TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሼር #share

በነገው ዕለት የሩጫው ተሳታፊ የሆናችሁ ሴቶች በውድድሩ መነሻ ቦታ ላይ ቢያንስ አንድ #ሞዴስ በማምጣት ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥናት #ሞዴስ

በኢትዮጵያ ሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ለመግዛት ከሚያገኙት ገቢ አንጻር ከፍተኛ ወጪ እንደሚያወጡ " ቢቢሲ አፍሪካ ቪዡዋል ጆርናሊዝም " ባካሄደው ጥናት አመልክቷል።

ጥናቱ ፦ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ዋጋ ምን ያህል ተመጣጣኝ እንደሆነ ለማየት የተደረገ ነው። 9 የአፍሪካ ሀገራትንም ዳሷል።

ጥናቱ ፤ ዝቅተኛ ወርሃዊ ገቢን ከርካሽ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ዋጋ ጋር ያነጻጸረ ሲሆን በዚህም የምርቶቹ ዋጋ የበርካታ ሴቶችን አቅም ያገናዘቡ እንዳልሆኑ ደምድሟል።

ጥናቱ የተደረገባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው ?
- ጋና፣
- ኢትዮጵያ፣
- ሶማሊያ፣
- ኡጋንዳ ፣
- ናይጄሪያ፣
- ሩዋንዳ፣
- ታንዛኒያ፣
- ደቡብ አፍሪካ
- ኬንያ ናቸው።

በጋና ዝቅተኛ ደመወዝ ያላቸው ሴቶች ከሚያገኙት ገቢ #ከፍተኛ የተባለውን ወጪ የሚያወጡባት ሲሆን ኢትዮጵያ ከጋና ቀጥላ ተቀምጣለች ፤ ኬንያ በአንጻሩ ምርቶቹ ርካሽ የሆነባት አገር ናት።

ከ9ኙ አገራት መካከል በ6ቱ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሴቶች በየወሩ እያንዳንዳቸው 8 ነጠላ ሞዴሶችን የያዙ 2 እሽግ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ለመግዛት ከደመወዛቸው ከ3 እስከ 13 በመቶ የሚሆነውን ማውጣት ይጠበቅባቸዋል።

በጋና አንዲት ሴት ከምታገኘው ዝቅተኛ ደመወዝ ተብሎ ከተቀመጠው 26 ዶላር ውስጥ ሦስቱን ዶላር ወይም ከሚያገኙት 7 ዶላር ውስጥ አንዱን፣ ሁለት እሽግ የንጽህና መጠበቂያ ምርት ለመግዛት ታወጣለች።

ይህም አሜሪካ እና በዩኬ ካሉ ሴቶች ጋር ሲነጻጻር እጅግ ከፍተኛ ነው። በአሜሪካ ሴቶች ከሚያገኙት 1 ሺህ 200 ዶላር ዝቅተኛ ገቢ የንጽህና መጠበቂያ ምርት ለመግዛት የሚያወጡት 3 ዶላር ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ አንዲት ሴት ከምታገኘው ገንዘብ በአማካይ ስድስት በመቶውን ለሞዴስ ታወጣለች ብሏል ጥናቱ።

በኢትዮጵያ ከ2 ዓመት በፊት በመሰረታዊ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ላይ የቀረጥና የታክስ ማሻሻያ ማድረጓን የአገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር።

በዚህ ውሳኔ መሠረት እነዚህ የሴቶችና የህጻናት ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ከውጭ ተመርተው ሲገቡ ቀደም ሲል ተጥሎባቸው የነበረው የ30 በመቶ ከፍተኛ የታክስ ምጣኔ ተቀንሶ ወደ 10 በመቶ ብቻ እንዲሆን መደረጉን ሚኒስቴሩ መግለጹ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም።

ጎረቤት አገር ኬንያ በወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ከቀረጥ ነጻ በማድረግ ከዓለም የመጀመሪያዋ አገር የሆነችው እንደ አውሮፓውያኑ 2004 ነበር።

ከ2 ዓመት በኋላ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ለማምረት የሚውሉ ጥሬ እቃዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ አድርጋለች።

በዚህ ምክንያት በኬንያ ያለው የንጽህና መጠበቂያ ዋጋ ቀንሷል። አሁን ላይ ርካሹ የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) በ35 የአሜሪካ ሳንቲም ይሸጣል።

ሆኖም ሴት ፖለቲከኞች እና ተሟጋቾች ምርቶቹ ከዚህ ያነሰ ዋጋ ለተገልጋዮች እንዲቀርቡ አሁንም እየጠየቁ ነው።

Credit : BBC AMHARIC

@tikvahethiopia