TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥቅምት 4/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሶማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 146 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሰው አልተገኘም።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 85 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 27 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 765 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 76 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የ2 ሰው ህይወት አልፏል (1 ከእንጅባራ ህክምና ማዕከል፣ 1 ከሃይቅ)

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 579 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 102 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 142 የላብራቶሪ ምርመራ 54 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 94 የላብራቶሪ ምርመራ 13 ሰዎች በቫረረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1304 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 55 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#AddisAbaba

በአ/አ ባለፉት 24 ሰዓት 3,246 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 308 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

* ያልተካከቱ የክልል ሪፖርቶችን ቆይት ብላችሁ ይህንኑ ፖስት ተመልከቱ !

@tikvahethiopiaBOT
ጥቅምት 6/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 137 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 35 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 606 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 115 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የ1 ሰው ህይወት አልፏል (ከጎንደር)

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 560 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 101 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ1 ሰው ህይወት አልፏል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 185 የላብራቶሪ ምርመራ 12 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 94 የላብራቶሪ ምርመራ 05 ሰዎች በቫረረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

* ላልተካከቱ የክልል ሪፖርቶችን ቆየት ብላችሁ ይህንኑ ፖስት ተመልከቱ !

@tikvahethiopiaBOT
#Harari

በሐረሪ ክልል የሐኪም ወረዳ ፖሊስ ጽ/ ቤት ለጥፋት ዓላማ ሲዘጋጁ የነበሩ 17 ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳወቀ።

በ15ቱ ተጠርጣሪዎች መኖርያ ቤት በተደረገው ፍተሻ በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተይዘዋል።

የጦር ሜዳ መነጽር ፣ የራዲዮ መገናኛ ፣ ፎቶ ካሜራ ፣ የጦር መሳርያ መያዣ ቁሳቁሶች ፣ 20 የሚደርሱ ሲም ካርዶች ፣ የጦር ሜዳ የመጀመርያ ህክምና መስጪያ ቁሳቁሶች ከተጠርጣሪዎቹ የተያዙ ናቸው።

በተጨማሪ የተለያዩ መታወቂያዎች፣ የባንክ ቤት ቼክና ደብተር፣ ላፕቶፖች፣ የጸረ ሽምቅ ውጊያ ማስተማሪያ መጽሃፎች እና ሌሎች ቁሳቁሶችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

Via ENA
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Harari

ዛሬ የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን አሳውቋል።

ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከልም 88.3 % ተማሪዎች ወደ ቀጣይ 9ኛ ክፍል የተዛወሩ ሲሆን የተሻለ ውጤትም ተመዝግቧል ብሏል ቢሮው።

የፈተናዉ ውጤት በቀጣይ ቀናት ለሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚሰራጭ እንደሆነ ተገልጿጻ።

ተማሪዎች ከሰኞ ጥር 3 ጀምሮ ውጤታቸውን በየትምህርት ቤታቸው በመመልከት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሚከታተሉበት ት/ቤት ምዝገባ እንዲያከናውኑ መልዕክት ተላልፏል። ~ የሀረሪ ክልል ት/ት ቢሮ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Harari : በሀረሪ ክልል የአዲስ መንግስት ምስረታ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ማካሄድ በጀመረው የመንግስት ምስረታ ጉባኤው የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር , የምክር ቤቱን አፈጉባኤ እና ምክትል አፈጉባኤ እንደሚሾም ይጠበቃል።

በተጨማሪም ጉባኤው በቆይታው በርዕሰ መስተዳድሩ የሚቀርቡ የምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የካቢኔ አባላትንም እጩዎችን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡

በክልሉ የአዲሱን መንግስት ምስረታ ለመታደም ከፌዴራል መንግሥት እና የሀረሪ ክልልን ከሚያዋስኑ አጎራባች ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

@tikvahethiopia
#Harari

ከፌደራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መምሪያ የሚተላለፉ መመሪያዎች እንደተጠበቁ ሆነው÷ የሀረሪ ክልል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ በክልሉ ውስጥ ከጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የክልከላ መመሪያዎች አውጥቷል።

ክልከላዎቹም ፦

1. ከፀጥታ አካላት ውጪ ማንኛውም እግረኛ በክልሉ ውስጥ ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 11:00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

2. ከአምቡላንስ እና ከጸጥታ አካላት ተሽከርካሪ ውጪ ማንኛውም ተሸከርካሪ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 11:00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎችና ሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች ከከተማው በስተጀርባ ያለውን መንገድ ወይም ባይ ፓስ መጠቀም ይችላሉ።

3. የክልሉ ሰሌዳ የሌላቸው ማናቸውም ታክሲዎች (ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪናዎች ጨምሮ) ወደ ክልሉ መግባት አይችሉም፤ የክልሉ ሰሌዳ ያላቸው ታክሲዎችም ወደ ሌላ ክልል መውጣት የተከለከለ ነው።

4. ከህክምና ተቋማትና የመድኃኒት ቤቶች በስተቀር ማንኛውም የንግድ ተቋማት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 11:00 ሰዓት አገልግሎት መስጠት አይችሉም።

#Share #ሼር

@tikvahethiopia
#Harari

በፖሊስ የአምቡላንስ መኪና የኮንትሮባንድ እቃ ሲያዘዋውሩ የተገኙ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

የክልሉ ፖሊስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በፖሊስ ኮሚሽን የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ አምቡላንስ በቀን 24/ 4/ 2014 ዓ.ም በህገወጥ መንገድ በርካታ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ጭኖ ሲንቀሳቀስ አወዳይ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር እንደዋለ ገልጿል።

አምቡላንሱ የኮንትሮባንድ እቃ የጫነ ቢሆንም ታማሚ የያዘ በመምሰልና የአምቡላንስ ድምፅ በማሰማት ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር የዋለው።

ተሽከርካሪው እና አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን አሽከርካሪው ለጊዜው መሰወሩና በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም የተከሰተውን ህገወጥ ድርጊት በወቅቱ ለበላይ አካል ማሳወቅ ሲገባቸው ያላሳወቁ አባላትም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

አሽከርካሪው አምቡላንሱን ከኮሚሽኑ ቅጥር ጊቢ ጎማ ለማሰራት በሚል በህገ ወጥ መንገድ ያለ መውጫ ይዞ እንዳወጣ ፖሊስ አሳውቋል።

ምንጭ፦ የሀረሪ ክልል ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#Harari

ለቀጣይ ሶስት ወራት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራዮችን ማስወጣት ተከለከለ።

በዛሬው ዕለት የሐረሪ ክልል መስተዳድር ም/ ቤት ባካሄደው ውይይት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራዮችን ከተከራዩት ቤት ማስወጣትን የሚከለክለው ደንብ መርምሮ ማፅደቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

ምክር ቤቱ ደንቡን ያፀደቀው በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተስተዋለ ያለውን የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እና በዜጎች ላይ የሚያሳድረውን ተፅእኖ ለመቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ብላል።

አዋጁ ለሶስት ወራት እንደሚቆይና የ " ንግድ ቦታ ኪራይን " እንደማያካትት ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia #Harari

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በሐረሪ ክልል መጀመሩን አሳውቋል።

ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት መሆኑን ተገልጿል።

በሐረሪ ክልል የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች የሚካሔድ ሲሆን ደንበኞች በዐ7 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት ይችላሉ ተብሏል።

ደንበኞች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርዶችን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶች ጥቅል እንደሚያገኙ ተገልጿል።

የደንበኝነት ማስጀመሪያ ጥቅሉ በሚያልቅበት ጊዜ ደንበኞች የአየር ሰዓት ከሽያጭ ማዕከላት ወይም መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች በመግዛት መሙላት እና አገልግሎቱን መጠቀም መቀጠል ይችላሉ።

በሐረሪ ክልል አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳውቆናል።

#SafaricomEthiopia #ሐረር_ክልል #Harari

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SafaricomEthiopia #Harari ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በሐረሪ ክልል መጀመሩን አሳውቋል። ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት መሆኑን ተገልጿል። በሐረሪ ክልል የደንበኞች…
#Harari #SafaricomEthiopia

በሐረሪ ክልል ፤ የ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " መለያ በተለጠፈባቸው ሁሉም መደብሮች እና ሱቆች ሲም ካርድ እና የአየር ሰዓት መግዛት ይቻላል ተብሏል።

በተጨማሪ በአራተኛ እና በሥላሴ አካባቢ ባሉት ሁለት የሽያጭ ማዕከሎቹ የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች ድጋፍ አገልግሎት በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጥሪ ማዕከል በተለያዩ ቋንቋዎች ፦
- በአማርኛ፣
- በአፋን ኦሮሞ ፣
- በሱማሊኛ፣
- በትግርኛ እና እንግሊዝኛ አገልግሎት የማግኘት አማራጭ ያላቸው ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞችን በ 👉 700 ላይ በመደወል ማናገር ይቻላል።

#SafaricomEthiopia #ሐረሪ #Harari

@tikvahethiopia