TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Kenya

የኬንያው ፕሬዝዳንት ተቃውሞ በተደራጀባቸው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቀርበው ከወጣቶች ጋር ተወያዩ።

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ያዘጋጁትን የፋይናንስ ሕግ ውድቅ እንዲያደርጉ ያስገደዳቸው የወጣቶች ተቃውሞ የተደራጀበት ማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ ለውይይት መቅረባቸው ታሪካዊ ነው ተብሏል።

ሩቶ ትላንትና ከሰዓት በ ' X ' ስፔስ ላይ ቀርበው ከህዝብ ለሚነሳው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

' X ' ላይ ከተቃዋሚ ወጣቶቹ ጋር ለጥያቄ እና መልስ መቅረባቸው ፍጹም ያልተጠበቀ እንደነበር ተነግሯል።

ፕሬዝዳንቱ በውይይቱ ቀጥተኛ እና መሸፋፈን ያልታየባቸው ጠንካራ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ነበር።

መጀመሪያ ውይይቱ በጽህፈት ቤታቸው ይፋዊ ገጽ አስተናጋጅነት ሊካሄድ ነበር በኋላ ባገጠመ እክል ከፕሬዝዳንቱ ተቃዋሚዎች አንዱ በሆነ ኦሳማ ኦቴሮ በተባለ ግለሰብ ገጽ ገብተው ነው ምላሽ የሰጡት።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ያለ ከልካይ የፈለጉትን ሲጠይቁ፣ ፕሬዝዳንቱ ሲናገሩ መሃል ላይ እየገቡ ሲመላለሱና ማብራሪያ ሲጠይቁ ነበር።

ተቃዋሚዎቹ ምን አሏቸው ?

መንግስታቸው እስካሁን ያስመዘገበውን ነገርና ባህሪያቸውን በተመለከተ አንስተው አብጠልጥለዋቸዋል።

በርካታ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በፖሊስ በጭካኔ መገደላቸውን አመልክተው " በሽብርተኛ አገር ውስጥ ነው እንዴ ያለነው? " በማለት ጠይቀዋቸዋል።

የመረጣችሁ ሰው በመሆኑ ቅድሚያ ለሰው ግድ ሊሰጣችሁ ይገባል ብለዋቸዋል።

ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ሥራ አጥ የሆነ አንድ የውይይቱ ተሳታፊ " በካቢኔዎት ውስጥ ብቃት የሌላቸው በርካታ ባለሥልጣናት አሉ " ብሏቸዋል።

➡️ ሙሰኛ እና የተቀመጡበት ቦታ የማይገባቸው በርካታ ሰዎች በመንግስት ውስጥ እንዳሉ ነግረዋቸዋል።

የተገደሉ ወይም የተጎዱትን ሰዎች ቤተሰቦች ለማነጋገር ሞክረዋል ወይ? ሲሉም ጠይቀዋል።

አንዳንዶች ውሸታም እና ሐዘኔታ የሌላቸው በሚል ከሰዋቸዋል።

ፕሬዝዳንቱ ምን መለሱ ?

● በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ባለሥልጣናትን በሙሉ ለማባረር ቃል ገብተዋል።

● " እውነት ነው ፤ አንዳንድ ባለሥልጣኖቻችን አስጸያፊ ድርጊቶችን እንደሚያሳዩ እስማማለሁ ፤ እራሳቸውን እንዴት እንደሚያስተካክሉ እኔም ጉዳዩን በግሌ አንስቼላቸዋለሁ። ከዚህ የበለጠም አደርጋለሁ " ብለዋል።

● በተቃውሞው የተገደሉ ሰዎችን አሃዝ በማጋነን አንዳንዶችን " ግድየለሽ " ሲሉ ከሰው ቁጥሩ 25 መሆኑን ተናግረዋል።

● በጥይት የተገደለ የ12 ዓመት ህፃን እናት ማነጋገራቸውን ገልጸዋል።

● በተቃዋሚዎች ላይ ሲተኩስ በካሜራ እይታ ውስጥ የገባ የፖሊስ አባል ክስ እንዲመሰረትበት እንዳዘዙ ተናግረዋል።

NB. የኬንያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ እንደሆነ አሳውቋል።

● ሩቶ አምባገነን እንዳልሆኑ ተናግረዋል። " እኔ ፕሬዝዳንት ነኝ ትክክል !! ግን ፕሬዜዳንቱ ፍጹም ስልጣን የለውም ለዛም ነው ዴሞክራሲያዊ ሀገር የሆነው ቼክ ኤንድ ባላንስ አለ። ፕሬዝዳንቱ አምባገነን አይደለም " ብለዋል።

● ረቂቅ ሕጉን ማንሳታቸውን በማረጋገጥ ፣ ሕጉን በተመለከተ ግን የተሳሳተ ግንዛቤ መፈጠሩን ጠቅሰዋል። የሕጉ ዓላማ የኬንያውያንን ንግድ ማጠናከረ ነበር በማለተ የተካተቱትን ዕቅዶች ጠቃሚነት አብራርተዋል።

ታሪካዊ ነው በተባለውና ምንም አይነት ቁጥጥር ባልነበረው የ ' X ' ህዝባዊ ግልጽ ውይይት መድረክ ላይ ከ150,000 በላይ ሰዎች ታድመው ነበር። 

ከዚህ በፊት አንድ ፕሬዝዳንት ይህን ያህል በይፋ ወጥቶ እራሱን በማጋለጥ ከሕዝቡ በቀጥታ ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠበት ጊዜ ባለመኖሩ ምክንያት ነው ታሪካዊ የተባለው።

ፕሬዝዳንት ሩቶ ሁልጊዜ በሚያስቆጡ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮችን በሚመለከት ክርክር ውስጥ ሲሳተፉ ይታያል።

በፖለቲካ ሕይወታቸው ፈታኝ ጥያቄዎችን እና ሁኔታዎችን ከመጋፈጥ ወደ ኋላ ሲሉም ታይተው አይታወቅም።

በመገናኛ ብዙኃን ዘንድ ከቀደምት ፕሬዝዳንቶች በበለጠ በራቸው ክፍት መሆኑ ይነገራል።


#BBCNEWS
#Kenyans
#CitizenTV

@tikvahEthiopia