ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።
#GondarUniversity
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ ግብሮች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በሦስተኛ ዲግሪ፣ በስፔሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊቲ ኘሮግራሞች ያሰለጠናቸውን ከ7000 በላይ ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።
#WerabeUniversity
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዙር ተመራቂ ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።
በ5 ኮሌጆች ስር በሚገኙ በ14 ፕሮግራሞች በመደበኛው መርሃ-ግብር ወንድ-629 ሴት- 503 በድምሩ 1,132 ትምህርታቸውን ከተከታሉት ውስጥ 1077 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።
#JinkaUniversity
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎቹን አስመርቋል።
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በአራት ኮሌጆች በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመደበኛ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 854 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።
የዛሬዎቹ ተመራቂዎች 501 ወንድ እና 353 ሴት ናቸው።
#DebreMarkosUniversity
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ለ12ኛ ዙር ዛሬ ጥር 15 እና ነገ ጥር 16/2013 ዓ/ም በቡሬ እና ዋናው ግቢዎች ያስመርቃል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና " የማህበራዊ ሳይንስ " የሁለተኛ ቀን የፈተና መርሀግብር ዛሬ ሲካሄድ ውሏል።
በነገው ዕለት የመጨረሻው ቀን የፈተናው መርሃ ግብር ተካሂዶ ቀድሞ በወጣው መርሀ ግብር ተማሪዎች ከነገ በስቲያ ጀምሮ ወደ የመጡበት እንዲመለሱ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዛሬው የፈተና ውሎ ጋር በተያያዘ በተለይም በደብረ ማርቆስ እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች አንዳንድ ተማሪዎች ከፈተና ማዕከል ለቀው ስለመውጣታቸው ለመስማት ችለናል።
በደብረ ማርቆስ እና ደብረ ታቦር ምንድነው የሆነው ?
#DebreTaborUniversity
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጥዋት በተወሰኑ " የፈተና አሰጣጥ ሥርዓቱን አናከብርም ፤ አንፈተንም ! " ባሉ ሥነ-ምግባር በጎደላቸው ተማሪዎች የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ተስተጓግሎ ነበር ሲል ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው በተለይ " ካልተኮራረጅን አንፈተንም ! " በሚል እሳቤ ለመበጥበጥ የሞከሩ አካላት ከደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ፣ ከደብረ ታቦር አስተዳደር ፣ ከከተማው ሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሀይማኖት አባቶችና ሌሎች አጋር አካላት ጋር ባደረገው ጥረትና ውይይት ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል ሲል አሳውቋል።
በከሰአቱ መርሀ ግብር የፈተና አሰጣጥ ፤ " ስርዓቱን አክብረን እንፈተናለን " ያሉ ተማሪዎች ተለይተው ፍጹም በሆነ መረጋጋት ፈተናቸውን እንደተፈተኑ ተቋሙ ገልጿል።
ዛሬ በደብረ ታቦር ከነበረው ሁኔታ ጋር በተያያዘ አንድ የደብረ ታቦር የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ምክንያቱ በምን እንደተነሳ ባያውቀውም በግቢው ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ጩኸት እና ተኩስ ሲሰማ እንደነበር ገልጿል።
የዶቼ ቨለ ሬድዮ በበኩሉ አንድ የአይን እማኝ በግቢው በተፈጠረው ችግር ጉዳት መድረሱን እንደገለፁለት ዘግቧል።
ፈተናውን መፈትን የማይፈልጉ ግቢውን እንዲለቅቁ ፣ ፈተናው መፈተን የሚፈልጉ ደግሞ ወደ ፈተና አዳራሽ እንዲገቡ ተነግሮ ፈቃደኛ ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ እየተፈተኑ እንደሆነ፤ ፈቃደኛ ያልሆኑት ደግሞ ግቢውን ለቅቀው እንዲወጡ መደረጉን እኙሁ የአይን እማኝ ተናግረዋል።
ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ላይ ስለጉዳት መጠን እና ዝርዝር ያለው ነገር የለም። ስለደረሰ ጉዳት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት እንጥራለን።
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፤ የተማሪ ቤተሰቦች እንዲረጋጉ ያሳሰበ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል።
በተቋሙ ያልተከናወኑ ጉዳዮች የተፈጸሙ በማስመሰል ኃላፊነት የጎደለው አሉባልታ በማሰራጨት ተማሪዎች ፈተናቸውን በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ እንዳይፈተኑ ለማድረግ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እያሰራጩ የመገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አጥብቆ እሳስቧል።
የቲክቫህ ቤተሰብ የሆነ አንድ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኛ የግቢው መግለጫ ትክክለኛ መሆኑን ገልፀው " እደግፈዋለሁ " ብለዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ ስለጉዳዩ ምንም ሳያውቁ የሚፅፉ ሰዎች የሚያደርጉት ድርጊት ይበልጥ ትውልዱን በራሱ እንዳይተማመንና እራሱን እንዳይችል የሚያደርግ እና ሀገርንም በእጅጉ ሚጎዳ ተግባር መሆኑ ጠቁመዋል።
ዛሬ ፈተናውን ሳይፈተኑ ግቢውን ለቀው ወጡ ከተባሉ ተማሪዎች በኩል ምን እንደተፈጠረ እና እንዳጋጠመ ለማወቅ @officialtikvahethiopiaBOT ላይ መልዕክታቸውን ማግኘት አልቻልንም።
#DebreMarkosUniversity
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ብሔራዊ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል በራሳቸው ፈቃድ ፈተናውን ጥለው የወጡ ተማሪዎች እንደነበሩ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
የከተማው ተቀዳሚ ከንቲባ ይትባረክ አወቀ ፤ ለዶይቼ ቬሌ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃላቸው ፤ " ከምሥራቅ ጎጃም አንዳንድ ወረዳዎች የመጡ ተማሪዎች ለተፈታኝ ተማሪ የማይመጥን መፈክር በማሰማት በጠዋት የመፈተኛ ግቢያቸውን ጥለው ወጥተዋል። " ሲሉ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ ፈተና እንዲወስዱ የተለያዩ አካላት ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካም ሲሉ ገልፀዋል።
" ተማሪዎቹ ባልተጨበጠ ወሬ እና በመንደር ፖለቲካ ተጠልፈዋል " ያሉት አቶ ይትባረክ ፤ " ግቢውን ጥለው ከወጡት ተማሪዎች ውጪ ሌሎች ተረጋግተው ተፈትነዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ " እንደተደበደቡ እና እንደተዋከቡ " ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ እንደሆነ ገልጸዋል።
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶክተር ተፈራ መላኩ ለአሐዱ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠቱ ቃል ደግሞ ፤ በዩኒቨርሲቲው ስር 4 የመፈተኛ ጣቢያች መኖራቸውን ጠቅሰው የዛሬውን ፈተናን አንፈተንም ብለው የወጡት በ " ጤና ካምፓስ " ውስጥ ሲፈተኑ የነበሩ ጥቂት ተማሪዎች ናቸው ብለዋል።
የተማሪዎቹ ፈተና አቋርጦ በፈተና ማዕከል መውጣት ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በርካታ የተዛቡ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ ያሉት ዶክተር ተፈራ ፤ " ተማሪዎቹ ፈተናውን ያቋረጡበት ዋነኛው ምክንያት ከዝግጅት ጉድለት የመነጨ ነው። " ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ በበኩሉ ፈተና አቋርጠው የወጡት በዩኒቨርሲቲው ጤና ካምፓስ የሚፈተኑ እና "ፈተናው የከበዳቸዉ ጥቂት ተማሪዎች " ናቸው የሚል መረጃ አጋርቷል።
ፈተና ጥለዉ ከወጡ ተማሪዎች መካከል አብዛኛዎቹ በ2013 ዓ.ም የጨረሱና ዳግም ፈተና የተፈቀደላቸው መሆናቸው ፖሊስ ያጋራው መረጃ ይገልጿል።
"ፈተና መፈተን ያልፈለጉ" ተማሪዎች በሰላም ግቢውን ለቀው ወጥተው እያለ ተቋሙ ውስጥ ብጥብጥ እንዳለ ተማሪዎችም እንደቆሰሉ ፣ እና እንደተደበደቡ ተደርጎ የሚሰራጨዉ ፍፁም መረጃ ሐሰት ነው ሲል አሳውቋል።
የትምህርት ሚኒስቴር በደብረ ታቦር እና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ጉዳዩ ላይ እስካሁን ድረስ ያለው ነገር የለም።
@tikvahethiopia