TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መልዕክት

የጥምቀት በዓል የቤተክርስቲያኒቱን ክብር በጠበቀ መልክና በሰላም እንዲከወን ኮሚቴዎች ተዋቅረው እየሰሩ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አሳውቃለች።

የጥምቀት በዓል የቤተክርስቲያኒቱ መገለጫና ትልቅ በዓል በመሆኑ በዓሉን ለማስፈፀም በተለያየ ዘርፍ የተቋቋሙ የበዓሉን መርሐ ግብር በተሟላ ሁኔታ የሚያግዙ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ስራቸውን እየሰሩ ይገኛሉ።

ቤተክርስቲያኗ፤በዓሉ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የዓለም ህዝብም የሚያደንቀው የቤተክርስቲያን በዓል ነው ብላለች።

ከበዓሉ ላይ በተያያዘ ሊደረጉ የማይገባቸው ጉዳዮች ተነስተው መልዕክት ተላልፏል። ይህም በዋናነት የባንዲራና የአለባበስ ሥነ ሥርዓትን የሚመለከት ነው።

አለባበስን በተመለከተ ካህናት የቤተክርስቲያኒቱን ሥርዓት በጠበቀ መልኩ መልበስ እንዳለባቸው ተገልጿል።

ምዕመናንም እንደተለመደው #ነጭ_ልብስ ለብሰው መገኘት እንዳለባቸው መልዕክት ተላልፏል።

በተጨማሪ በዓሉን ላይ የሚያዙ ጥቅሶች የሚያስማሙ እንጂ የሚያጋጩ ሊሆኑ እንደማይገባቸው ቤተክርስቲያን መልዕክቷን አስተላልፋለች።

ባንዲራን አስመልክቶ ምዕመናን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያጸደቀችው የቤተክርስቲያኒቱ አርማ ያለበትን ባንዲራ እና የፌዴራል መንግስቱን ባንዲራን መያዝ እንደሚችሉ ከዚያ ውጪ ግን ይዞ መውጣት እንዳልተፈቀደ አስገንዝባለች።

በተጨማሪ ምዕመናን የሚመጡት በዓሉን ለማክበር እንደመሆኑ በዓሉን የጸብና የመታገያ መድረክ ሊያደርጉት እንደማይገባ ማሳስቢያ ተላልፏል።

"ማንም የፖለቲካ ሀሳቡን በቤቱ  እንጂ የእምነት ማስፈጸሚያ ቦታ ላይ ሊተገብረው አይገባም፤ እንዲህ ያለ ድርጊት በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ ያስወግዛልም፤ የፖለቲካ ሀሳባቸውን ለማስፈጸሚያ የሚጠቀሙ የቤተክርስቲያኒቱ ጠላቶች ናቸውም " ተብሏል።

@tikvahethiopia