TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ😷

ባለፉት 24 ሰዓት 24 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 7,840 የላብራቶሪ ምርመራ 1,982 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 867 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 202,545 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,825 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 155,190 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 795 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ😷

ባለፉት 24 ሰዓት 16 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 8,296 የላብራቶሪ ምርመራ 1,976 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,435 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 204,521 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,841 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 156,625 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 828 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ😷

ባለፉት 24 ሰዓት 24 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 8,022 የላብራቶሪ ምርመራ 2,068 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,484 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 206,589 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,865 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 158,109 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 865 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ😷

ባለፉት 24 ሰዓት 22 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 8,294 የላብራቶሪ ምርመራ 2,372 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,327 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 208,961 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,890 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 159,436 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 853 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ😷

ባለፉት 24 ሰዓት 25 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 9,017 የላብራቶሪ ምርመራ 2,353 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 493 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 211,314 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,915 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 159,929 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 829 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ

በየምርጫ ጣቢያዎቹ ውጤት እየተለጠፈ ይገኛል፤ ነገር ግን በርካታ #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ ነው።

ውድ አባላት ይፋዊና ቦርዱ ማህተም ያላረፈባቸውን ፤ በተለም ደግሞ በዘፈቀደ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎችን #በጥንቃቄ እንድትከታተሉ ይሁን።

ከምርጫ በኃላ ችግር የሚፈጥረው እንዲህ አይነት ጉዳይ ስለሆነ ሰላማዊ ሂደቱ እንዲጠበቅ አስተዋጽኦ አድርጉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በአዲስ አበባ ሀርመኒ ሆቴል ለዓለም ዓቀፉ የቁርዓን ውድድር ማጣሪያ ሲካሄድ ውሏል። የፊታችን እሁድ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የቁርኣን ሂፍዝ ውድድር እንደሚካሄድ ይታወቃል። በዚህ ልዩ ውድድር ላይ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የመጡ ተወዳዳሪዎች መካከል ዛሬ የማጣሪያ ውድድሩ እየተካሄደ ሲሆን ውድድሩ በዓለም ዓቀፍ ዳኞች የተመራ ነበር። በእሁዱ ውድድር የሶማሌ ክልሉ ተወላጅ…
#እጅግ_በጣም_አስቸኳይ

በነገው ዕለት የዓለምዓቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር መዝጊያ ፕሮግራም በስታድየም ይደረጋል ተብሎ የተገለጸ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁንና አንዳንድ ዶክመንቶች በጊዜ ባለማሟላታቸው እንዲሁም አዲስ አበባ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት የተቆፋፈረና ምቹ ባለመሆኑ የመዝጊያው ፕሮግራም ከስታዲየም ውጪ እንዲደረግ ተወስኗል።

ስለዚህም ህዝቡን ይቅርታ እየጠየቅን ከዚህ ጋር የተያያዙ ዝርዝር ጉዳዮችን በቀጣይ ጊዜያት የምናሳውቅ ይሆናል።

ማሳሰቢያ ፦ ከሀገሪቱ ጫፍ እስከ ጫፍ ወደ አዲስ አበባ እየመጣችሁ ያላችሁ እንግዶች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይህንን በመገንዘብ ሳትለፉ ባላችሁበት እንድትከታታሉ እንጠይቃለን።

(አዘጋጅ ፦ ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር)

የነገውን ፕሮግራም ተካፋይ ለመሆን ስትጠብቁ የነበራችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን የአዘጋጆቹን መልዕክት ያልሰሙ ካሉ #ሼር አድርጓቸው / ላኩላቸው።

@tikvahethiopia
#ትኩረት

በአማራ ክልል፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በዚህ ሰዓት የፀጥታ ችግር መኖሩን በወረዳው ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል።

ያለው ሁኔታ #እጅግ_በጣም ከፍተኛ የሆነ ትኩረት የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለው የፀጥታ ስጋት " ለነፍሳችን ሰግተናል " ያሉ ነዋሪዎች የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ እና ሁኔታው እንዲረጋጋ ጠይቀዋል።

ዛሬ በወረዳው ለተፈጠረው የፀጥታ ችግር ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረግን ነው።

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ፤ "ሰንበቴ በአሁኑ ሰአት ጭንቅ ውስጥ ገብታለች ፤ ዱኣ ወይም ፀሎት ትፈልጋለች!! የሚመለከተው የመንግስት ባለድርሻ አካላትን ልዩ ትኩረት ትሻለች። " ሲል አንድ አጭር ፅሁፍ አሰራጭቷል።

ወረዳው ይህንን ከማለት ውጭ ስለጉዳዩ ምንም የሰጠው ዝርዝር መረጃ የለም።

በአጣዬ በኩልም ስጋት መኖሩን ቤተሰቦቻችን እየገለፁ ይገኛሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በአካባቢው ካሉት የቤተሰብ አባላቱ ሁኔታውን ለመከታተል ጥረት ያደርጋል።

ይህ የሀገራችን ቀጠና ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጊዜ የፀጥታ ችግር ሲከሰትበት እና የሰዎች ህይወት ሲቀጠፍበት ፣ ንብረትም ሲወድምበት እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
ለመላው የኢትዮጵያ ልጆች የቀረበ ጥሪ !

የ " ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር " በድርቅ ምክንያት ለጉዳት የተጋላጡ ወገኖችን ለመርዳት የሚያስችል የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጥሪ አቅርቧል።

ማህበሩ ከቅርብ አመታት ወዲህ በደቡባዊና ደቡብ ምስራቃዊ አካባቢዎች የተከሰተው የድርቅ አደጋ በሰውና በእንስሶች ላይ ያስከተለውና እያስከተለ ያለው ጉዳት #እጅግ_አስከፊ መሆኑን ገልጿል።

ማኅበሩ እ.አ.አ በ2022 ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባባር ፦
- በደቡብ ክልል ከንባታ ጠንባሮና ጋሞ ዞኖች፣
- በኦሮሚያ ክልል ቦረና፣ ባሌ፣ ምስራቅ ባሌ እና ምስራቅ ጉጂ ዞኖች፣
- በሶማሌ ክልል ሸበሌ፣ ፋፈን እና አፍዴር ዞኖች ከዚህ በተጨማሪ ሞያሌ አካባቢ በድርቅ አደጋ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ 14,530 አባዎራዎችን ህይወት ለመታደግ ከ104 ሚሊዮን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

በአሁኑ ወቅትም በተለይም #በኦሮሚያ እና #ሶማሌ ክልሎች እንዲሁም ሞያሌ አካባቢ በ206.3 ሚሊዮን ብር መሰል ድጋፍ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው።

ድርቁ በሰውም ሆነ በእንስሶች ላይ እያስከተለ ካለው ጉዳት አንፃር እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ማህበሩ የተጎጂዎችን ህይወት ለመታደግ እያደረገ ያለውን ጥረት መላው ኢትዮጵያውያን በአይነትም ሆነ በገንዘብ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል።

እንዴት ድጋፍ ማድረግ ይቻላል ?

1ኛ. #የአይነት_ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ አዲስ አበባ ስቴዲየም አካባቢ በሚገኘው የማህበሩ ዋና መ/ ቤት ግቢ ድረስ በማምጣት መለገስ ይችላሉ።

2ኛ. የገንዘብ ልገሳ ማድረግ የሚፈልጉ በ #ቴሌ_ብር ሂሳብ ቁጥር 0907 ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ።

3ኛ. ለቦረና ድርቅ ምላሽ ተብሎ በተከፈት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 👉 1000529766916 እንዲሁም 907 አጭር የሂሳብ ቁጥርን በመጠቀም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በዳሽን ባንክ፤ በአቢሲኒያ ባንክ፤ በአዋሽ ባንክ እና በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይቻላል።

4ኛ. የእጅ ስልክ በመጠቀም በ9400 ላይ OK ብሎ በመላክ 1 ብር መለገስ ይቻላል።

#EthiopianRedCrossSociety
#ETHIOPIA🇪🇹

@tikvahethiopia
Audio
#Gondar

የጎንደር ግጭት ከተማዋን አስከፊ ሁኔታ ላይ እንደጣላት አንድ በጎንደር ሆስፒታል የሚሰራ የቲክቫህ የቤተሰብ አባል የሆነ የሕክምና ዶክተር አሳውቆናል።

የጎንደር ሁኔታ #እጅግ_አስከፊ እንደነበር የገለፀልን የህክምና ዶክተሩ " በግጭቱ ምክንያት የመጨረሻ ኢሰብአዊ ድርጊት ተፈጽሟል ፤ ሰላማዊ ዜጎች እዚህም እዚያም ተገድለዋል " ሲል አስረድቷል።

በሆስፒታሉ ውሃ ፣ ኦክስጂን ፣ እንዲሁም ደግሞ መድሃኒት ቤት ከመድሃኒት ውጭ እየሆኑ መሆኑን ገልጿል።

" የከባባድ መሳሪያ ድምጾች ከሆስፒታሉ ውስጥ ሆነን ይሰማን ነበር " ያለው ዶክተሩ ላለፉት ቀናት ከተማዋ በተኩስ ስትናጥ መቆየቷን አመልክቷል።

እስከ ትላንት ሰኞ ከሰዓት ድረስ በግጭቱ ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል የሚያመላልስ እና አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ አንድ አምቡላንስ ብቻ እንደነበር እሱም በሚያስዝን ሁኔታ ዒላማ መደረጉን የጎንደር ሆስፒታል ዶ/ር የሆነው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል አሳውቆናል።

የንፁሃን ነዋሪዎች ጉዳይ ትኩረት የሚሻው መሆኑን አስገንዝቧል።

(ድምፅ ዛሬ ጥዋት ላይ የተቀዳ)

@tikvahethiopia
#Hawassa

" እንደሚወራው አይደለም ፤ ከአንድ ቤት በላይ የከፋ ጉዳት አላደረሰም " - የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

በሀዋሳ ከተማ የተነሳ የእሳት አደጋ አንድ መዝናኛ ቤት አውድሞ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።

ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት አካባቢ በከተማው በተለምዶ 05 በመባል በሚታውቀዉ ሰፈር (አደባባይ አለፍ ብሎ ወይም ከመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት/አስፓልት ተሻግሮ) የተነሳው የእሳት አደጋ አንድ መዝናኛ ቤትን በከፋ ሁኔታ አውድሞ በቁጥጥር ስር ውሏል።

እሳት አደጋው የደረሰው በማህበር ተደራጅተዉ በምግብና መጠጥ ሽያጭ የሚተዳደሩ ወጣቶች ውስጥ በአንደኛው ቤት ነው።

የእሳት አደጋው መፈጠሩን ተከትሎ በአካባቢው ግርግር ቢፈጠርም ከሰአት በኋላ ሁሉም ተረጋግቶ ወደተለመደው እንቅስቃሴ ተመልሷል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የከተማው ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ወንድሙ ቶርባ ፤ " ችግሩ እንደተፈጠረ የሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የኢንዱስትሪው መንደር የእሳት ብርጌድ በፍጥነት ደርሶ ተቆጣጥሮታል " ብለዋል።

" ከፍተኛ አደጋ በደረሰበት መዝናኛ ቤት ውስጥ በነበረ የኤሌክትሪክ ገመድ ላይ በተፈጠረ እሳት ነው አደጋው የተፈጠረው " ሲሉ ገልጸዋል።

በአደጋው በመዝናኛ ቤቱ ላይ ውድመት መድረሱን ጠቁመዋል።

አደጋው በደረሰበት ወቅት በአካባቢው ወደነበሩ ቤቶች እሳቱ እንዳይስፋፋ ሌሎች ሰዎች እቃቸዉን ቢያወጡም ቆይተው ወደቤቶቻቸዉ ተመልሰዋል ብለዋል።

" ከሁኔታው ጋር በተያያዘ ግርግር ቢፈጠርም ሰዎች ተመልሰው ወደ ስራቸዉ ገብተዋል " ሲሉ አክለዋል።

" አደጋው እንደሚወራዉ #እጅግ የከፋ አይደለም " ያሉ ሲሆን ከአንድ ቤት በላይ የከፋ ጉዳት አላደረሰም ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia