TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የግብፁ መሪ ምን አሉ ? የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር የሁለቶሽ ምክክር ካደረጉ በኃላ በጋራ ሆነው መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህም ወቅት የግብፁ መሪ ፤ " የአረብ ሊግ ቻርተር በሉዓላዊነታቸው እና በግዛታቸው ላይ ጥቃት የሚደርስባቸውን የአረብ ሀገራት እንድንከላከል ያስገድደናል " ሲሉ ተደምጠዋል። " ግብፅ በሶማሊያ ደህንነት ላይ ምንም አይነት ስጋት እንዲፈጠር…
ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ስለ ግብፅ ምን አለች ?

" በስምምነቱ ዙሪያ የሚነሱ ማንኛውንም የውጭ #ጣልቃገብነቶችን እንቃወማለን " - ሶማሌላንድ

ዛሬ የራስ ገዟ ሶማሌላንድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል መግለጫ አውጣለች። በዚህ መግለጫም ስለ ለሰሞነኛው የግብፅ ሁኔታ ምላሽ ሰጥታለች።

ምን አለች ?

ሶማሌላንድ ፤ ከግብፅ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት ከፍ አድርጋ እንደምትመለከት ገልጻ በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ላይ ያላትን ስጋትም እውቅና እንደምትሰጥ ገልጻለች።

" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተከሰቱ ክስተቶች አንፃር ቀጠናዊ ጉዳዮችን በውይይት እና በትብብር ለመፍታት ያለኝን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጣለሁ " ብላለች።

ይሁን እንጂ በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እና በ #ኢትዮጵያ 🇪🇹 መካከል ከተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) በኋላ የሚነሱ ማንኛውንም አይነት የውጭ #ጣልቃገብነቶችን እንድምትቃወም በድጋሚ አረጋግጣለች።

በመግለጫዋ ፤ " የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር በተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች አከብራለሁ " ስትል ገልጻለች።

" ሁሉም ፍላጎት ያላቸው አካላት ቀጠናዊ መረጋጋትን እና ገንቢ አጋርነትን በማስፈን ላይ እንዲያተኩሩ አበረታታለሁ " ያለችው ሶማሌለንድ ፤ " በዚህ መንፈስም #ግብፅ በቅርብ ጎረቤቶቿ እንደ ፦
* #ሱዳን
* #ሊቢያ
* #ጋዛ ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ አቅጣጫዋን እንድትቀይር እናበረታታታለን " ብላለች።

" እነዚህ አካባቢዎች (ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ጋዛ) በአሁኑ ጊዜ ጉልህ ከሆኑ ተግዳሮቶች ጋር #እየታገሉ ነው ፤ እናም የግብፅ ገንቢ ተሳትፎ ለዘላቂ ሰላም እና ደህንነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለን እናምናለን " ስትል ገልጻለች።

የሶማሌለንድ መንግሥት በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ልማትን ለማስፈን ከሁሉም ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን እና ትብብርን ያደርጋል ስትል አሳውቃለች።

" የጋራ ጂኦፖለቲካዊ አካባቢያችንን ሁኔታ ለማሻሻል ከግብፅ እና ከሌሎች ተባባሪዎች ጋር #በመከባበር እና #በጋራ_ጥቅም ላይ የተመሰረተ ገንቢ ግንኙነትን ለመፍጠር እንሰራለን " ስትል ገልጻለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በደበሶ ከተማ በመኪና አደጋ የሞቱ ምእመናን ዛሬ ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።

በምዕራብ ሐረርጌ ደበሶ ከተማ ትላንት ጥር 12/05/2016 ዓ/ም የቃና ዘገሊላ ክብረ በዓል ዕለት ታቦታትን አጅበው በመጓዝ ላይ የነበሩ ምእመናን ላይ ከድሬደዋ የሚመጣ ከባድ የጭነት መኪና ባደረሰው አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ሰብከት ማሳወቁ ይታወሳል።

ሕይወታቸው ያለፈው ምእመናን ዛሬ ልባቸው በሀዘን የተሰበረ እጅግ በርካታ ምእመናን በተገኙበት ከቀኑ በ7:45 ላይ ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።

ሀገረ ስብከቱ ፤ " ከተቀበሩት መካከል ሦስቱ ጨቅላ ህጻናት ሲሆኑ አንዱ ሕይወቱ ያለፈው ግለሰብ የቀበሌው ሚኒሻ ሃይማኖቱ #ሙስሊም ስለሆነ በወገኖቻችን በሙስሊሞች የቀብር ስፍራ ተቀብሯል። " ሲል አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ሰብከት ማግኘቱን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
#አክሱምኤርፖርት

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የአክሱም ሃፀይ ዮሃንስ አውሮፕላን ማረፍያ ለማደስ በጨረታ ላሸነፈው የኮንስትራክሽን ድርጅት ይፋዊ የርክክብ ስነ-ሰርዓት አላካሄደም ተብሏል።

ይህ ሁኔታ ደግሞ የእድሳት ሰራው በፍጥነት በሙሉ አቅም እንዳይሰራና እንዲዘገይ ምክንያት እየሆነ ነው በሚል ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፕረዚደንት ለአንድ ጊዜ ፤ ከ7 ዓመታት በላይ ድግሞ የትግራይ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕረዚደንት በመሆን አገልግለዋል።

መምህሩ ከሽረ ከተማ መልስ ወደ ሃፀይ ዮሃንስ አውሮፕላን ማረፍያ አክሱም ጎራ ብለው ባዩት ነገር ባለመደሰታቸው የሚከተለው አስተያየት በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ አጋርተዋል።

" በአካል ሄጀ እንዳረጋገጥኩት የአክሱም ሃፀይ ዮሃንስ አውሮፕላን ማረፍያ የመሬት (site) ርክክብ አስከ አሁን አልተተገበረም።

ርክክቡ የሚያከናውኑው የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትን ኮንሰልታንቱ እስከ አሁነን ቦታው ላይ አልተገኙም። ርክክቡ ስላልተፈፀመ ደግሞ የእድሳት ስራው በተሟላ መልኩ አልተጀመረም።

እርግጥ ነው እድሳቱ ለማካሄድ ጨረታው ያሸነፈው የኮንስትራክሽን ድርጅት ቦታው የማጥራት የመሰለ ቀላል ስራ እየሰራ ነው። ይፋዊ የርክክብ ስነ-ስርዓት ሳይካሄድ ግን ስራው አይጀመርም። እና አስረካቢው አካል ለምን ዘገየ ? " ብለዋል። 

የመምህሩ አስተያየት ደግፈው አስተያየት የሰጡ ሰዎች ደግሞ ፤ " እድሳቱ በይፋ መጀመሩ በሚድያ መስማታቸው እንዳስደሰታቸው አስታውሰው ፤ ዜና ከተነገረ አንድ ወር አስቆጥሮ ስራው በጊዜው አለመጀመሩ አሳዝኖናል " ብለዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ አክለው የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትና ኮንሰልታንቱ ለምን ርክክቡ እንዳልፈፀሙ እንዲጠየቁላቸው ጥያቄ አቅርበዋል።

ዘግይቶ ከምንጮች በተገኘ መረጃ ታህሳስ 2016 ዓ.ም አጋማሽ እድሳቱ እንደሚጀመር በሚድያዎች የተነገረለት አውሮፕላን ማረፍያው ፤ ጥር 14/2016 ዓ.ም የመሬት (site) ርክክብ ተፈፅሞ በሙሉ እቅም ወደ ስራ ይገባል መባሉ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
                                       
@tikvahethiopia            
#CPJ

ኤርትራ 16 #ጋዜጠኞችን_በማሠር ከአፍሪካ ቀዳሚውን ሥፍራ እንደምትይዝ በጋዜጠኞች መብት ላይ አተኩሮ የሚሠራው ሲፒጄ ያለፈውን የፈረንጆቹ 2023 ዓ/ም በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።

16 ጋዜጠኞችን አሥራ የያዘችው ኤርትራ፣ በዓለም 7ኛ ደረጃን እንደምትይዝም ሲፒጄ ገልጿል።

አንዳንዶቹ ጋዜጠኞች በዓለም ለረጅም ግዜ የታሠሩ እንደሆነም ሪፖርቱ አመልክቷል።

በሁሉም ጋዜጠኞች ላይ ክስ ተከፍቶ እንደማያውቅም ሪፖርቱ ጠቁሟል።

እስካለፈው ወር ድረስ በአፍሪካ የታሠሩት ጋዜጠኞች ቁጥር 47 እንደነበር ያመለከተው ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ 8 ጋዜጠኞችን በማሠር፣ ካሜሩን ደግሞ 6 በማሠር የሁለተኛና እና ሶስተኛ ረድፍ ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

" በኢትዮጵያ በእሥር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች ቁጥር፣ በአገሪቱ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን የሚገኙበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ያስያል ሲል " ሲፒጄ በሪፖርቱ አመልክቷል።

ባለፈው ዓመት በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረውን ጦርነት ያስቆመ የሠላም ስምምነት ቢፈረምም፣ በአማራ ክልል በአካባቢው በሚገኙ ኃይሎች እና በፌዴራሉ ኃይሎች መካከል የሚካሄደው ግጭት አሁንም እንደቀጠለ ነው ያለው ሲፒጄ፣ ስምንቱም ጋዜጠኞች የታሠሩት ግጭቱን በተመለከተ ዘገባ ካወጡ በኋላ መሆኑን አስታውቋል።

ባለፈው ዓመት በመላው ዓለም ላይ የታሠሩ ጋዜጠኞች ቁጥር እስከአሁን ከታዩት ከፍተኛ ሆኑ ከተመዘገበው ዓመት ጋር እንደሚቀራረብ ያመለከተው ሲፒጄ፣ የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት ባለፈው ጥቅምት መጀመሩን ተከትሎ፣ እስራኤል ጋዜጠኞችን በብዛት ካሰሩ አገራት ጎራ መቀላቀሏን አስታውቋል።

ቻይና 44 ጋዜጠኞችን በማሠር ቀዳሚውን ሥፍራ ስትይዝ፣
ሚያንማር 43 በማሠር ሁለተኛ
➡️ ቤላሩስ 28 ጋዜጠኞችን በማሠር ሶስተኛ ሥፍራን ይዘዋል።

#VOA #CPJ

@tikvahethiopia
" ለገንዘብ ተብሎ በግብረሰዶማውያን እና በስደተኞች ጥገኝነት ጥየቃ (asylum) ጉዳይ ሀገሪቱ ያላት ፖሊሲ አይቀየርም " - ሀንጋሪ

በመጪው ሰኔ የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ይደረጋል ተብሎ እቅድ ተይዟል።

ከምርጫው ጋር ተያይዞ ስለ ግብረሰዶማውያን እና ስለስደተኞች እንዲሁም ስለሌሎች ጉዳዮች የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ከአንድ የሀገር ውስጥ ሬድዮ ጣቢያ ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ ብዙ የአውሮፓ ፖለቲከኞች ይህንን ወቅት እንደምንም ብለው መትረፍ ይፈልጋሉ ብለዋል።

" ምርጫ በሌለበት ጊዜ ማስመሰል ትችላላችሁ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " ምርጫ ሲደረግ ግን ከህዝቡ ጋር መነጋገር አለባችሁ። ነገር ግን ሰዎች ብራስልስ ውስጥ የሚጠቀሙትን የሌቦች ቋንቋ አይረዱም። የህዝብን ቋንቋ መናገር መጀመር አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።

ንግግራቸውን ቀጠል አድርገው፤ " የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን ፤ የብራሰልስ አካላት በሃንጋሪውያን ላይ ያላቸውን ነገር ማለትም ስደተኞችን ወደ ሀገር ውስጥ እንደማናስገባ እና የግብረሰዶማውያን አክቲቪስቶችን ወደ ትምህርት ተቋማት እንዲገቡ እንደማንፈቅድ በመጨረሻ አምነዋል " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " የግብረሰዶማውያን ፕሮፓጋንዲስቶችን ወደ ትምህርት ቤቶቻችን እንድናስገባ እንዲሁም ስደተኞችን ወደ ሀገራችን እንድናስገባ የሚያደርግ በዓለም ላይ ምንም አይነር ገንዘብ የለም " ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።

ለገንዘብ ተብሎ በግብረሰዶማውያን እና በስደተኞች ጥገኝነት ጥየቃ (asylum) ጉዳይ ሀገሪቱ ያላት ፖሊሲ እንደማይቀየር የሀገሪቱ መንግሥት አሳውቋል።

የአውሮፓ ህብረት ከግብረሰዶማውያን እና ከስደተኞች መብት እንዲሁም #ከአካዳሚክ_ነፃነት ጋር በተያያዘ ብዙ ለሀንጋሪ ሊሰጥ የሚገባውን ብዙ ቢሊዮን ዩሮ (20 Billion EUR) ይዞባታል።

እ.ኤ.አ. ከ2010 ጀምሮ በስልጣን ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኦርባን ግብረሰዶማዊነትን እና የፆታ ለውጥን በትምህርት ቤቶች ውስጥ #ሊያስተዋውቁ ይችላሉ የሚባሉ ነገሮችን የሚከለክል ህግ በ2021 አጽድቀዋል።

ህጉ ከገንዘብ ቅጣት እስከ እስር ቤት መወርወር ያደርሳል።

ይህ ህግ የፀደቀው ህፃናትን ከ " ከግብረሰዶማውያን ፕሮፓጋንዳ " መጠበቅ በማስፈለጉ ሲሆን በዚህ ህግ ምክንያት ከአውሮፓ ህብረት ጋር አለመግባባት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል። የአውሮፓ ህብረቱም ከዚህና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ 20 ቢሊዮን ዩሮ ገንዘብ ይዞባታል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

አሁን ባሉበት ሆነው የአፖሎ አካውንት ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቁጥር ብቻ በቂ ሆኖዋል። የባንክ አካውንት ለመክፈት ይህን ያህል ቀሏል።

አሁኑኑ መተግበሪያውን በማውረድ የ9% ወለድ፣ አነስተኛ ብድርና ሌሎች አገልግሎቶችን ያግኙ። 

https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo 
 
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#GeneneMekuria

አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ የሀገራችንን ስፖርታዊ ክንውኖችን በማቅረብ እንዲሁም ከስፖርታዊ ክንዋኔዎች በተጨማሪ በጠቅላላ እውቀቱና መረጃ አያያዙ በርካታ እውቀቶችን ያስጨበጠ ጋዜጠኛ ነበር።

በተለያዩ የፅሁፍ ስራዎች ፣ የራዲዮና ቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ላይ ታሪኮችንና ወጎችን በማቅረብም በሚዲያው ላይ ከአርባ አመታት በላይ አገልግሏል።

ለአብነት በቀድሞ ዛሚ ኤፍ ኤም፣ በኤፍ ኤም አዲስ ፣ በብስራት ኤፍ ኤም ፣ በአሻም ቴሌቪዥን ላይ የተለያዩ የታሪክና የስፖርት ዝግጅቶችን ባማረና ቀልብን በሚስብ አቀራረብ ሰርቷል።

የሀገር ውስጥ ስፖርት ላይ ባለው አስተዋጽኦ ካፍ በ2009 ዓ.ም የ60 ዓመት ጎንደል ኦፍ ሜሪት ሽልማትም ሸልሞታል። ስድስት ጋዜጠኞች ብቻ ያገኙትን ሽልማት በመውሰድ ከምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው ነው። 

መጋቢት 5/1957 ዓ.ም በይርጋለም የተወለደው ጋዜጠኛ ገነነ ፤ ስፖርትና ታሪክ አጣምሮ የሚወድ ፣ ለሚናገራቸውም ወይም ለሚያቀርባቸው የጽሁፍ ስራዎች በቂ ማስረጃ እና ሰነድ ይዞ የሚቀርብ በመሆኑ " ተንቀሳቃሹ ቤተ መፅሐፍት " የሚል ስያሜንም አግኝቷል።

ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቢቆይም ዛሬ ህይወቱ አልፏል።

Via Ethio FM & Tikvah Sport

@tikvahethiopia