TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ነቀምቴ አንድነታቸውን አጠናክረው ለአካባቢያቸው ጽዳትና ደህንነት ተግተው እንደሚሰሩ በነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። ብሔራዊ የጽዳት ቀን ዛሬ በነቀምቴና ቁኒ ከተሞች ተካሄዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ነቀምቴ

ትናንት የተካሄደውን አገር አቀፍ የደም ልገሳ ቀንን ምክንያት በማድረግ የነቀምቴ ደም ባንክ 302 ዩኒት ደም መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡ የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዴሬሳ ባያታ እንዳሉት ’’ ደም ለግሰን ሕይወትን እናድን’’ በሚል መሪ ሃሳብ ትናንት በነቀምቴ ከተማና በተለያዩ የወለጋ ዞኖች ደም የማሰባሰብ ሥራ ተከናውኗል። በነቀምቴ ከተ አንደኛ ማዞሪያ እና ወለጋ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በሻምቡ፣ ባኮ እና ጊምቢ ከተሞች በተዘጋጁ ጊዜያዊ የደም መሰብሰቢያ ማዕከሎች 500 ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ 302 ዩኒት ደም በአንድ ቀን መሰብሰቡን አስረድተዋል፡፡ ደም ለጋሾቹ በበኩላቸው የጀመሩትን የደም ልገሳ በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ነቀምቴ

"...ጥቃት ያደረሰባቸው ሰው ማንነት ገና አልታወቀም። የፀጥታ ሰዎች ግን ክትትል እያደረጉ ነው። ከሰሞኑ ጉዳይ ጋር አይገናኝም!" አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ
.
.
ኢትዮ-ቴሌኮም የምዕራብ ሪጅን ሥራ አስኪያጅ አቶ ገመቺስ ታደሰ ትናንት ምሽት በመኖሪያ ቤታቸው መገደላቸውን የነቀምት ከተማ ኮምንኬሽን ጽህፈት ቤት ዛሬ አስታውቋል። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ ለጀርመን ራድዮ ጣቢያ እንደተናገሩት አቶ ገመቺስ የተገደሉት ተተኩሶባቸው ነው፤ ጥቃቱን ፈጽመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ማንነት ለመለየትም የፀጥታ አካላት ክትትል እያደረጉ ነው። ግድያው ሰሞኑን በኦሮምያ ከተፈጠረው አመረጋጋት ጋር የተያያዘ ስለ መሆን አለመሆኑ የተጠየቁት አቶ ደሳለኝ ግድያው ከሰሞኑ ተቃውሞ ጋር የተያያዘ አይደለም ብለዋል።

«ትናንት ማታ የተመቱት ግለሰብ በመሣሪያ ነው የተመቱት። በመኖሪያ ቤታቸው ነው ጥቃቱ የደረሰበት። ጥቃት ያደረሰባቸው ሰው ማንነት ገና አልታወቀም። የፀጥታ ሰዎች ግን ክትትል እያደረጉ ነው። ከሰሞኑ ጉዳይ ጋር አይገናኝም። ከዚሁ ጋር በተገናኘ የተለየ ሰልፍ የወጣ የለም። የተለየ ያሳየው ተቃውሞም የለም።» የነቀምት ከተማን ጨምሮ የወለጋ አራቱም ዞኖች ላለፉት አራት ወራት በወታደራዊ እዝ (ኮማንድ ፖስት) ስር ናቸው።

Via DW(የጀርመን ድምፅ ራድዮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ነቀምቴ

የአራቱ የወለጋ ዞኖች ማለትም የምስራቅ፣ ምእራብ፣ ሆሮ ጉዱሩ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች እንዲሁም የነቀምቴ ከተማ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ የሰላም ኮንፍረንስ በነቀምቴ ከተማ እየተካሄደ ነው። የኢህአዴግ እና የኦዲፒ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ በኮንፍረንሱ ላይ በመገኘት ተሳታፊዎችን በማወያየት ላይ ይገኛሉ።

በውይይቱ ላይ የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ አቶ በዳሳ ጂንፌሳ ባስተላለፉት መልእክት፥ የኦሮሞ ህዝብ ባለው እሴት አንድ ሆኖ የባርነት ቀንበርን እንደሰበረ ሁሉ ችግሮቹንም በአንድነት በመሆን በውይይት መፍታት አለበት ብለዋል። አንድ መሆን ከቻልን ችግሮችን በቀላሉ መፍታት እንችላለን ሲሉም ከንቲባው መልእክት አስተላልፈዋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia