TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኮሬዞን

" ሪፈር ብትባልም አምቡላንስ በማጣቷ ምክንያት #መንታ ልጆቿን አጥታለች  " - ነዋሪዎች

" እኛ አካባቢ ትንንሽ ነገሮችን አጋኖ እና ሌላ አቀላቅሎ የማቅረብ መሠረታዊ ችግሮች አሉ " - አቶ ታደለ አሸናፊ

በአዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የመዋቅር ጥያቄ በሚነሳባቸው ቀበሌዎች የታሰሩ ባለስልጣናት ጭምር ከእስር አለመፈታታቸው እንዲሁም የህክምና አገልግሎት ክፍተት በተለይ ለእናቶች ፈተና መደቀኑ የአካባቢውን ነዋሪዎችን አማሯል።

አንድ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪ ፦
- የዞኑ አመራሮች ለህብረተሰቡ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን አምቡላንስ ከክላስተሩ
በመቀማታቸው የወላድ እናቶች ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል።

- አምቡላንሱን ከክላስተር ወደ ዞኑ ከተማ በመውሰድ ለአመራሮች አግልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

- ይህ አምቡላንስ ከመወሰዱ ጋር ተያይዞ በቀን 07/05/2016 ዓ/ም አንዲት የአልፈጮ ቀበሌ ነዋሪ የሆነች እናት በወሊድ ምክንያት ወደ አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ሪፈር ብትባልም አምቡላንስ በማጣቷ ምክንያት መንታ ልጆቿን አጥታለች።

- ይህ ብቻ አይደለም፣ በአካባቢው የህሙማን ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም በቂ የህክምና አገልግሎት ማግኘት አልተቻለም።

የተነሳውን ቅሬታ በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የጤናውን ዘርፍ ጭምር እየተቆጣጠሩ ነው የተባሉት የኮሬ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊና የማኀበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ታደለ አሸናፊ ፦

* በወረዳው የመዋቅር ይገባኛል ጥያቄ ይነሳል፤ ልክ ነው።

* መኪናው ተበላሽቷል ለጊዜው።

* ጋራዥ እንዲገባ ሁሉ ደብዳቤ ተፅፎ ያንን ፕሮሰስ እጨረሰ ነው ያለው። አመራሩ ተነጋግሮ ‘ይሄ መኪና በፍጥነት ጋራዥ ገብቶ መውጣት አለበት’ ተብሎ አቅጣጫ ከተሰጠ በኋላ ሌላ አምቡላንስ እዛው ማዕከል አለ።

* ሌላ እዛው ሁለተኛ አምቡላንስ አለ፤ ያ አምቡላንስ ደግሞ ለአገልግሎት ሂዶ እናቶችንም ሌሎች የታመሙ ሰዎችንም አገልግሎት እየሰጠ ነው።

* የሚባለው ነገር በተባለው ልክ አይደለም።

" ሪፈር ብትባልም አምቡላንስ በማጣቷ ምክንያት መንታ ልጆቿን አጥታለች " የተባሉትን እናት ጉዳይ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፦ " ሰው ሞቷል መባሉ ምናልባት በጤና ችግር ሰው ሊሞት ይችላል። እኛ አካባቢ ላይ ትንንሽ ነገሮችን #አጋኖ ሌላ አቀላቅሎ የማቅረብ መሠረታዊ ችግሮች አሉ። " ሲሉ መልሰዋል።

ሌላው እዛው ሁለተኛ አምቡላንስ አለ የሚለውን የአቶ ታደለ ምላሽ በተመለከተ አንድ የአልፈጮ ቀበሌ ነዋሪ ለቲክቫህ በሰጠው ቃል ፤ " ‘አምቡላንሱን ጋራዥ ነው የወሰድነው’ ስለተባለው፣ አምቡላንሱ ምንም አይነት እንከን አልነበረውም። ‘ምትክ ልከናል’ የሚለውም ውሸት ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም  ፤ " ሚዲያን እንደጠላት ነው የሚፈሩት። ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ጠይቀናቸዋል። ‘ይህን ወደ ሚዲያ ላይ ከመውጣቱ በፊት የምትልኩልን ከሆነ አምቡላንሷን ላኩልን’ ብለን ከአንዴም አራቴ ጠይቀናል። ‘የምንፈልግ ከሆነ እንሰጣለን፣ የማንፈልግ ከሆነ እንደምትሆኑ ሆኑ’ ብለው ነው ምላሽ ሰጥተው የነበረው " ብለዋል።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia