የሚያስትምሩ ወላጅ የልጃቸው ወርሃዊ ክፍያ 1450 ብር እንደነበና 65.7 በመቶ በመጨመር 2500 ብር እንደተደረገ ገልጸዋል። " ወላጆች እንዲጨምርብን አንፈልግም ነበር ግዴታ ከሆነም ከ30 በመቶ በላይ እንዳይጨምሩ ተከራክረን ነበር። " ያሉት እኚሁ ወላጅ " ት/ቤቱ ግን 80 በመቶ እንጨምራለን ብለው ወላጅ ባይስማማም 65.7 በመቶ ወስነዋል " ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።

----

" መንግስት ካለ ለምን መጨመር የሚቻለውን ከፍተኛ ተመን አይወስንም ? " ሲሉ የጠየቁ አንድ የተማሪ ወላጅ " እመኑኝ በዚህ ሁኔታ ብዙዎች ት/ት ሊያቆሙ ይችላሉ " ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

----

በአንድ የግል ት/ቤት ውስጥ ልጃቸውን የሚያስተምሩ ወላጅ ት/ቤቱ መንግስት ምንም ሊያስገድደው እንደማይችል እና ነፃ ገበያ እንደሆነ ተናግሮ ምንም ለውጥ እንደማናመጣ ነገረን ያሉ ሲሆን "  መንግሥት ስምምነት ሳይደረግ ዋጋ መጨመር አይቻልም ማለቱ ተስፋ ሰጥቶናል " ብለዋል ፤ እሳቸው ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት 78% መጨመሩንና በተርም / በሁለት ወር ከአስራ አምስት ቀን 7600 እንከፍል የነበረውን 13324 ነው ያደረጉብን ሲሉ ገልጸዋል።

----

አንድ ወላጅ ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ት/ቤት የ65 በመቶ ጭማሪ ሊያደርግ መሆኑን ገልጸው " በዚህ ኑሮ ውድነት ይህን ማድረግ ግፍ ነው ፤ የእኛ የወላጆች ገቢ ባላደገበት ይህ እንዴት ይድረጋል ፤ ለእኛስ አይታሰብም ወይ ? ሲሉ መልዕክታቸውን ልከዋል።

----

በኮ/ቀ በሚገኝ የአንድ የግል ትምህርት ቤት የወለጅ ኮሚቴ ነኝ ያሉ አንድ የቲክቫህ አባል " እንደ ኮሚቴ ተስማምተን የነበረው 200 እስከ 300 ጭማሪ ነበር ፤ ለምሳሌ በዚህ የት/ዘመን 1300 + 300 = 1600 ፤ 2016 ነበር የተስማማነው አሁን ግን 600 ጭማሪ አድርገዋል " ሲሉ ገልጸዋል። " ይህ ለምን እንደሆና ምክንያቱን በግልፅ አላወቅንም " ያሉት እኚሁ የወላጅ ኮሚቴ " ለሚቀጥለው ዓመት 1900 ተብሎ በደብዳቤ አሰውቀውናል " ሲሉ አክለዋል። " ልጆቻችንን ከመስወጣተችን በፊት ትምህርት ቢሮ ክትትል ያድርግ !! " ሲሉ አደራ ብለዋል።

----

" መንግስት ውይይት ሳይደረግ መጨመር አይቻልም ብሏል ፤ ውይይት ሲባልስ #ስንት_ሠው_ተገኝቶ ነው ውሣኔ ማሣለፍ የሚችለው ? " ሲሉ የጠየቁ አንድ ወላጅ " ይህ በራሡ #ክፍተት ያለው አገላለፅ ነው፤ እንዳሻችሁ እንደማለት ነውና መንግስት የኑሮ ጫና የሚፈታተንን ሳያንስ ሌላ ጫና ለመሸከም የሚችል ጫንቃ የለንምና ፤ የፈጠራትን ክፍተት መንግሥት ራሡ ይዝጋት እንላለን " ብለዋል። "

----

በአንድ የግል ት/ቤት ልጃቸውን የሚያስተምሩ ወላጅ ፤ ት/ቤቱ በቀጣይ አመት ከ1300 ባንዴ 2700 ጭማሪ ማድረጉን እና ያልፈለገ መልቀቅ ይችላል እንዳሏቸው ገልጸዋል። " በዛላይ ቀጣይ አመት በተርም ነው ምከፍሉት አሉን " የሚሉት ወላጅ " ሁለት ልጆቼን ለማስተማር 2600 ከፍዬም አንገዳግዶኝ ነበር የባሰው መጣና ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ  " ብለዋል።

----

" እኔ ልጄን የማስተምርበት ት/ት ቤት ወደ 120% ነው የጨመረው " ያሉ አንድ ወላጅ " ከአንድም ሁለት ጊዜ ከት/ት ቤቱ አሰተዳደር ጋር ብንሰበስብም መስማማት ላይ ግን መድረስ አልቻልንም። " ብለዋል። " እንደውም ት/ት ቤቱ መጀመሪያ 22ዐ% ነበር ያቀረበው ከብዙ ክርክር በኋላ ነው ወደ 120% የወረደው ሆኖም ግን ከዚህ በታች አሻፈረኝ ብሏል። ብዙ ወላጅም በጣም ተማሯል። " ሲሉ ገልጸዋል።

----

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነኝ ያሉ አንድ ወላጅ ፤ ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት 40 % ጭማሪ መደረጉን ገልጸው በዚህ ኑሮ ውድነት ፤ በዛ ላይ ሁለት / 2 / እና ከዛ በላይ ልጆች ያሏቸው ምን ይሆናሉ ? ሲሉ ሁኔታው እጅግ እንዳስጨነቃቸው ገልጸዋል።

----

አንድ ወላጅ ልጆቻቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ከጭማሪ ጋር በተያያዘ ከወላጆች ጋር ስምምነት እንደሌለ ገልጸዋል። ትምህርት ቤቱ ግን " የፈለገ ልጆቹ ያስቀጥል፤  ያልተስማማ ሌላ ት/ቤት ይቀይር " የሚል ምላሽ መስጠቱን አመልክተዋል " መንግስት የሰጠው አቅጣጫ ወላጆች ሳይስማሙ ማለት የሹፈት ውሳኔ ነው ፤ ሌላ ትም/ቤት ፈልጉ ከተባለ ለልጃችን ስንል ሳንስማማ እንቀጥላለን ፤ #መንግስት ነው ይህን #መቆጣጠር ያለበት፤ እውነቴ ነው በዚህ አካሄድ ብዙ ልጆች ከትምህርት ውጪ ይሆናሉ። " ሲሉ ስጋታቸውን አስረድተዋል።

----

የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የሆኑ ወላጅ " ከክፍያ ጭማሪ በተያያዘ እኛ ወላጆች ምንም ባልተስማማንበት ሁኔታ ነዉ እየጨመሩ ያሉት ፤ በአካባቢያችን ከ50% በላይ ነዉ ጭማሪ የተደረገው እና የሚመለከተው አካል ከጊዜዉ ጋር ታሳቢ በማድረግ መፈትሔ እንዲሰጥ ። " ሲሉ ጠይቀዋል።

----

አንድ ወላጅ አምስት (5) ልጆቸውን በሚያስተምሩበት የግል ትምህርት ቤት በአመት አጠቃላይ 434 ሺህ ብር ሲከፍሉ እንደነበር አሁን ግን 100 % ጭማሪ (868,000 ብር) እንደሚደረግ እንደተነገራቸው ገልጸዋል ፤ መንግሥት በግል ት/ቤቶች እየተደረገ ያለውን ነገር እንዲከታተልና መፍትሄ እንዲፈልግ አደራ ብለዋል።

----

በአንድ የግል ትምህርት ቤት ልጃቸውን የሚያስተምሩ ወላጅ ትምህርት ቤቱ የ60,000 ሺህ ብር ጭማሪ ለማድረግ እንደወሰነና ለዩኒፎርም እና ለመሳሰሉት እስከ 30,000 ብር ጭማሪ እንደተደረገ አመልክተው የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይፈልግ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

(ተጨማሪ ወላጆች የላኩይ መልዕክት በዚሁ ፅሁፍ ላይ #edit ተደርጎ ይካተታል)

በአጠቃላይ እጅግ በጣም በርካታ የተማሪ ወላጆች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው መልዕክታቸውን ልከዋል።

የወላጆቹ ሃሳብ ሲጠቃለል ፤ በዚህ የኑሮ ጫና ወቅት እጅግ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ መንቀሳቀስ በምንም መልኩ ተቀባይነት እንደሌለውና ት/ቤቶችም ይህንን ተገንዝበው ማስተካከያ ማድረግ እንዳለብቸው የሚያሳስብ ነው።

ከምንም በላይ ደግሞ ፤ #መንግስት በሁሉም የግል ት/ቤቶች ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ዜጎችን ወደ ምሬት ውስጥ የሚከቱ ተግባራትን ማስቆም እንዳለበት የሚያገነዝብ ነው።

@tikvahethiopia
“ ልጅ ያለው የልጅን ነገር ያውቀዋል። ቶሎ ካልታከመች ክፍተቱ እየጨመረ ነገሮች ሁሉ ይከብዳሉ ” - የ9 ዓመቷ ታዳጊ እናት

ልጃቸው ለየልብ ህመም የታመመችባቸው እናት ደጋግ ኢትዮጵያውያን እንዲያግዟቸው ተማጽኑ።

ወ/ሮ መባ አላምረው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ሊያ የ3ኛ ክፍል ተማሪ 2ኛ ልጄ ናት። #ልቧ 15 ሚሊ ሜትር #ክፍተት አለው ” ብለዋል።

የልብ ስፔሻሊቲ ዶክተርም፣ “ ‘ችግሩ ክፍተት መፍጠሩ ብቻ ሳይሆን የቀኝ ልቧ አቅጣጫውን በመሳት ወደ ሳምባዋ ክፍል ደም እየረጨ ነው። ሳምባዋም ወደ ማበስበስ ደረጃ እየደረሰ ነው። በአስቸኳይ ቀዶ ጥገና መደረግ አለበት’ ” እንዳሏቸው አስረድተዋል።

“ በፊት ላይ ‘#የሳንባ #ምች ነው’ እየተባለ ነበር። አሁን ‘የልብ ክፍተት ነው’ ተባለች። #እጇንም #እግሯንም #መሸምቀቅ ጀመራት። ትምህርቷን አቋርጣ ቤት ከተቀመጠች 1 ወር ሆናት ” ብለዋል።

“ ‘ሳንባዋ ለንቅለ ተከላ የሚደርስ ነው’ አሉኝ ” ያሉት እኝሁ እናት፣ ለሰርጀሪው ብቻ 595 ሺሕ ብር፣ የሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ 700 ሺሕ ብር ለቀዶ ጥገና እንደተጠየቁ አስረድተዋል።

የታዳጊዋ እናት፣ “ ልጅ ያለው የልጅን ነገር ያውቀዋል። ቶሎ ካልታከመች ክፍተቱ እየጨመረ ነገሮች ሁሉ ይከብዳሉ። ሁሉም ያቅሙን በገንዘብም በጸሎትም እንዲተባበረኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲረዳኝ እለምናለሁ ” ሲሉ ተማጽነዋል። 

እናት መባ አላምረውን በስልክ ለማግኘት በ +251939665539 መደወል ይቻላል። የባንክ የሒሳብ ቁጥራቸው 1000470071536 ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia