TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amhara

➡️ “ በአጠቃላይ 7 ሰዎች ሞተዋል። በተለይ ሕፃናት ተርበዋል ” - ደባርቅ የሚገኙ የትግራይ ተፈናቃዮች 

➡️ “ በድርቁም ችግር አለ፤ ተፈናቃዮች ላይም ችግር አለ ” - የሰሜን ጎንደር ዞን

በ2013 ዓ/ም ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በአማራ ክልል ፤ በሰሜን ጎንደር ዞን ፤ ደባርቅ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች እርዳታ እየተደረገላቸው ባለመሆኑ የምግብ እጥረት እንደተጋረጠባቸው፣ በዚህም የሞቱ ሰዎች እንዳሉ ገልጸዋል።

ተፈናቃዮቹ ሁኔታውን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል “ ኬንዳውን (መጠለያውን) አፈረሱብን። በየመስሪያ ቤቱ ብንገባም ተቀባይነት አጣን ” ብለዋል።

“ የትግራይ ተፈናቃዮች በየመስሪያ ቤቱ፣ በየመስጂዱ (በተለይ ሕፃናት፣ ሕሙማን፣ እናት አባት የሞቱባቸው) ናቸው ” ያሉ ሲሆን “ ባይሆን ለእነርሱ እንኳን እርዷቸው ብለን እንኳ ብንለምን ‘ ምንም የለም፤ ለእናንተ አይሰጥም ’ አሉን ” ሲሉ አማረዋል።

“ ሕዝቡ ግን ረሃብ ሞተ። በተለይ ሕፃናት ፣ መድኃኒት ተጠቃሚዎች። ከ2016 ዓ/ም መስከረም ወር ወዲህ 4 ሰዎች ሞተዋል። ከዚያ በፊት ደግሞ 3 ሰዎቸ ሞተዋል። በአጠቃላይ 7 ሰዎች ሞተዋል ” ነው ያሉት።

መጠለያውን ያፈረሱት ግንባታ ሊገነቡበት እንደሆነ ፣ የተፈናቃዮቹ ብዛት 403 አባውራ፣ በአጠቃላይ ደግሞ 1,244 መሆናቸውን፣ የተፈናቀሉት በ2013 ዓ/ም እንደሆነ ፣ የተፈናቀሉት ከመቐለ ፣ ከዓዲግራት ፣ ሽረና ሌሎች የተለያዩ ቦታዎች እንደሆነም አስረድተዋል።

“ እኛ እዚህ ተቀባይነትን ካጣን ሌላ ቦታ ተቀባይነት ካገኘን ዜግነታችንንም ቢሆን ቀይረን ፈርመን አብረን እንሄዳለን ተረካቢ ድርጅት ካገኘን ” እስከማለት የደረሱት እኚህ ተፈናቃዮች ይህን የወሰኑት የሚረዳቸው ስላጡ መሆኑን ገልጸዋል።

የእለት ደራሽ ምግብ እርዳታ እንዲሰጣቸውም አጥብቀው ጠይቀዋል።

በተፈናቃዮች በኩል ለቀረበው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ የጠየቅናቸው አንድ የሰሜን ጎንደር ዞን ባለስልጣን፣ “ የክልሉ አደጋ መከላከል ኮሚሽን ‘ከእኔ ውጪ መረጃ እንዳይሰጥ’ ብሎ በክልሉ መንግስት አሳውጇል። እኔማ እንዴት ብዬ ልስጥህ። ‘መረጃ በአንድ ማዕከል ይሁን’ ብለው አቅጣጫ ስለሰጡ ” ብለዋል።

እኝሁ አካል “ በድርቁም ችግር አለ። ተፈናቃዮች ላይም ችግር አለ። የሰላም ተመላሽ ላይም ችግር አለ። ይህን ለማለት ግን እቸገራለሁ። መረጃ ሰጥተናል ለክልሉ መንግስት ” ከማለት ውጪ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ተቆጥበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
° ለተናቃዮቹ ለምን እርዳታ አልተደገላቸውም ?
° መጠለያውስ ለምን ፈረሰ ? በማለት የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተቢበሪያ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ፍቅሬ ሙሉጌታን ጠይቋል።

ጉዳዩን #ከፍተኛ_የመንግስት_አካላት እንደያዙት እና እሳቸው ማብራሪያ መስጠት እንደማችሉ ከመግለጽ ውጪ ዝርዝር ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

#TikvahEthopiaFamilyAA

@tikvahethiopia