" ጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የተከሰተው ውጥረት እና ግጭት ከመባባሱ በፊት አስቸኳይ ምላሽ ይሻል " - ኢሰመኮ
ኢሰመኮ አሰባሰብኩ ባለው መረጃ እና አነጋገርኳቸው ያላቸው የአስተዳድር መዋቅር ጠያቂዎች እንደገለፁት በጋሞ ዞን ፣ አርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ሥር የሚገኙ ፦
* ኤልጎ
* ወዘቃ
* ደምብሌ እና ጫሞ 01 የተባሉ አራት ቀበሌዎች ከጋሞ ዞን በመውጣት ልዩ ወረዳ ሆነው ለመደራጀት በተለያየ ጊዜ ጥያቄ ሲያነሱ ቆይተው ነበር።
በተለይ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ ውዝግቡ እየተባባሰ እንደመጣ ገልጸዋል።
ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ አቅራቢዎች ምን አሉ ?
በተለያዩ መድረኮችና ወቅቶች በሚያነሱት በዚህ የአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ ምክንያት እና በ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ፣ ለሁለቱም ም/ቤቶች የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲን በመምረጣቸው ምክንያት የጋሞ ዞን አስተዳደር በተለያየ መንገድ ስልታዊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸመብን ነው ብለዋል።
ኢሰመኮ ስለጉዳዩ የዞኑን አስተዳደር መጠየቁን ገልጾ አስተዳደሩ ፤ የመዋቅር ጥያቄ አቅራቢዎች የአካባቢ ምርጫ ተካሂዶ አካባቢውን ለማስተዳደር ሕግን በተከተለ መንገድ ምርጫውን በማሸነፍ ሥልጣን ሳይረከቡ መንግሥት ቀበሌዎቹን ማስተዳደር የለበትም በሚል ምክንያት በአካባቢው የመንግሥት መዋቅር እንዲፈርስና አካባቢው እንዳይረጋጋ እያደረጉ ነው ብሏል።
ከጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ አቅራቢዎች እና በጋሞ ዞን አስተዳደር መካከል ያለው አለመግባባት ውጥረት እየጨመረ ቆይቶ፣ ጥቅምት 11/2016 ዓ/ም አንድ በወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በኤልጎ ቀበሌ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር በዋለበት ሂደት እና በቁጥጥር ሥር በነበረበት ወቅት በተፈጸመበት ድብደባ #መሞቱን ተከትሎ ሁኔታው እጅግ ተባብሶ ወደ ግጭት አምርቷል።
የጋሞ ዞን ፖሊስ አስተዳደር ከግለሰቡ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እያደረገ መሆኑን ለኢሰመኮ አስረድቷል፡፡
ሆኖም ከጥቅምት 11/2016 ክስተት ጀምሮ በተለያዩ ሰዎችና ቡድኖች በተፈጸሙ ጥቃቶች የነዋሪዎች የሙዝ እርሻዎች እና በመንግሥት የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ንብረት ማውደም ጉዳት ደርሷል።
ከኅዳር 16/2016 ጀምሮ በተለያዩ ጊዜዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት በግለሰቦች እና በጸጥታ አካላት በተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች ለጊዜው ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቀ ነዋሪዎች እና የጸጥታ አባላት ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
በርካታ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡
አሁንም የቀጠለው ውጥረት፣ ግጭትና እየተወሰዱ ያሉ የኃይል እርምጃዎች በነዋሪዎች ላይ ተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳያስከትል ኮሚሽኑ ያለውን ሥጋት ገልጾ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopia