TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ አስመልክቶ ጥር 9/2016 ዓ.ም ያስተላለፈው ውሳኔ ለትግራይ ተፈታኞች አይመለከትም " - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
የትምህርት ሚኒስቴር ከሰሞኑን ባስተላለፈው ውሳኔና ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች በላከው ደብዳቤ ዘንድሮ የሚሰጡ ፈተናዎችን ማሳወቁ ይታወሳል።
በዚህም ፦
- የተፈጥሮ ሣይንስ ተማሪዎች እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት እንደሚፈተኑ ገልጿል።
- የማኅበራዊ ሣይንስ ተማሪዎች ደግሞ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት እንደሚፈተኑ ገልጿል።
የፈተናው አወጣጥም ፤ ከኢኮኖሚክስ ትምህርት ውጪ ሁሉን የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ፈተናው ይዘጋጃል።
የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ከ12ኛ ክፍል ብቻ ይዘጋጃል ማለቱ ይታወሳል።
ዛሬ ጥር 15/2016 የትግራይ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ ፤ " ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ በቅርቡ ያሳተላለፈው ውሳኔ ለትግራይ ተፈታኞች አይመለከትም "ብለዋል።
ሃላፊው አያይዘው " መምህራንና ተማሪዎች ፈተናው በነባሩ ሰርዓተ ትምህርትና መፃሕፍት የሚዘጋጅ መሆኑን እንድታውቁ " ሲሉ ገልጸዋል።
በፈተናው የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችንም ይፋ አድርገዋል።
የተፈጥሮ ሳይንስ ፦
➡ እንግሊዝኛ፣
➡ ሒሳብ፣
➡ ፊዚክስ፣
➡ ኬሚስትሪ፣
➡ ባዮሎጂ
➡ ስነዜጋና ስነምግባር እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት፤
የማኅበራዊ ሣይንስ፦
➡ እንግሊዝኛ፣
➡ ሒሳብ፣
➡ ታሪክ፣
➡ ጂኦግራፊ፣
➡ ስነዜጋና ስነ-ምግባር እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት መሆናቸውን አስረድተዋል።
" የፈተናው ጥያቄም ከነባሩ መፅሐፍ እንደሚዘጋጅ ለማሳወቅ እንወዳለን " ማለታቸው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
#TikvahEthFamilyMekelle
@tikvahethiopia