TIKVAH-ETHIOPIA
አውሮፓ ህብረት ምን አለ ? የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እና በራዝ ገዟ ሶማሊላንድ መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት በተመለከተ አጭር መግለጫን ትላንት ምሽት አውጥቶ ነበር። በዚህ መግለጫው፤ እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የኢትዮጵያ የባህር በር አገልግሎት (በሊዝ) ማግኘት የሚያችላትን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል…
#ኢጋድ #ሶማሊያ
ዛሬ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚህም መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዲላፕሎማሲው መስክ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት መካከል እያታየ ያለው ሁኔታ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።
ኢጋድ ሁኔታውን በንቃት እየተከታተለ መሆኑን እና በቀጠናው መረጋጋት ላይ ያለውን ተፅእኖ እንደሚገነዘብ አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሁኔታዎችን በሰላማዊ እና በመግባባት መንፈስ ለመፍታት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ዶክተር ወርቅነህ በመግለጫቸው በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል ስለተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ያነሱት ነገር የለም።
የሶማሊያ መንግሥት የዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ እንዳበሳጨው ለመረዳት ተችሏል።
የሶማሊያ መንግሥት " የመግለጫው ሃሳብ ለኢትዮጵያ ያደላ ነው " በማለት ዶ/ር ወርቅነህ በአስቸኳይ ይቅርታ እንዲጠይቁ፣ የይቅርታ መግለጫም በማውጣት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስዱ ብሏል።
ሶማሊያ ፤ የኔ አንድ ግዛት ናት በምትላት ሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ መካከል የተረፈመው ስምምነት ያበሳጫት ሲሆን ስምምነቱ የግዛት አንድነቴን እና ሉዓላዊነትን የጣሰ ነው በማለት እየተቃወመች ትገኛለች።
(የሁለቱም መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

Photo
#ኢትዮጵያ🇪🇹
ኢትዮጵያ ምን አለች ?
" ... ምንም እንኳን ሶማሊላንድ እስካሁን የተሟላ ዕውቅና ባታገኝም የወደብ አገልግሎትና ልማትን ጨምሮ ከአንዳንድ ሀገራት ጋር ስምምነት ፈርማለች።
ከዚህ ቀደም በርበራ ላይ ለኢትዮጵያ የ19 በመቶ ድርሻ እንዲኖራት ይፈቀድ የነበረ የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሞ እንደነበርም ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅት ሌሎች ሀገራት ተመሳሳይ ሂደት እየተከተሉ መሆኑም ይታወቃል። ይሄ ሲሆን የተሰማ ኮሽታም ሆነ ቅሬታ አልነበረም።
ኢትዮጵያ የወታደራዊ ቤዝና ኮሜርሻል ማሪታይም አገልግሎት በሰጥቶ መቀበልና በኪራይ ለማግኘት የተፈራረመችው የመግባቢያ ሰነድና ሂደትም በመሠረቱ አንድና ያው ነው። "
(ሙሉ መግለጫ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/83987)

#Update የሶማሊላንድ ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ። የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ምክትል ፕሬዜዳንት አብዲራህማን ሳይሊች የሶማሊላንድን ካቢኔ ለነገ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። ይኸው የተጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ በሶማሊያ መንግሥት ካቢኔ እና የፌዴራል ምክር ቤቶች ለተደረገው አስቸኳይ ስብሰባ #ምላሽ የሚሰጥ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ንግድ እና ቱሪዝም ሚኒስትር አብዲረሺድ ኢብራሂም ያገኘው…
#Update
ራስ ገዟ ሶማሊላንድ የሶማሊያ መንግሥትን አስጠነቀቀች።
ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ለማደናቀፍም ይሁን ለመቃረን የሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ ይሁን አካል ላይ እርምጃ ወስዳለሁ ብላለች።
የራስ ገዟ ሶማሌላንድ" የሚኒስትሮች ምክር ቤት " ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ነበር።
ከስብሰባው በኃላ ባወጣው ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ ፦
- ምክር ቤቱ እ.ኤ.አ. ጥር 1/2024 በአዲስ አበባ የተፈርመውን የመግባቢያ ስምምነት በሙሉ ድጋፍ አፅድቆ እንደተቀበለውና እንደሚያደንቅ ገልጿል።
- ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ " ለሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " ሉዓላዊነት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያ ሀገር በመሆኗ ምስጋናውን አቅርቧል።
NB. (የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ ስምምነቱ በሂደት ሶማሌላንድ ዕውቅና ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት በጥልቀት አጢኖ አቋም እንደሚወስድበት መግለፁ ይታወቃል)
- ምክር ቤቱ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሶማሌላንድ ምድሯን፣ አየሯን እና ባህሯን ሙሉ በሙሉ የምትቆጣጠር ነፃ ሀገር ናት ብሏል። በተጨማሪም " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " ሕገ መንግሥት መሠረት " የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " ከማንኛውም ብሔራዊ ጥቅሟን ከሚያስጠብቅና ከሚጣጣም አካል ጋር ስምምነት የማድረግ ሥልጣን አላት ብሏል።
- ምክር ቤቱ ፤ " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እና በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግስት መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት አስመልክቶ የሶማሊያ መንግስት የሰጠውን መግለጫ እና ድርጊት በጽኑ አውግዟል። የሶማሊያ መንግስት በመሰል ጉዳዮች ከመሳተፍ እንዲቆጠብ አስጠንቅቋል።
- ምክር ቤቱ ከሶማሊያ የወጡት መግለጫዎች " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እና በሶማሊያ መንግስት መካከል ከዚህ ቀደም የተደረጉ ስምምነቶችን የሚጻረር መሆኑን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይወቅልኝ ብሏል።
- ምክር ቤቱ ፤ " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እና በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ መንግስታት መካከል የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ለማደናቀፍ ወይም ለመቃወም ለሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ ወይም አካል ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
- ምክር ቤቱ የሶማሌላንድ ህዝብ ለተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ላደረገው ደማቅ አቀባበል እና ድጋፍ ያለውን አድናቆት ገልጿል።
- ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክን አርአያነት በመከተል በዓለም ዙሪያ ያሉ መንግስታት " ለሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እውቅና ለመስጠት ድፍረት እና ጥበብ እንዲያሳዩ አሳስቧል። ይህን መሰሉ ዕውቅና ለአህጉራዊ መረጋጋት፣ ለደህንነት እና ለአፍሪካ ቀንድ የዴሞክራሲ መርሆች መሻሻል አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ አጽንኦት ሰጥቷል።
ℹ ሶማሊላንድ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት እራሷን እንደ አንድ ነፃ ሀገር የምትቆጥር ሲሆን የራሷ ህገመንግስት፣ የመገበያያ ገንዘብ፣ የፀጥታ ኃይል፣ ፓስፖርት፣ ራሱን የቻለ የፖለቲካ ስርዓት አላት። እስከዛሬ ግን ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘት አልቻለም። ሶማሊያ እንደ አንድ የራሷ ግዛት ነው የምታያት።
#ቲክቫህኢትዮጵያ

#DStvEthiopia
እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የገና በዓልን ከወዳጅ ዘመድ ጋር ሰብሰብ ብለን ‘እያየሁ ነው … አትቀይሩት’ የሚያስብል
የመዝናኛ አማራጭ ያጣጥሙ!
መልካም በዓል!
#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው

" ጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የተከሰተው ውጥረት እና ግጭት ከመባባሱ በፊት አስቸኳይ ምላሽ ይሻል " - ኢሰመኮ
ኢሰመኮ አሰባሰብኩ ባለው መረጃ እና አነጋገርኳቸው ያላቸው የአስተዳድር መዋቅር ጠያቂዎች እንደገለፁት በጋሞ ዞን ፣ አርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ሥር የሚገኙ ፦
* ኤልጎ
* ወዘቃ
* ደምብሌ እና ጫሞ 01 የተባሉ አራት ቀበሌዎች ከጋሞ ዞን በመውጣት ልዩ ወረዳ ሆነው ለመደራጀት በተለያየ ጊዜ ጥያቄ ሲያነሱ ቆይተው ነበር።
በተለይ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ ውዝግቡ እየተባባሰ እንደመጣ ገልጸዋል።
ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ አቅራቢዎች ምን አሉ ?
በተለያዩ መድረኮችና ወቅቶች በሚያነሱት በዚህ የአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ ምክንያት እና በ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ፣ ለሁለቱም ም/ቤቶች የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲን በመምረጣቸው ምክንያት የጋሞ ዞን አስተዳደር በተለያየ መንገድ ስልታዊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸመብን ነው ብለዋል።
ኢሰመኮ ስለጉዳዩ የዞኑን አስተዳደር መጠየቁን ገልጾ አስተዳደሩ ፤ የመዋቅር ጥያቄ አቅራቢዎች የአካባቢ ምርጫ ተካሂዶ አካባቢውን ለማስተዳደር ሕግን በተከተለ መንገድ ምርጫውን በማሸነፍ ሥልጣን ሳይረከቡ መንግሥት ቀበሌዎቹን ማስተዳደር የለበትም በሚል ምክንያት በአካባቢው የመንግሥት መዋቅር እንዲፈርስና አካባቢው እንዳይረጋጋ እያደረጉ ነው ብሏል።
ከጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ አቅራቢዎች እና በጋሞ ዞን አስተዳደር መካከል ያለው አለመግባባት ውጥረት እየጨመረ ቆይቶ፣ ጥቅምት 11/2016 ዓ/ም አንድ በወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በኤልጎ ቀበሌ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር በዋለበት ሂደት እና በቁጥጥር ሥር በነበረበት ወቅት በተፈጸመበት ድብደባ #መሞቱን ተከትሎ ሁኔታው እጅግ ተባብሶ ወደ ግጭት አምርቷል።
የጋሞ ዞን ፖሊስ አስተዳደር ከግለሰቡ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እያደረገ መሆኑን ለኢሰመኮ አስረድቷል፡፡
ሆኖም ከጥቅምት 11/2016 ክስተት ጀምሮ በተለያዩ ሰዎችና ቡድኖች በተፈጸሙ ጥቃቶች የነዋሪዎች የሙዝ እርሻዎች እና በመንግሥት የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ንብረት ማውደም ጉዳት ደርሷል።
ከኅዳር 16/2016 ጀምሮ በተለያዩ ጊዜዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት በግለሰቦች እና በጸጥታ አካላት በተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች ለጊዜው ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቀ ነዋሪዎች እና የጸጥታ አባላት ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
በርካታ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡
አሁንም የቀጠለው ውጥረት፣ ግጭትና እየተወሰዱ ያሉ የኃይል እርምጃዎች በነዋሪዎች ላይ ተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳያስከትል ኮሚሽኑ ያለውን ሥጋት ገልጾ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርቧል።

" ጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የተከሰተው ውጥረት እና ግጭት ከመባባሱ በፊት አስቸኳይ ምላሽ ይሻል " - ኢሰመኮ ኢሰመኮ አሰባሰብኩ ባለው መረጃ እና አነጋገርኳቸው ያላቸው የአስተዳድር መዋቅር ጠያቂዎች እንደገለፁት በጋሞ ዞን ፣ አርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ሥር የሚገኙ ፦ * ኤልጎ * ወዘቃ * ደምብሌ እና ጫሞ 01 የተባሉ አራት ቀበሌዎች ከጋሞ ዞን በመውጣት ልዩ ወረዳ ሆነው ለመደራጀት በተለያየ…
" ዞናችን ሰላም ነው ! ...ሰብዓዊ መብት የሚባለው መቼ መጥቶ አጣራ ? " - የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ
የኢሰመኮን መግለጫ በተመለከ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት የጋሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አባይነህ አበራ " ኢሰመኮ ያወጣው ሪፖርት መሰረት የሌለውና በመረጃ ያልተደገፈ " ሲሉ አጣጥለዋል።
" እንደዛ አይነት ነገር (ኢሰመኮ በመግለጫው ያነሳቸው ጉዳዮች) ጋሞ ዞን ውስጥ የለም። ዞናችን ሰላም ነው ፤ አይደለም ሰላም ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ሰላም የሚያስተምር አካባቢ ነው። እንዳዛ አይነት ችግር የለም። " ብለዋል።
" መንግሥት ኦፕሬሽን ሲጀምር ከምዕራብ ጉጂ ሸሽተው የመጡ የኦነግ ሸኔ አባላት እና ከነሱ ጋር የተደራጁ አሉ ፤ እነሱን መንግሥት እያሰሳቸው ነው ከዛ ውጭ ምንም አይነት ችግር የለም ፤ እንደዞናችን አንድም ችግር የለም " ሲሉ ተደምጠዋል።
ኢሰመኮ መግላጫውን ከማውጣቱ በፊት ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖችን፣ የአስተዳደር አካላትን ፣ የፀጥታ አካላትን ማነጋገሩን ቢገልፅም የዞኑ ምክትል አስታዳዳሪ ግን ማንኛውም የሰብዓዊ ተቋም እኛ ጋር አልመጣም አልጠየቀንም ብለዋል።
" ሰብዓዊ መብት መቼ መጥቶ አጣራ ? ምንም ያጣራውም የተወያየው ነገር የለም። ሰብዓዊ መብቶች እራሳችሁ ወርዳችሁ አጣርታችሁ ነው ያወጣችሁት ? ማንኛውም የሚያጣራ አካል መንግሥትን ያገኛል ከዛ ወርዶ ያጣራል ፤ ምላሽ ይሰጣል አልሰጥም ካለም በራሱ ይሄዳል። እስከዛሬ ወደኛ የመጣ የሰብዓዊ መብትም የለም ማንም አካል የለም። ከሰሚ ሰሚ የአካባቢውን ገፅታ ለማበላሸት የሚደረግ ካልሆነ በስተቀር እንደዛ የሚባል ችግር በዞናችን የለም ዞናችን ሰላም ነው። አሁንም ድሮም ወደፊትም ሰላም ይሆናል። ከፀጥታ ጋር የተያያዘ ችግር የለም " ብለዋል።
በዞኑ አርባምንጭ ዙሪያ በልዩ ወረዳ እንዋቀር የሚሉ ነዋሪዎች የሉም ወይ ? ተብለው የተጠየቁት አቶ አባይነህ ፤ " ልዩ ወረዳ መጠየቅ የሚችል መጠየቅ ይችላል። ህገመንግስታዊ መብት ነው። ሰው ይህን ስለጠየቀ አይታሰርም። አይደለም አሁን በኢህአዴግ ጊዜም አልታሰረም። አሁን ደግሞ ብልፅግና ሰው ላይ ነው የሚሰራው መነሻውም መድረሻውም ሰው ነው ዜጋ ተኮር ነው ፤ ዜጎች የሚጠይቁትን በህጋዊ መንገድ ምላሽ ይሰጣል። yes/no ብሎ ይመልሳል እንጂ አያስርም " ብለዋል።
ምክትል አስተዳዳሪው ቃላቸውን የሰጡት ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያሳውቃል።

" ዞናችን ሰላም ነው ! ...ሰብዓዊ መብት የሚባለው መቼ መጥቶ አጣራ ? " - የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ የኢሰመኮን መግለጫ በተመለከ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት የጋሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አባይነህ አበራ " ኢሰመኮ ያወጣው ሪፖርት መሰረት የሌለውና በመረጃ ያልተደገፈ " ሲሉ አጣጥለዋል። " እንደዛ አይነት ነገር (ኢሰመኮ በመግለጫው ያነሳቸው ጉዳዮች) ጋሞ ዞን ውስጥ…
#አርባምንጭዙሪያ
የተለያዩ ጥያቄዎችን አንግበዉ ጫካ የገቡ አካላት በተደጋጋሚ በሰላም እጅ አንዲሰጡ ቢጠየቁም መቀበል አልፈለጉም ሲል የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በአርባምንጭ ዙሪያ የሚስተዋለዉ ግጭት የሰብአዊና ቁሳዊ ጥፋት እያስከተለ ለአመታት ቢዘልቅም አሁንም መፍትሄ እንዳልተገኘለትና ችግሩ የአካባቢዉን ማህበረሰብ የእለትተእለት እንቅስቃሴ እያስተጓጎለ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከነዋሪዎች ተረድቷል።
በዚህ ጉዳዩ ላይ በርካታ ጥያቄዎችና ጥቆማዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መቅረቡን ተከትሎ ሁኔታዉን ለማጥራት በቦታው ያለዉን የጸጥታ አካል ለማነጋገር ተሞክሯል።
የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሰላም መስተካከል ስለምን አልቻለም ? በሚል ጥያቄ የቀረበላቸዉ የወረዳዉ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበዉ አዳል ፤ ችግሩን ለመፍታት መንግስት ያቀረበዉ የሰላም ጥሪ በአካባቢዉ ችግር ሲፈጥሩ የነበሩ አካላት እንዳልተቀበሉትና ይባሱኑ በአካባቢዉ ሰላም ለማስከበር በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ጥቃት መፈጸማቸዉን ይገልፃሉ።
በቅርቡ በደቡብ ክልል አድማብተና ሀይል ላይ ጥቃት ሊፈጽሙ መሞከራቸዉንና የተወሰነ ጉዳት ቢያስከትሉም በተወሰደባቸዉ የመልስ ምት ተበታትነው መሸሻቸዉን የሚገልጹት ኮማንደር ክበበው ይህ ህዳር 19/2016 ከተፈጸመ ወዲህ የጸጥታ አካሉ አካባቢዉን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ አካባቢዉን ወደሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን ያነሳሉ።
አሁን ላይ ከማህበረሰቡ ጋር ጠንካራ ዉይይት እየተደረገ መሆኑንና ጫካ ገብተዉ ችግር የሚፈጥሩ አካላትም እጃቸዉን በሰላም እንዲሰጡ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሁሉ ስምምነት ላይ መደረስ እንደተቻለ አመልክተዋል።
በአካባቢው የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ነዋሪዎች ያሉ ሲሆን ችግሮች ሰፍተዉ በአካባቢው የተዘረጋዉን መዋቅር አስካለመቀበልና ከጸጥታ አካላት ጋር እስከመታገል ተደርሷል።
በዚህም የተማረረዉ የአካባቢዉ ህዝብ የችግሩን መጠናከር ተከትሎ ወደአካባቢዉ ከተሞች መሸሽ መጀመሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ ቤተሰብ አባል የላከው ዘገባ ያስረዳል።

የሌለ ነገር የለም!
**
የተሻሻለው የሲቢኢ ብር መተግበሪያ በርካታ አዲስ ነገሮችን ይዟል፡፡
• በርካታ መተግበሪያዎችን በአንድ ላይ የያዘ
• የነዳጅ ክፍያ በቀላሉ መፈፀም የሚያስችል
• የአገልግሎት፣ የመብራት፣ የኤሌክትሪክ፣ የቴሌኮም፣ የትራፊክ ቅጣት ሌሎችንም በርካታ ክፍያዎች በቀላሉ መፈፀም የሚያስችል
• ክፍያዎችን ማቀድ የሚያስችል
• ለተለያዩ ሁነቶች መግቢያ ዲጂታል ትኬት በቀላሉ መሸጥ የሚያስችል
• የትምህርት ቤት ክፍያዎችን መክፈል የሚያስችል
• ወደሁሉም ባንክ ገንዘብ መላክ የሚያስችል
• ለእያንዳንዱ የገንዘብ እንቅስቃሴ ዲጂታል ደረሰኝ ያለው
• የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያዎን (ፋይዳ) ማግኘት የሚችሉበት
• ለአጠቃቀም ቀላል...
**
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለመጫን ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

ሚና ፈርኒቸር .. ከዘመኑ ጋር 🤌
👉KSA4O:-ይህን code ይዞ ለመጣ ደንበኛ ልዩ ቅናሽአዘጋጅተናል🎄
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ይቀላቀሉንን
CLICK HERE ‼️https://t.iss.one/minafurniture
☎️ 0932325151
👉KSA4O:-ይህን code ይዞ ለመጣ ደንበኛ ልዩ ቅናሽአዘጋጅተናል🎄
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ይቀላቀሉንን
CLICK HERE ‼️https://t.iss.one/minafurniture
☎️ 0932325151
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #ባለበት ይቀጥላል ተብሏል። የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። ቀደም ሲል የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ? - ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም - ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75…
#እንድታውቁት
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል።
ሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በታህሳስ ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ?
- ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
- ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ16 ሳንቲም ነው።

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ማለፊያ ነጥብ ማምጣት ላልቻሉ ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት (Remedial) ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ወስኗል።
በሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ታህሳስ 24/2016 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የማካካሻ ትምህርት ለሚሰጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከው ደብዳቤ ፤ የማካካሻ ትምህርቱ ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሰጥ ያዛል።
በዚህም ተቋማቱ ከጥር 1 ጀምሮ በቀሩት ወራት ትምህርቱን ውጤታማ በሆነ መንገድ መስጠት እንዳለባቸው ተገልጿል።
Via @tikvahuniversity