TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ህገ ወጥ የውጭ #ምንዛሬ ግብይት ሲካሄድባቸው የነበሩ በርካታ የንግድ ቤቶች መታሸጋቸው ተሰማ።

የንግድ ቤቶቹ የታሸጉት በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በሚመራ ግብረ ሀይል ሲሆን፥ ፖሊስ ከትናንት ጀምሮ ባካሄደው ድንገተኛ ክትትል እና ፍተሻ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።

የንግድ ቤቶቹ የታሸጉበት ምክንያት፦

📌በህጋዊ የንግድ ፍቃድ ህገ ወጥ ተግባር በመፈፀማቸው ነው። ተግባሩም ህገ ወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሬ በህገ ወጥ መንገድ የውጭ ሀገራት ገንዘብን #መግዛት እና #መሸጥ ድርጊት ነው።

በዚም በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለከተማ ጋንዲ ሆስፒታል፣ ኢትዮጵያ ሆቴል እና ቴሌ ባር አካባቢ የሚገኙ የንግድ ቤቶች ታሽገዋል።

እንዲሁም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አሜሪካ ጊቢ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ሁለት አካባቢዎች ላይ የሚገኙ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ናቸው በተደረገው ፍተሻ ተለይተው ታሽገዋል።

📌በፍተሻው ወቅት በርካታ የውጭ ሀገራት እና የሀገር ውስጥ ገንዘቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

©fbc ፎቶ(ካፒታል)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

#የህዝብ_ተወካዮች_ምክር_ቤት መስሪያ ቤቶች የጤና ተቋማትና የወጣቶች መዝናኛ በሚገኙባቸው አከባቢዎች 100 ሜትር ርቀት ውስጥ #ማጨስ የሚከለክልን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጸደቀ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከአልኮል መጠጦች ጋር በተያየዘም ከ21 አመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች አልኮል #መሸጥ የሚከለክለውንም ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምጽ #አጽድቋል፡፡

ማንኛውንም #የአልኮል_ምርት በብሮድካስት ሚድያ #ማስተዋወቅ የሚከለክለውን ረቂቅ አዋጅ ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia