TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ኩባንያው በ' ቲክቶክ ' ጉዳይ እስከመጨረሻው ያሉትን የህግ አማራጮችን ተጠቅሞ እንዳይታገድ ማድረግ ካልቻለ ፤ ለአሜሪካ ከመሸጥ ይልቅ እስከመጨረሻው #መዝጋት ይመርጣል ተብሏል።
አሁን ' ቲክቶክ ' የሚሰራበት #አልጎሪዝም ለኩባንያው እንደ ዋናው ነገር እንደሚቆጠርና በዚህ አልጎሪዝም መተገበሪያውን የመሸጥ እድሉ እጅግ ሲበዛ አነስተኛ እንደሆነ የኩባንያው ምንጮች ገልጸዋል።
በዚህም ፤ ለአሜሪካ ገዢ ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ እስከወዲያኛው ድረስ መዝጋትን እንደሚመርጥ ተጠቁሟል።
አሜሪካ ' ቲክቶክ ' እንዲሸጥ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ገደብ አስቀምጣለች ካልሆነ ግን እስከ ወዲያኛው እንዲታገድ ሕግ አጽድቃለች።
በርካታ ጉዳዩን የሚከታተሉ የዘርፉ ሰዎች አሁን ባለው የአሜሪካ አቋም 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ' ቲክቶክ ' እስከ ወዲያኛው ድረስ የመወገዱ ነገር እውን መሆኑ አይቀርም ብለዋል።
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#የደመወዝ_ጭማሪ " ታች ላለው የመንግስት ሠራተኛ 300 እጥፍ ደመወዙን ጨምረናል " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ መንግሥት ሠራተኛ የደመወዝ ጭማሪ ምን ተባለ ? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በዚህ ማብራሪያቸው በሪፎርሙ በዋጋ ንረት ምክንያት ሊጎዱ ይችላሉ / ሪፎርሙ በትሩን ሊያሳርፍባቸው ይችላል ተብሎ ከተለዩት የመንግሥት…
#Ethiopia
" መንግሥት ነዳጅ ይገዛል፣ ማዳበሪያ ይገዛል። ከዚህ ውጭ ሁሉ ነገር ብላክ ማርኬት / ጥቁር ገበያ ነበር ግብይቱ። አሁን ምን ተአምር ተፈጥሮ ነው ዋጋ የሚጨመረው ? " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ፖሊሲ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ምን አሉ ?
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፦
- ውሳኔው እንደውም የዘገየ ነው።
- አዲስ ነገር አልወሰንም።
- ኢትዮጵያ ገንዘቧን devaluate አደረገች/ ገንዘቧን አዳከመች የሚለው ስህተተ ነው።
- ገንዘብ devaluate አላደረግንም/ አላዳከምንም። ያደረግነው Unification ነው። ሁለት ገበያዎች ነበሩ አንዱ 100 አንዱ 50 ሲራራቁ አደጋው ስለበዛብን unify ይሁኑ ነው ያልነው።
- የተደረገው devaluation ሳይሆን unification ነው።
- ኢትዮጵያ ውስጥ ከነዳጅ እና ከማዳበሪያ ውጪ በብላክ ማርኬት / ጥቁር ገበያ የማይሰራ ምን ነገር አለ ? ልብስን ጨምሮ።
- ለመሆኑ ባንኮች ፣ የግል ባንኮች በብላክ ማርኬት / በጥቁር ገበያ አይዘረዝሩም ብር ? ኮሚሽን አይቀበሉም ? nepotism የለም ? በገበያው ነው የሚሰራው ? እንደዛ ነው ? ይሄን ያክል የማይገባን አታድርጉን።
- ሌላው ይቅር መንገድ ሲሰራ መንግስት ኮንትራት ሲሰጥ ኮንትራክተሮች በብላክ ማርኬት / ጥቁር ገበያ ሒሳብ ነው ዋጋ የሚያስገቡት።
- ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ስራ የለም በኖርማል በ50 ብሩ (1 ዶላር 50 ብር ሲመነዘር) የሚሰራ ስራ። የሚሰራው በጥቁር ገበያ ምንዛሬ ነው።
- መንግሥት ነዳጅ ይገዛል፣ ማዳበሪያ ይገዛል። ከዚህ ውጭ ሁሉ ነገር ብላክ ማርኬት / ጥቁር ገበያ ነው።
- አሁን ምን ተአምር ተፈጥሮ ነው ከ50 ወደ 70 ገባ ተብሎ ዋጋ የሚጨመረው ? እሱን እንነጋገራለን።
- ባንኮች ገበያውን እያያችሁት ወስኑ ስላልን 70 ፣ 50 ፣ 60 አድርጉ አንልም። አሁን የሄዳችሁበት ዋጋ መጠን unification አያረጋግጥም። እኛ ያልነው በብላክ ማርኬት / ጥቁር ገበያ እና በዋናው ገበያ ያለው ልዩነት significant መሆን የለበት insignificant እናድረግው እንጂ እናተ 70 ስትገቡ እነሱ 130 ከገቡ ምን ለውጥ አለው ? ይሄ ንግግር ይፈልጋል። እስካሁን የተሰራው በቂ አይደለም።
- ብላክ ማርኬት / ጥቁር ገበያውን የሚቀንስበትን መንገድ መከተል አለብን።
- ኢትዮጵያ ውስጥ ቡና የሚሸጥ ሰው ልክ ማታ ዜና ሰምቶ ጥዋት 10 ብር ቢጨምር ምንም ምክንያት የለውም #መዝጋት ነው። እንዲህ አይነቱን ጠንካራ በሆነ መንገድ ማስተካከል ያስፈልጋል።
- ክልሎች seriously ተከታተሉ (ዋጋ ሚጨምሩትን) ።
- ይሄ ለውጥ በግሉ ዘርፍ ምንም ለውጥ አያመጣም ማለት አይደለም። ለውጡ ስለሚታወቅ በተሰላ መንገድ የሚደረግ ለውጥ ችግር የለውም ግን መዝረፍና መቀማት አይፈቀድም።
- ዋጋ ጨማሪዎች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ይደረጋል። ጥብቅ እርምጃም ይወሰዳል።
- ያደረግነው ድርድር የተሳካ ነው (ከIMF እና WB ጋር ከመሳሰሉት)። ይሄን ውሳኔ ስንወስን ትውልድ አስበን ነው።
- ይህ የሪፎርም ውሳኔ እንደ ኮሶ መድሃኒት ነው ፤ በጣም ይመራል ግን ፍቱን መድሃኒት ነው። ይህን ጨክነን ካላደረግን ከበሽታን ካልተፈወስን ቀጣይ የምናስበውን እድገት ማረጋገጥ አንችልም።
- በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤክስፐርቶችን አነጋግረናል። ዝም ብለን ዘለን አልገባንም። ብዙ የዓለም ሞያተኞች ጋር ተወያይተናል።
- ሪፎርሙ በጣም ብዙ ጥቅም ስላለው ወሰድን እንጂ ችግር አለበት።
- በዚህ ሪፎርም የሚጎዱ ሰዎች አሉ።
1. የመንግሥት ሰራተኞች ፦ ለደመወዝ ማሻሻያ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ጠይቆናል። ታች ላለው 1500 ብር ለሚበላው ሰራተኛ 300 እጥፍ ደመወዝ ጨምረናል። ላይ ያለውን ከ25 ሺህ በላይ ለጊዜው ታገሱን ብለናል።
2. አርሶ አደሮች ፦ ምርቱን ኖርማል ዋጋ ሽጥ ንረት እንዳታመጣ እየተባለ ማዳበሪያ በውጭ ዶላር ምክንያት ስለሚጫንበት ማዳበሪያ ድጎማ እንቀጥላለን ብለናል። በቢሊዮን እናወጣለን።
3. የነዳጅ ተጠቃሚ ሁሉንም ፦ ትራንስፖርት ፣ ሸቀጣሸቀጥ ላይ ጉዳት ስለሚያመጣ ለነዳጅ ድጎማ ብቻ 100 ቢሊዮን ብር እናወጣለን።
- ድሃን የሚጎዳ ሪፎርም አንሰራም። ድሃ ተኮር ነን።
- ኮንትሮባንዲስቶች በእጅጉ ይጎዳሉ። ወርቅ ቅባት እህል ማጭበርበር ይቸገራሉ፣ ከጎረቤት ሀገር ጋር ማሻጠር ይቸገራሉ። ማርኬቱ እዛም እዚም እኩል ከሆነ ሰው በባህሪው ህጋዊ መንገድ ይከተላል።
- ኮንትሮባንዲስቶች ስለማይመቻቸው ዩትዩበር እየገዙ ሊንጫጩ ይችላሉ። ግን አያስቆሙንም።
- ድሃ እንዳይጎዳ እንሰራለን። ኮንትሮባንዲስቶች እስካሁን የዘረፋችሁት ይበቃል አሁን ወደ ህጋዊ መንገድ ግቡ ብለን እንመክራለን።
- ይሄ ሪፎርም የመሳካት ውጤቱ ሆነ የአለመሳካት ውጤቱ በእኛ እጅ ላይ ነው። ወሳኞቹ እኛው ነን። ዋና ዋና ተዋናዮቹ ፦
• አርሶ አደር ፦ ጨክኖ ማረስ አለበት። ምርት ማደግ አለበት።
• ኤክስፖርተሮች ፦ በፍጥነር እጃቸው ላይ ያለውን እያወጡ ገንዘብ ማስገባት አለባቸው።
• ገቢ ፦ ገቢ መሰወር አደገኛ ነው። የሚገባችሁን ውሰዱ ቀሪውን ለመንግሥት ስጡ።
• መንግሥት ፦ ዋናው ተዋናይ ነው። ገቢ ሲሰበስብ የማይሰርቅ ፣ አገልግሎት በአግባቡ መስጠት አለበት... ።
እነዚህ ከተሟሉ ይሳካል። ከእነዚህ አንዳንዶቹ ከተበላሹ ሪፎርሙ ይጎዳል።
- አደገኛ ጥንቃቄ የሚያስገልገው ስግብግብ ነጋዴ ነው። አላግባብ ዋጋ ከጨመረ ስራ ያበዛብናል ፤ የሌባና ፖሊስ ጨዋታ እንጀምራለን። ማህበረሰቡንም ይጎዳል።
- ባለፉት 2 ፣ 3 እና 4 ዓመታት የኢትዮጵያ ገበያ ብላክ ማርኬት ሆኖ ስላበቃ ምንም አዲስ ነገር አያስገልግም ጥቂት ቦታዎች አሉ እነሱን እንደጉማለን።
- ይሄ ዓመት ይሄ ሪፎርም ከባድ ጊዜ ነው መዘጋጀት ያስፈልጋል። ብዙ ጣጣ ይኖረዋል። ይሄን አመት ያንገጫግጨናል። ይሄን ዓመት በአንድነት ከሰራን ከቀጣይ አመት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያድጋል።
ሙሉ ማብራሪያው ፦ https://youtu.be/kk7CaKaQQSU?feature=shared
#TikvahEthiopia