TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#መምህራን " የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስት በመወያየት የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን እንዲከፍለን እንጠይቃለን " - የትግራይ መምህራን ማህበር የትግራይ መምህራን ማህበር የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስት በመወያየት የመምህራንን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዲከፍል ጠየቀ። ማህበሩ ይህን ያለው ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ ነው።…
“ የ2015 ዓ.ም የ5 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ በአጭር ጊዜ እንደሚከፈል መግባባት ላይ ተደርሷል ” - የትግራይ መምህራን ማህበር

የትግራይ መምህራን ማህበር ስራ አስፈፃሚ ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ባካሄደው ውይይት ላቀረባቸው ጥያቄዎች የሚጨበጥና ተስፋ ሰጪ መልስ ማግኘቱን ለሁሉም የወረዳ መምህረን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ማህበሩ ምን አለ ?

- የመምህራን መብትና ጥቅም አስመልክቶ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በተቀናጀ መልኩ እየጠየቀ መምጣቱን ማህበሩ ገልጿል።

- የመምህራን መብት እንዲጠበቅ በተለይ በጦርነቱ ምክንያት ሳይከፈል የቀረው የ17 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ አስመልክቶ ታህሳስ 17 / 2016 ዓ.ም በማህበሩ ማኔጅመንት ደረጃ አስቸኳይ ውይይት በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉን አስታውሷል።

- ከውሳኔዎቹ አንዱ በተለይ የመምህራን ውዝፍ ደመወዝ ጥያቄ እስከ ጥር 15 /2016 ዓ.ም ካልተመለሰ በትግራይ ደረጃ ሰላማዊ ሰልፍ እናካሂዳለን የሚል ነው ፤ ስለዚሁ ጉዳይ የመምህራን ማህበር ስራ አስፈፃሚ ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ባጠረ ጊዜ ውስጥ ውይይት እንዲካሄድ የሚልም የውሳኔ ሃሳብ እንደነበር አመልክቷል።

- በተቀመጠው ውሳኔ መሰረት የትግራይ መምህራን ማህበር ስራ አስፈፃሚ ጥር 4 / 2016 ዓ.ም ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳና ከትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ ውይይት ማካሄዱን የውይይቱ ዋና ነጥቦችም ፦
የ2015 ዓ.ም የ5 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ፣
የ2014 ዓ.ም የ 12 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ፣
ከደደቢት ማይክሮፋይናስ ስለተወሰደ የብድር ወለድ ስለሚነሳበት ሁኔታ፣
የመምህራን የትራንስፖርት አገልግሎት ሰርቪስ ስለማግኘት፣ የሚሉ እንደነበሩ አሳውቋል።

- በውይይቱ በተለይ ውዝፍ ደመወዝን በሚመለከት የ2015 ዓ.ም የ5 ወራት በአጭር ጊዜ #እንደሚከፈል ፣ የ2014 ዓ.ም የ12 ወራት ውዝፍ ደመወዝ መከፈል የሚመለከት ጥያቄ ወደ ፌደራል መንግስት መቅረቡ ፣ ከደደቢት ማይክሮፋይናንሰ የተወሰደ የብድር ወለድ ስለሚነሳበት ሁኔታ ቀጣይ ውይይት እንደሚካሄድ ፣ የከተማ የመምህራን ሰርቪስ የሚመለከት ጥያቄ በአጭር ጊዜ እንደሚመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል።

- በአጠቃላይ ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ የተደረገው ግንኙነት ገንቢ እንደነበረ ፣ አቅጣጫ የተቀመጠላቸው ጉዳዮች አፈፃፀማቸው የሚመለከት ቀጣይ ውይይት እንደሚካሄድ መተማመን ላይ መደረሱን ማህበሩ ገልጿል።

መረጃውን ማህበሩ ለሁሉም የትግራይ ወረዳ መምህራን ማህበር ጥር 7 / 2016 ዓ.ም ፅፎ የላከውን ሰርኩላር ደብዳቤ ዋቢ በማድረግ ያደረሰን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                               
@tikvahethiopia