TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቤቲንግ

የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ሲስተም የሚሰጡ ድርጅቶች ፍቃድ ለሌላቸው የውርርድ ቤቶች ሲስተም እየሰጡ መሆኑን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ሲስተም የሚሰጡ ድርጅቶች ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ህጋዊ ፍቃድ ላላገኙ አካላት የመወራረጃ ሲስተም በመስጠት ህገወጥ ስራ እየሰሩ ነው ብለዋል።

አቶ ቴዎድሮስ ፤ ህገወጥ የውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶች እየተበራከቱ የመጡት ውርርዱን እንዲሰራ የሚያደርገውን ስርዓት (system) የስፖርት ውርርድ ሲስተም ሰጪ ድርጅቶች ፍቃድ ለሌላቸው የቤቲንግ ቤቶች እየሰጡ በመሆኑ እንደሆነ ገልፀዋል።

" በዚህ ምክንያት የስፖርት ውርርድ መመሪያው እየተሻሻለ ነው " ያሉ ሲሆን " ሲስተሙን የሚሰጡ ድርጅቶች ለአንድ ሲስተም ለሚፈልግ ግለሰብ ሲስተሙን ከመስጠታቸው በፊት የብሄራዊ ሎተሪ ፈቃድ አለህ ወይ ? ብለው ማረጋገጥ አለባቸው " ብለዋል።

" ፍቃድ የሌላቸው በቀላሉ ሲስተሙን የሚያገኙ ሰዎች ከቅርንጫፍ ስታንዳርድ እና ከኛ ቁጥጥር ውጪ የቤቲንግ ቤቶችን እየከፈቱ ነው " ያሉት አቶ ቴዎድሮስ ይህ በህግ ስርዓት ላይ እንዲገባ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

" ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሲስተም ፕሮቫይድ የሚያደርጉ ድርጅቶች በስፖርት ውርርድ መመሪያ ውስጥ እንዲካተቱ ይደረጋል" ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የውርርድ ቤቶች ቅርንጫፍ ከመከፈታቸው በፊት በመመሪያው መሰረት ስለመከፈቱ እንዴት ታጣራላችሁ ? የሚል ጥያቄ አንስቷል።

አቶ ቴዎድሮስ ፤ በቁጥጥር ሰራተኞቻቸው በኩል ቅርንጫፍ ከመከፈቱ በፊት መመሪያውን ተከትሎ ስለመከፈቱ ቀድመው ሄደው እንደሚያዩ አስረድተዋል።

ፍቃድ የሌላቸው እና ሲስተሙን በቀላሉ የሚያገኙ ሰዎች በየቦታው ህገወጥ የውርርድ ቤቶችን እየከፈቱ መሆኑን በመጠቆም በተለይ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ከተሞች ይሄ ችግር በስፋት መኖሩን ጠቁመዋል።

በቅርቡ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር መመሪያውን ባልተከተሉና ህገወጥ የውርርድ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ያስታወሱት አቶ ቴዎድሮስ ፤ በክልል ከተሞች የተሰራው የቁጥጥር ስራ አመርቂ ውጤት እንዳልታየበት በመጥቀስ " አዲስ አበባ ላይ እየታየ ያለውን መልካም ውጤት በክልሎች ለመድገም እንሰራለን " ብለዋል።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቤቲንግ

ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ጨምሮ ሌሎችም ተቋማት ነገ ከጥዋቱ 2:30 ላይ የስፖርት ውርርድ ፈቃድ ከተሰጣቸው ድርጅቶች ጋር ሊመክሩ ቀጠሮ መያዛቸው ተሰምቷል።

ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር አዘጋጀሁት ባለው የምክክር መድረክ ላይ ፤ የስፖርት ውርርድ ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች ጥዋት 2:30 ላይ ቀበና አካባቢ በሚገኘው ራስ አምባ ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ እንዲገኙ ጥሪ አቅርቧል።

አስተዳደሩ ነገ የድርጅት ሥራ አስኪያጅ ወይም አንድ ተወካይ እንዲገኝ ጥብቅ ማሳሰቢያ የሰጠ ሲሆን በውይይቱ ላይ የሚቀርቡ መረጃዎች፦

1. የድርጅቱ ቅርንጫፍ መ/ቤቱች ዝርዝርና ሙሉ አድራሻ / አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ ክልል ከተሞች የሚገኙ ቅርንጫፎች በተናጠል / ከተቻለም በቅርቡ በተደረገው ዘመቻ የተዘጉ ቅርንጫፎች እንዲለዩ ወይም የተለየ ምልክት እንዲደረግባቸው፤
2.  የድርጅቱ ሠራተኞች ብዛት
3. የድርጅቱ የቴክኖሎጂ አቅራቢ ድርጅት ሥምና አገር ናቸው ብሏል።

በውይይቱ ላይ፣ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ እና የአዲስ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ተወካዮች ይገኛሉ ተብሏል።

በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ 3,241 የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ መወሰዱ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ " ቤቲንግ " ቤቶቹን ለማሸግ ምክንያት ናቸው ያላቸው ፦

- ከስፖርት መጫወቻነቱ ባለፈ ሀገር  ተረካቢ ትውልድን እያጠፋ በመሆኑ፤
- ከፍተኛ የወንጀል ማስፍፊያ እየሆነ በመምጣቱ፤
-  የከተማውን ወጣት ግዜውን አላግባብ በስፍራው እያሳለፈ በመምጣቱ፤
- ከተፈቀደላቸው ፈቃድ ዉጪ እየሰሩ በመምጣታቸው፤
- የሰዉ ልጅ ህይወት አላግባብ እየጠፋ በመምጣቱ፤
- ተማሪዎችም ትምህርታቸውን ትተዉ በቦታው እየተገኙ በተገቢው መንገድም እንዳይማሩ በማድረጉ ፤
- የመማር ማስተማሩን ሂደት እያወከ በመምጣቱ የሚሉት እንደሚገኙበት አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቤቲንግ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ጨምሮ ሌሎችም ተቋማት ነገ ከጥዋቱ 2:30 ላይ የስፖርት ውርርድ ፈቃድ ከተሰጣቸው ድርጅቶች ጋር ሊመክሩ ቀጠሮ መያዛቸው ተሰምቷል። ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር አዘጋጀሁት ባለው የምክክር መድረክ ላይ ፤ የስፖርት ውርርድ ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች ጥዋት 2:30 ላይ ቀበና አካባቢ በሚገኘው ራስ አምባ ሆቴል የስብሰባ…
#ቤቲንግ

➡️ " ቤቲንግ ቤቶች ዳግም #እንዳይከፈቱ ሕብረተሰቡ አሳስቦናል " - የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ

➡️ " ሁሉንም ቤቶች በጅምላ መፈረጅ ትክክል አይደለም። ህጉን ተከትለው የሚሰሩና ብዙ ሰራተኛ ያላቸው ቤቲንግ ቤቶች አሉ " - የቤቲንግ ቤት ባለቤቶች

በአዲስ አበባ ከተማ በቤቲንግ ቤቶች እንቅስቃሴ ዙሪያ ሲካሄድ በነበረ የዳሰሳ ጥናት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉ ተሰምቷል።

ውይይቱ የተደረገው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ገቢዎች፣ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኃላፊዎች ወይም ተወካዮች በተገኙበት ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በተቋቋመው ግብረሃይል አማካይነት ባለፈው ጊዜ በዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ የተገኙ የቤቲንግ ቤቶች በጥናት ተመስርቶ እንዲታሸጉ መደረጋቸውን ገልጿል።

በዚህም፦

1ኛ. አብዛኛው ቤቲንግ ቤቶች በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ላይ በመሆናቸው፣

2ኛ. የብሔራዊ ሎቶሪ ባወጣውን ደንብ መሠረት ዕድሜያቸው ከ21ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች ገብተው ሲጫወቱ በመገኘታቸው፣

3ኛ. በቤቶቹ ውስጥ አዋኪ ድርጊቶች ማለትም፦ ጫት መቃም፣ አልኮል መጠጦች መጠጣት...ወዘተ ሲፈፀምባቸው በመገኘታቸው፣

4ኛ. ያለንግድ ፈቃድ ሲሰሩ በመገኘታቸው፣

5ኛ. የቡድን ፀብ የተከሰተባቸው መገኘታቸው ለመዘጋታቸው ምክንያት መሆኑን አስረድቷል።

ቢሮው፤ " ሕብረተሰቡም በቤቲንግ ቤቶች ደስተኛ እንዳልሆነ ተረድተናል " ብሏል።

ቢሮው ፤ ከዘርፉ ከሚገኘው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ አመዝኖ እንደሚታይ ፤ ቤቲንግ ቤቶች ዳግም እንዳይከፈቱ ሕብረተሰቡም አሳስቦናል ሲል አሳውቋል።

በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱ ምክንያቶች የታሸጉ የቤቲንግ ቤቶች ፦

1ኛ. ለቤቲንግ ቤት ያከራዩ የቤት ባለቤቶች የንግድ ዘርፉን ቀይረው ከመጡ፣

2ኛ. " አገልግሎቱን አንፈልግም ካሁን ቀደም ሳናውቅ ስለገባንበት ከዚህ በኋላ አንሠራም " ብለው ማረጋገጫ ለሚሠጡና ቤቶቹ ተከፍተው ለሌላ አገልግሎት እንዲውሉ ለማድረግ ዝግጅቱ ተጠናቋል ሲል የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።

በሌላ በኩል፤ በአዲስ አበባ ስፖርት ውርርድ /ቤቲንግ/ በመንግስት ከታሸገ 3 ወር ሆኖታል የሚሉ በዘርፉ ላይ ያሉ አካላት ፤ ትክክለኛ መረጃ እያገኙ እንዳልሆነና በየ ወረዳው የሚነገራቸው የተለያየ ሃሳብ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

" ዘርፍ ቀይሩ ወይንም ዕቃ አውጡ እየተባልን ነው ፤ ብሄራዊ ሎተሪ እንደሚከፍትልን እና ዝግጅት እንድናደርግ ብሎም እድሳት አድርጎ ፍቃዳችንን ከሰጠ በኋላ ነው እንዲ የተጉላላነው " ብለዋል።

" በስራችን ብዙ ሰራተኞችን የያዝን እና ከፍተኛ ግብር ለሀገራችን የምናስገባን ድርጅቶች ማንገላታት አግባብ አይደለም " የሚሉት የዘርፉ ባለቤቶች " ስራ በሌለበት ወቅት ብዙ ስራ አጦች በከተማችን ባሉበት ሁኔታ ተጨማሪ ስራ አጦች እንድንሆን እየተደረግን ነው " በማለት ቅሬታ አቅርበዋል።

" ቤቲንግ መስራት ሲገባቸው አለአግባብ ከህግ ውጪ የሚንቀሳቀሱ ካሉ በህግ መጠየቅ እንጂ ሁሉንም በአንድ መፈረጅ አይገባም " ብለዋል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ቤቲንግ ቤቶች እስከ ወዲያኛው እንዲዘጉ ጫና እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

የዘርፉ ባለቤቶች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፤ " በአጠቃላይ ጥብቅ ቁጥጥር ተደርጎ ከእምነት ተቋማት ፣ ከትምህርት ቤት መራቅ ያለበትን ርቀት ተከትሎ እድሜ ከ21 አመት በላይ ብቻ እንዲጠቀም ተደርጎ ቢቀጥል ለሀገርም ለህዝብም ጥቅም ይኖረዋል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምን አለ ?

መጋቢት 7 / 2016 ዓ/ም ባጋጠመው የሲስተም ችግር ምክንያት ያለአግባብ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር ፤ በዚህም በርካታ ግለሰቦች በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የወሰዱትን የገንዘብ ልክ እየመለሱ እንደሆነ ገልጿል። 

ነገር ግን አንዳንድ ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ ወደ #ቤቲንግ (የስፖርት ውርርድ) ተቋማት በማዛወራቸው መመለስ እንደተቸገሩ ጥቆማ እንደሰጡት ገልጿል።

ገንዘቡን ተመላሽ ማድረግ እንዲቻል ወደ ቤቲንግ ተቋማት የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ ያዘዋወሩ አቅራቢያቸው በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመገኘት ለዚሁ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት እንዲያመለክቱ አሳስቧል።

ባንኩ ገንዘብ ወስደው ሙሉ ሙሉ ያልመለሱ (በከፊል የመለሱ) ቀሪ ያልመለሱትን ገንዘብ እንዲመልሱ በማለት ለ5,166 ደንበኞቹ የሰጠው የመጨረሻ ማሳስቢያ ዛሬ ቅዳሜ አብቅቷል።

@tikvahethiopia
#Hawassa

በሀዋሳ ከተማ የስፓርት ውርርድ ( #ቤቲንግ ) ቤቶች እየታሸጉ / እየተዘጉ ይገኛሉ።

ይህ ተከትሎ የስፖርት ውርርድ ቤት ባለቤቶች " እንዴት የንግድ ፈቃድ እያለን ይዘጋብናል ? " ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

እነዚህ የስፖርት ውርርድ ቤቶች ከወራት በፊት በተለያዩ ምክኒያቶች ተዘግተው የቆዩ ሲሆን በቅርቡ ተከፍተው ነበር።

አሁን ላይ ተመልሰው መዘጋት/መታሸግ መጀመራቸው ግራ እንዳጋባቸውና ልክ እንደባለፈዉ ጊዜ ከስራቸዉ ተስተጓጉለው ቤት መዋል መጀመራቸው እንዳሳዘናቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ቤተሰብ አባል ፥
° ቤቶቹን ለምን ታሸጉ ?
° መፍትሄውስ ምንድን ነው ? ሲል የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለን ጠይቋል።

እሳቸውም ፤ " #በሲዳማ_ክልል_ስር የወጣ አንድም የንግድ ፈቃድ የለም " ብለዋል።

" ከወራት በፊት ከነዚህ አካላት (ቤቲንግ ቤቶች) ጋር በነበረን ውይይት የንግድ ፈቃድ በማውጣት ህጋዊ እንዲሆኑ ተግባብተን ነበር " ሲሉ አስታውሰዋል።

" ይሁንና ከረዥም ጊዜ በኋላ ዳግም ስናጣራ አሁንም ህጋዊ መሆን አልቻሉም " ያሉት ሀላፊው " ከዚህ ባለፈም እነዚህ ቤቶች በትምህርት ቤት ፣ በሀይማኖት ተቋማትና በመኖሪያ ሰፈሮች እንዲሰሩ አይፈቀድም ሌላዉ የመዘጋታቸዉ ምክኒያት ይኸው ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።

ለግለሰቦቹ በሰላማዊ መንገድ ምክንያቱ ተነግሯቸው ቤታቸዉ እየተዘጋ መሆኑን የገለጹት አዛዡ ፤ " ከዚህ ዉጭ ' ገንዘብ ተወሰደብኝ ' እንዲሁም ' የአላግባብ ህገወጥ የሆነ ተግባር ተፈጽሞብኛል ' የሚል አካል በማንኛዉም ሰአት ወደ ሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመምጣት ሊያመለክት ይችላል " ብለዋል።

ቤቶቹ ተመልሰው #የመከፈት እድል አላቸዉ ወይ ? ተብለው የተጠየቁት ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ " መጀመሪያ ህጋዊ ይሁኑ ከዛ በኋላ ከፖሊስ በተጨማሪ የሚመለከታቸዉ አካላት የሚመለከቱት ጉዳይ ይሆናል " ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia