TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ለቀናት የስራ ማቆም አድማ ላይ የቆዩት የዓየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሰራተኞች ዛሬ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ መግታቸውን ፋና ዘገበ።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል ኮሎኔል #ወሰንየለህ_ሁነኛው
ሰራተኞቹ ወደ ስራ መመለሳቸውን አረጋግጠዋል።

ከመንግስት በተሰጠ አቅጣጫም በደመዎዛቸው ላይ #ማስተካከያ ለማድረግ ጥናት ይካሄዳል ብለዋል።

የሌሎች ሰራተኞችን ፊርማ #አስመስሎ በመፈረምና ሌሎች ስራ እንዲያቆሙ በማነሳሳት ወንጀል የተጠረጠሩ ዘጠኝ የሲቪል አቭዬሽን እና የዓየር ትራፊክ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።

ተጠርጣሪዎቹም ትናንት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱም ለመርማሪ
ፖሊስ የስምንት ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የነዳጅ ምርቶች ላይ መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል‼️

በአለም ላይ ያለውን የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ጭማሪን ግምት ውስጥ በማስገባት እና በህዳር ወር ተደረገው ዋጋ #ማስተካከያ ዝቅተኛ በመሆኑ፥ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ #መጠነኛ_ጭማሪ ማድረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፡-

•ቤንዚን በሊትር 19 ብር ከ69 ሳንቲም የነበረው 20 ብር ከ19 ሳንቲም

•ነጭ ናፍጣ በሊትር 17 ብር ከ78 ሳንቲም የነበረው 18 ብር ከ03 ሳንቲም

•ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 15 ብር ከ41 ሳንቲም የነበረው 15 ብር ከ66 ሳንቲም

•ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 14 ብር ከ90 ሳንቲም የነበረው 15 ብር ከ15 ሳንቲም

•እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 20 ብር ከ62 ሳንቲም፣

•ቤኒዚን ኢታኖል ድብልቅ በሊትር 19 ብር ከ89 ሳንቲም እንዲሁም ኬሮሲን በሊትር 18 ብር ከ03 ሳንቲም ሆኗል፡፡

የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋው ከነገ ጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ማደያዎች ተግባራዊ እንደሚሆንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 22/2011 ዓ.ም.

በሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ #መሃመድ_ዑመርን ጨምሮ በ47 ግለሰቦች ላይ #ክስ ተመስርቷል።
.
.
ለከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉትን ‹‹ቪ8›› መኪኖች በሌሎች አዳዲስና ወጪ ቆጣቢ ተሽከርካሪዎች የመተካቱ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገልጿል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው #አለመረጋጋት እና የተቃውሞ ቀናት ጉዳት ሳይደርስበት በሀሰት ጉዳት የደረሰበት በማስመሰልና ይህንን የሃሰት ፎቶ በማህበራዊ ድረ ገፅ በመልቀቅ ግጭቶች እንዲፈጠሩ ለማድረግ የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
.
.
በቅርቡ የፀደቀውን የስደተኞች አዋጅ በመቃወም በአዲስ አበባና በጋምቤላ #የተቃውሞ_ሠልፍ ሊደረግ እንደሆነ ተሰምቷል።
.
.
በሶማሌ ክልል ግጭት፣ ግድያና ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ከአራት ወራት በላይ በእስር ላይ የነበረው #ቴዎድሮስ_አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) በ80,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጥቷል።
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን "ግዴታዬን እወጣለሁ ፣ መብቴንም እጠይቃለሁ!" በሚል መርህ ቃል የከተማ አቀፍ የታክስ ንቃናቄ መድረክ ተካሂዷል።
.
.
ከኮንሶ ዞን ወደ ሶያማ ቡርጂ ወረዳ ሲጓዝ በነበረ የጭነት መኪና ላይ ባልታወቁ #ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በትላንትናው ዕለት የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል።
.
.
#በምሥራቅ_ወለጋ_ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች 2ሺህ 380 ዩኒት ደም መለገሳቸውን የነቀምቴ ደም ባንክ አገልግሎት አስታውቋል።
.
.
የመልካም አስተዳደርና የሥራ  አጥነት መሠረታዊ ጥያቄዎች በፍጥነት ለመመለስ የሚያግዝ የ60 ቀናት ዕቅድ ተዘጋጅቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ተናግረዋል።
.
.
ሰሞኑን በድሬዳዋ በተፈጠረው ሁከትና ነውጥ #በማራገብ ሂደት #ፖሊስ እና #አድማ_በታኝ አሉበት፤ ይህም በፖሊስ ውስጥ መሠረታዊ ሪፎርም እንደሚያስፈልግ ያመለክታል ተብሏል።
.
.
15ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በዛሬው ዕለት በጂቡቲ ተጀምሯል፡፡
.
.
ትናንት በሶማሌ ክልል መዲና- ጅግጅጋ የሃይማኖት ክብረ በዓልን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።
.
.
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው #በኔዘርላንድ የሚገኙ ኩባንያዎችን ጎብኝተዋል።
.
.
የኢትዮጵያ #ጉብኝታቸዉን አጠናቀዉ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በዝግጅት ላይ ያሉት የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የሚበሩበት አዉሮፕላን የቴክኒክ #እክል ገጥሞት መዘግየቱ ተሰምቷል።
.
.
ከአዲስ አበባ ወደ ነቀምት በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 11 ሺህ ሊትር ነዳጅ መያዙን የኢሉገላን ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
በአማራ ክልል በአምሀራ ሳይንት ወረዳ በአጅባር ከተማ በተቀሰቀሰ #ተቃውሞ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ማቋረጣቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
.
.
ከጥረት ኮርፖሬት የሃብት ምዝበራ ጋር በተያያዘ የአምባሰል ንግድ ስራዎች ስራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ #ምትኩ_በየነን ጨምሮ አምስት ሰዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
.
.
የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያና ዩጋንዳ የፖሊስ አመራሮችና አቃቤ ሕጎች የሶስት ቀናት አውደጥናትን ዛሬ #በኤርትራ_አስመራ ተጀምሯል፡፡
.
.
በአለም ላይ ያለውን የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ጭማሪን ግምት ውስጥ በማስገባት እና በህዳር ወር ተደረገው ዋጋ #ማስተካከያ ዝቅተኛ በመሆኑ፥ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ #መጠነኛ_ጭማሪ ማድረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምንጭ፦ etv፣ fbc፣ የጀርመን ራድዮ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ ኢዜአ፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

"ሰላም ፀግሽ, የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ እና የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ዉጤት #እንዲስተካከልልን በጠየቅነዉ መሰረት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ደብዳቤ ለዩኒቨሲቲዉ ቢልክም እስካሁን #ተመላልሰን ብንጠይቃቸዉም ምንም አይነት #ማስተካከያ አላደረጉም።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለደሴ ሳፋ ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት የአካባቢ የወል ንግድ ምልክትና እውቅና ተሰጥቷል። የወሎ ጋቢ ደግሞ ከሀምሌ 27/2011 በኃላ እውቅና ሊያገኝ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

#እናመሰግናለን~አቶ እንዳልካቸው አበበ

ቀደም ብሎ የቀረበው መረጃ #የስም_መቀያየር የነበረበት መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን!! /መረጃው ላይ #ማስተካከያ የሰጡት እንዳልካቸው አበበ የወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የብራንዲንግ አስተባባሪ ናቸው። በTIKVAH-ETH ስም እናመሰግናለን!!/ እንደምንጭነት የተጠቀምነው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሲሆን ይህን ማስተካከያ እነሱም እንደሚወስዱ እና መረጃው ላይ ያለውን የስም መቀያየር እንድሚያርሙ እምነት አለን።/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ማስተካከያ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ 'ደጎል አደባባይ' ተብሎ በሚጠራው አካባቢ "ፖሊስ ፈንጂ አመከነ" በሚል የተሰራጨው መረጃ 'ስህተት' መሆኑን ማምሻውን አሳውቋል።

ፖሊስ አረጋግጥኩት ባለው መሰረት ቦታው የነበረ በላስቲክ የተሞላ 'ድራፍት ቢራ' እንጂ 'ፈንጂ' አለመሆኑን ህብረተሰቡ እዲገነዘብ ብሏል።

የአ/አ ፖሊስ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

* ከቲክቫህ አባላት ሁኔታውን በሚመለከት የሰጡት መረጃም ተነስቷል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የግል ተፈታኞችን በተመለከተ የመቁረጫ ነጥብ ፦ - በተፈጥሮ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ። - በማህበራዊ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ። ከኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (#MinistryoSHE) የመቁረጫ ነጥብን በተመለከተ የተላከልንን ዝርዝር መግለጫ ከላይ…
#ማስተካከያ

ትላንት ይፋ በተደረገው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመቁረጫ ነጥብ ላይ የተደረገ ማስተካከያ (መስማት ለተሳናቸው እና ለአይነስውራን) እንደሚከተለው ቀርቧል።

ተፈጥሮ ሳይንስ ፦

- መስማት ለተሳናቸው ወንድ ተማሪዎች 275 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

- መስማት ለተሳናቸው ሴት ተማሪዎች 270 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

ማህበራዊ ሳይንስ ፦

- መስማት ለተሳናቸው ወንድ ተማሪዎች 270 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

- መስማት ለተሳናቸው ሴት ተማሪዎች 265 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

- ለአይነስውራን ወንድ ተማሪዎች 240 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

- ለአይነስውራን ሴት ተማሪዎች 235 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

መረጀውን ያገኘነው ከ #MoSHE ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ከ4,000 በላይ ሴቶች ተደፍረዋል ” - የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር የኢትዮጵያ ሴቶች ማኀበር ሴቶች ላይ እየደረሱ ናቸው የተባሉ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን በተመለከተ በየክልሉ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን በመጋበዝ ትላንት ረቡዕ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በዚህም ላይ ከተገኙት ባለድርሻ አካላት መካከል የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር አንዱ ነው። በአማራ ክልል በ “ፋኖ”…
#Amhara

“ ' 4 ሺህ ሴቶች ተደፍረዋል ' በሚል ያልተረጋገጠ ሀሳብ አንስተዋል ” - ወ/ሮ ሁሉአየሽ አወቀ

የኢትዮጵያ ሴቶች ማኀበር ፤ ሴቶች ላይ እየደረሱ ናቸው የተባሉ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን በተመለከተ በየክልሉ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን በመጋበዝ ባለፈው የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ እንደነበርና ቲክቫህ ኢትዮጵያም መረጃ ማጋራቱ ይታወሳል።

በወቅቱ የአማራ ሴቶች ማኀበርን የወከሉት ወ/ሮ በላይነሽ ሽባባው ስለሴቶች በአማራ ክልል ያለውን ሁኔታ ለተሳታፊዎችና ኃላፊዎች ገለጻ ሲያደርጉ፣ “ አማራ ክልል ራሱ የበፊቱን እንኳን ትተነው አሁን በሚስተዋለው ግጭት ብቻ ከ4,000 በላይ ሴቶች #ተደፍረዋል ” ሲሉ ገልጻ አድርገው ነበር።

ይህንንም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዘግቦት እንደነበር ይታወሳል።

ሆኖም የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ሁሉአየሽ አወቀ፣ ዘገባው ከተሰራ በኋላ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ የወ/ሮ በላይነሽን ገለጻ መሠረት በማድረግ የተዘገበውን ዜና ጠቅሰው፣ “ የእናንተ ስህተት አይደለም በእርግጥ የልጆቷ ስህተት ነው ” ብለው ዘገባው #ማስተካከያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል።

ወ/ሮ በላይነሽ በስብሰባው ላይ ያደረጉት ገለጻ የድምጽ ቅጅ እንደገና ሲረጋገጥ፣ “ 4 ሺህ ሴቶች ተደፍረዋል ” የሚል ሆኖ እያለ፣ መረጃውን የት እንዳገኙት እንዲገልጹ የአማራ ሴቶች ማኀበር ሲጠይቃቸው፣ “ ‘4 ሺህ የተባለው እንደ ኢትዮጵያ የቀረበ እንጂ እኔ አላልኩም፣ 400 ነው ያልኩት " ሲሉ ለመካድ እንደሞከሩ ያስረዱት ም/ዳይሬክተሯ፣ “ 400 ከየት አመጣሽ ? ሲባል ‘ከሴቶች ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ ሲባል ሰምቼ ነው’ የሚል ሀሳብ ነው ያመጣች ግን 400ም የእኛ መረጃ አይደለም ” ብለዋል።

አክለው “ የ6 ወራት ሪፓርታችንም ‘ፆታዊ ጥቃት ደረሰብን’ ብለው ተቋማችን ድረስ የመጡ 4 ሴቶች ናቸው። እነዚያን ሴቶችም ሁለቱን ሰጥተናል። ሁለቱን ከፓሊስ ጋ ሁነን ገና በሂደት ላይ ያለ ጉዳይ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ አንድ ሰው ከአንድ ተቋም ሲላክ ታምኖበት፣ ዘርፉን ያውቀዋል ተብሎ ነውና የሚላከው ባለሙያዋ የተናገረችው ስህተት መሆኑን እንዴት ነው የምታረጋግጡልኝ ? የሚል ጥያቄ ለም/ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሁሉአየሽ አቅርቧል።

“ እውነት የምነግርህ እኔ ምክትል ዳይሬክተር ነኝ ፤ ልጅቷ ፕላንድ የሚባል ፕሮጀክት አለ የእርሱ አስተባባሪ ነች ” ያሉት ም/ ዳይሬክተሯ፣ “ ዙሮ ዙሮ ግን እርግጠኛ ሆኘ የምነግርህ ክልሉ ያለበት ሁኔታ ይታወቃል። ቁጥሩ ከዚህ በላይ ሊሆንም ይችላል፣ ሊያንስም ይችላል፣ ስትሰበስበው ነው የምታገኘው ” ሲሉ አስረድተዋል።

ተቋማቸው መልዕክቱን በሰነድ መልኩ እንዲልክ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጠይቀው ምክትል ዳይሬኮተሯ ፈርመው የላኩት ደብዳቤ ፦

- " ወ/ሮ በላይነሽ ሽባባው ' በክልሉ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት 4,000 ሴቶች ተደፍረዋል ' የሚል ያልተረጋገጠ ሀሳብ አንስተዋል " ይላል።

- ክልሉ በዚህ ወቅት በግጭት ላይ በመሆኑ በሴቶች ላይ የተለያዩ ጥቃቶች እንደሚፈጸሙ ቢገመትም ተቋሙ ግን ታች ድረስ ወርዶ መረጃ ለመሰብሰብ ባለው ግጭት ምክንያት ምቹ ሁኔታ ስለሌለና ኢንተርኔት በመዘጋቱ ምክንያት መረጃዎችን ሰብስቦ ማረጋገጥ እንዳልተቻለ ይገልጻል።

* የተባለው መረጃው በተቋሙ ውስጥ እንደሌለ፤ ምቹ ሁኔታን ሲገኝ ታች ወርዶ ያረጋገጥነውን መረጃ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደሚያሳውቅ ያመለክታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያደረጉት ገለጻ ስህተት እንደሆነ የተነገረላቸው ወ/ሮ በላይነሽን በድጋሚ ማብራሪያ እንዲሰጡ ያደረገው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

#AATikvahFamily

@tikvahethiopia