TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
20,000 ሰው

"በቃና ቴሌቪዥን 20 ሺ ሰው የሚፈልግ የስራ ማስታወቂያ ወጥቶ ነበር፤ ስራውን #ለመመዝገብ 2480 ብር አካባቢ ያስከፍላሉ እናም ዛሬ ለመመዝገብ "ልደታ መርካቶ" ህንፃ ሄደን ቢሮው #ታሽጓል፤ እነሱም #ታስረዋል ብለው መለሱን። እነዚህ አካላት እውነተኛ ናቸው? አይደሉም? ደግሞስ በሚዲያ እንዴት ይለቀቃል ታማኝ ካልሆነ?? እባክህ አጣራልን። አመሰግናለሁ!"

B ከተባለች የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የደረሰኝን ይህን ጥቆማ ይዤ "አብዛን ንግድ" ወደተባለው ድርጅት ጋር በተደጋጋሚ ስልክ ብደውልም ስልኮቹ በመዘጋታቸው ምክንያት ስለጉዳዩ መጠየቅ አልቻልኩም። ከድርጅቱ ምላሽ ሊሰጥ የሚችል አካል ካለ @tsegabwolde መልዕክት ያኑርልኝ።

/0930787232/
/0902087777/

ጉዳዩን አጣርቼ የምደርስበትን አሳውቃችኃለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስጠንቀቂያ በሀረሪ ክልል የህክምና ቁሳቁሶችን ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የሚሸጡ መድሃኒት መደብሮችን ከእኩይ ተግባራቸድ እንዲቆጠቡ የክልሉ ጤና ቢሮ አሥጠንቅቋል። ቢሮው ፥ በጤና ባለሞያዎች የታዘዙ የመድሃኒት ምርቱ እያለ የለም በማለት እና ለህብረተሰቡ በተጋነነ ዋጋ በማቅረብ የግል ጥቅማቸውን የሚያሯሩጡ መድሀኒት መደብሮች ከዚህ እኩይ ተግባር ሊቆጠቡ ይገባል ብሏል። በተያያዘ በጤና ባለሞያዎች…
#ታሽጓል

በሀረሪ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ፣ በጤና ባለሞያ ያልታዘዙ መድሀኒቶች ሲሸጡ እና የሞያ ፍቃድ ሳይኖራቸው መድሀኒት ሲሸጡ የነበሩ የመድሃኒት መደብሮች እየታሸጉ ነው።

ትላንት 6 ዛሬ ደግሞ 6 በአጠቃላይ 12 የመድሃኒት መደብሮች ላይ የማሸግ እርምጃ መውሰዱን ከክልሉ ጤና ቢሮ ሰምተናል።

ውስን ችግር ያለባቸው የመድሃኒት መደብሮች ደግሞ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

ምንጩ ያልታወቀ ምርት መሸጥ፣ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ፣ ያለ የሞያ ፍቃድ መስራት እንዲሁም በባለሞያ ያልታዘዙ መድሀኒቶች ሲሸጡ የተገኙ ተቋማት ላይ በቀጣይም ተመሳሳይ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ የክልሉ ጤና ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የውጭ አገራት ገንዘብ በሕገወጥ አሠራር ሲመነዘርባቸው ይታዩ የነበሩ ወይም በጥቁር ገበያ ይሳተፉ የነበሩ በዛ ያሉ ሱቆች መታሸጋቸውን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

በተለይ በብሔራዊ ቴአትር እና አካባቢው ፣ ስታዲየምና ዙሪያ ገባው ፣ ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንዲሁም ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢዎች በሚገኙ ልዩ ልዩ አነስተኛ ሱቆች ውስጥ በሚሰሩ ሰዎች አላፊ አግዳሚው ምንዛሪ ይፈልግ እንደሆን በግላጭ ይጠየቅ ነበር።

በእነዚህ አካባቢዎች በተለይ ደግሞ ወጣቶች በብዛት ሲሳተፉበት በሚስተዋለው ይህን መሰል ሕገ ወጥ ተግባር የአሜሪካ ዶላርን ፣ የአውሮፓ መገበያያ ገንዘብ ዩሮን፣ ፓውንድንና እና ሌሎች የውጭ አገራት ገንዘቦችን ብሔራዊ ባንክ በየዕለቱ ከሚያወጣው የውጭ አገራት ገንዘብ የምንዛሪ ተመን ከፍ ባለ የተጋነነ ልዩነት ሕገ ወጥ የገንዘብ ምንዛሪ ተግባር ሲፈፅሙ ማየት የተለመደ ዕለታዊ ክስተት ነበር።

ሬድዮ ጣቢያው ዛሬ በአካባቢው አደረኩት ባለው ቅኝት አብዛኞቹ ሱቆች በመደዳ በራቸው ላይ #ታሽጓል የሚል ማኅተም ያረፈበት ወረቀት ተለጥፎባቸው ተዘግተውና ለወትሮው በርከት ብለው ይህንኑ ተግባር በመፈጸም ይታዩ ከነበሩ ሰዎች መንገዶቹ ጭር ብለው ታዝቤያለሁ ብሏል።

እነዚህ ሱቆች ሲታሸጉ በአካባቢው የነበረውን ሁኔታ የተመለከቱ ሰዎች የማሸግ እርምጃው ' ቀይ ቀለም ያለው ወታደራዊ መለዮ ባጠለቁ ወታደሮች ' ታኅሣሥ 20/2014 ዓ.ም (ረቡዕ) በድንገት እንደተወሰደባቸው ተናግረዋል።

በወቅቱ ይሄንኑ ሕገወጥ ሥራ ሲያከናውኑ የነበሩና የተገኙ ሰዎችም እርምጃው ድንገተኛ ስለነበር በእነዚሁ የፀጥታ አካላት ተይዘው እንደተወሰዱ ለጀርመን ሬድዮ ጣቢያ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia