TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የግብረሰዶም ድርጊትን የተላመዱና የሚለማመዱ በውጭ የሚኖሩ #ብሩንዲያውያን ወደ ሀገር ቤት እንዳይመለሱ " - የቡሩንዲው ፕሬዜዳንት

ቡሩንዲ በሀገሯ ግብረሰዶምን በፍፁም እንደማትቀበል አሳወቀች።

የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ቡሩንዲ ሀገራቸው ግብረሰዶምን በፍፁም እንደማትቀበል አሳውቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ በጋዜጠኞች ተጠይቀው ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከግብረሰዶም ጋር ታያይዞ " ሃያላኑ ሃገራት ለአፍሪካ ሀገራት እርዳታ እየለገሱ ለግብረሰዶማውያን መብት የመስጠት ግዴታን የሚያስቀምጡ ከሆኑ እርዳታቸውን እዛው መያዝ አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ግብረሰዶም በቡሩንዲ ወንጀል ነው ያሉት ፔሬዝዳንቱ ይህ ወንጀል እስከ ሁለት አመት እስር እንደሚያስቀጣ ገልፀዋል።

" በግሌ እንደዚህ አይነት ሰዎችን (ግብረሰዶሞችን) ቡሩንዲ ውስጥ ካየን ስታዲየም ውስጥ አስገብተን በድንጋይ መውገር አለብን ብዬ አስባለሁ፤ ይህንን ለሚያደርጉ ደግሞ ሃጢያት አይሆንም " ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ በአፍሪካ አህጉር ከ30 በላይ ሀገራት ይህን ድርጊት የማይቀበሉ እና ወንጀል መሆኑን ያስታወሱ ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በማጣቀስ " አምላክ ግብረሰዶምን ይቃወማል " ብለው በሀገራቸው ድርጊቱን በፍፁም እንደማይቀበሉት አስረድተዋል።

የዚህ አይነት የድርጊት መብት እንዲከበር ከምዕራባውያን ሀገራት ግፊት የሚደረግበትን መንገድ አስመልክቶ የተጠየቁት ፕሬዝዳንቱ ይህንን የሚመርጡ ሰዎች ወደ ምዕራቡ ዓለም ሄደው እነዚያን ልማዶች እንዲያደርጉ አስጠንቅቀው ድርጊቱ ከሀገሪቱ እና ከአህጉሪቱ ባህል እና እሴት ውጪ በመሆኑ በጭራሽ በሀገራቸው እንማይፈቀድ አስጠንቅቀዋል።

" ሰይጣንን የመረጡ እና የግብረሰዶም ድርጊትን የተላመዱና የሚለማመዱ በውጭ የሚኖሩ #ብሩንዲያውያን ወደ ሀገር ቤት እንዳይመለሱ " ሲሉም አክለዋል።

በግብረሰዶማዊነት ጉዳይ በሌሎች በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የተጠናከረ ህግ እያወጡ ሲሆን የጋና የፓርላማ አባላት ድርጊቱ በሶስት አመት እስራት የሚያስቀጣ ህግ እና የድርጊቱ ተከራካሪ ሆነው ዘመቻ የሚያደርጉ ሰዎችን እስከ 10 አመት እስራት ሊያስቀጣ የሚችል ህግ እያወጡ መሆኑ ተዘግቧል።

ኡጋንዳም ከእድሜ ይፍታህ እስራት እስከ #ሞት ድረስ የሚያስቀጣ ጠንካራ ህግ ማውጣቷ የሚዘነጋ አይደለም።

Via @TikvahethMagazine
January 1,2024

በግሪጎሪያን ቀን አቆጣጠር አዲሱ ዓመት 2024 ገብቷል።

እጅግ በርካታ ሀገራት አዲሱን ዓመት 2024 እየተቀበሉ ይገኛሉ።

ከዓለማችን ሀገራት መካከል የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር ያላት #ኢትዮጵያ በግንባር ቀደምትነት የምትነሳ ሲሆን ሀገራችን የግሪጎሪያን ቀን አቆጣጠርን እንደ ዘመን መለወጫ አትጠቀምም።

የ13 ወራት ፀጋ ባለቤቷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት የዘመን አቆጣጠሯ መለየቱ ብቻ ሳይሆን የራሷ የሆኑ ባህሎች፣ ቋንቋዎች ፣ ፊደል፣ ጥበብ ያለባት ሀገር ናት።

@tikvahethiopia
" በብዛት የምንቀጥረው የእኛ ልጆች የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ከዩኒቨርስቲ የሚመጡ ግራጁየቶችን ነው " - የአንድ ባንክ ባለስልጣን

" ጉዳዩ የሚታወቅ ነው እኮ " - የኢትዮጵያ  ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

የሥራ ቅጥርን በተመለከተ በተለያዩ ተቋማት የሚደረግ ብሔር ተኮር፣ የዘመድ አዝማድና የሙስና ቅጦር ለምሬት እንደዳረጋቸው በርካቶች በተደጋጋሚ እሮሮ ሲያሰሙ ይደመጣሉ።

በተለይ #በባንክ_ቤቶች ይሄው ችግር በሰፊው እንደሚስተዋል መነገር ከጀመረም ሰንበትበት ያለ ቢሆንም ችግሩ መፍትሄ ስላልተቸረው አሁንም እንደቀጠለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረዳት ችሏል።

የአንድ ባንክ ባለሥጣን ባንኩ በዚህ ዓመት አዘጋጅቶት በነበረው የባለአክሲዮኖች ስብስባ የሠራተኛን የቅጥር ሁኔታን በተመለከተ በመርሀ ግብሩ ወቅት ከአንድ ባለአክሲዮን ለቀረበላቸው ጥያቄ ባደረጉት ገለጻ፣ " በብዛት የምንቀጥረው የእኛ ልጆች የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ከዩኒቨርስቲ የሚመጡ ግራጁየቶችን ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ባለስልጣኑ እንዲህ ያሉት በባንኩ ሠራተኞች አገልግሎት አሰጣጥ ክፍተትን በተመለከተ ከአንድ የባንኩ ባለአክሲዮን የቀረበላቸውን ጥያቄን በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት አውድ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
* በብሔር ተኮር ፣
* በሙስና የቅጥር አፈጻጸሞች ዙሪያ ከዜጎች የደረሱት ቅሬታዎች እንዳሉ፣ እንደ ተቋምም በዚሁ ረገድ የሕዝብን እንባ ለማበስ ጉዳዩን አይቶት (ተከታትሎት) እንደሆነ፣ የኢትዮጵያ  ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን ጠይቋል።

አንድ የተቋሙ ከፍተኛ ባለሥልጣን በሰጡን ቃል፣ " ጉዳዩ የሚታይ እኮ አይደለም፣ የሚታወቅ ስለሆነ " ብለዋል።

ከዚህ በፊትም ከሥራ ቅጥር ጋር በተያያዘ በርካታ አቤቱታዎች ወደ ተቋሙ ይመጡ እንደነበር አስታውሰዋል።

" አቤቱታ በተናጠል ሊመጣ ይችላል " ያሉት የተቋሙ ባለስልጣን " ነገር ግን ማስረጃ ስለማይኖር፣ እከሌ በዘመድ ነው የተቀጠረው፣ ገንዘብ ሰጥቶ ነው የተቀጠረው የሚለውን ነገር ኢቪደንስ ስለማይኖር ሰውም አይመጣም " ብለዋል።

" ግን አጠቅላይ ስሩአውት ዘከንትሪ ያለው ትሬንድ ወይ ዘመድ ካለህ፣ ወይ ገንዘብ ካለህ ነው የምትቀጠረው በማስረጃ እንዲህ ነው ለማለት ግን ያስቸግራል " ነው ያሉት ባለሥልጣኑ።

የመፍትሄ አቅጣጫው ምን እንደሆነ ሲጠየቁም፣ " ሲቪል ሰርቪስ ወቅታዊ ሁኔታዎች ይዘውት እንጂ አጠቃላይ በዚህ የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ተከታታይ የሆነ ሥራ እንደሚሰራ፣ እኛም ጠይቀናቸዋል " ብለዋል።

አክለውም፣ " ከዚህ ከአገልግሎቱ አሰጣጥ ጋር፣ ከመልካም አስተዳደር ጉዳይ፣ ከቅጥርም፣ ከእያንዳንዱ የሰው ኃይል ጋር ተያይዞ በቅጡ እየሄደ አይደለም የሚል ሀሳብ አንስተንላቸው እነርሱም ዝግጅት አጠናቀው 'በስድስት ወራት የምንሰራው ሥራ ነው' የሚል ሀሳብ አንስተዋል " ሲሉ አስረድተዋል።

ዘገባውን ያጠናቀረው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዉ ወሰነ-ትምህርት ተማሪዎቻቸውን ለመጥራትና መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸዉን ሙሉ ለሙሉ…
#BDU

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሲጀመር ተማሪዎች ኃላፊነት ለመውሰድም ይዘጋጁ ብሏል።

በአማራ ክልል የሚገኙ 10 የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት 2 ሳምንታት መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ እንደሚጀምሩ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከክልሉ ኮማንድ ፖስት፣ የፀጥታ አደረጃጀቶች፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የ10 ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ፀጥታ አካላት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቶ የውይይቶቹ የመጨረሻው ክፍል ሐሙስ ከተደረገ በኃላ ነው ውሳኔው የተላለፈው።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

- ከመስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተማሪዎችን ለመቀበል ተዘጋጅተን የነበረ ቢሆንም፣ በክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ሳቢያ ተሰናክሏል።

- በእኛ በኩል የዝግጅት ክፍተት የለብንም።

- በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቁጥጥር ሥር የሆነ የፀጥታ ሁኔታ አለ። ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆነም የፀጥታ ሁኔታ አለ። ከእኛ ውጪ በሆነው ጉዳይ ላይ ምንም ማድረግ አንችልም። ምንም ማድረግ ባልቻልንበት ሁኔታ የሰው ልጅ ጠርቼ አንድ መጥፎ ነገር ቢከሰት ምንድነው የምለው ? የሚለውን ተማሪዎችም፣ ወላጅንም ታሳቢ አድርገን ተማምነን ይቆይ የሚል አቋም ስለነበረን በዚህ ምክንያት ነው እስካሁን ቀስ እያልን የመጣነው።

- የመማር ማስተማሩ እንዲጀመር በነበረው ውይይት ሒደት አቅደን የነበረው ተመራቂ ተማሪዎችን ወደ የትምህርት ግቢያቸው ማስገባት ነበር።

- እስካሁን ባለን ልምድ ግጭቶች እዚህም እዚያም ሊቀሰቀሱ ይችላሉ። ቀጣይነታቸው ግን ብዙም አይደለም። አንድ ቀን ወይ ሁለት ቀን መስተጓጎል ሊፈጠር ይችላል ከዚያ ግን ያበቃል።

- ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ተጠርተው ሲመጡ ታሳቢ ማድረግ ያለባቸው ጉዳዮች አሉ ፤ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ዕክሎችን ከግምት በማስገባት ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው።

- ተማሪውም፣ ወላጅም፣ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብም እንደ አገር የሚመለከታቸውም አንድ ላይ ሆነን መደበኛ ትምህርት መጀመር አለብን ብለን ወስነናል።

- የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተቋማቸው ከልደት (ገና) በዓል በኋላ ባሉት ቀናት ለተማሪዎቹ ጥሪ ያደርጋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
አዲስ መኪና የማሸነፍ እድል እንፈልጋለን? M-PESA ላይ በቀላሉ እንመዝገብ እና በM-PESA ግብይቶችን ፈፅመን አዲሱን መኪና የግላችን እናድርግ

የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

አሸናፊ ኮዶችን ከታች በሚገኘው ሊንክ ማግኘት ትችላላቹህ
https://safaricom.et/index.php/faqs

#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ

በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል።

ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡

የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር እና የአጋርነት መግባቢያ ሠነድ በተለያዩ ዘርፎች በቀጣይ ለሚኖራቸው ግንኙነቶች ማዕቀፍ  እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽኅፈት ቤት ይፋ ባደረገው መረጃ አሳውቋል።

የመግባቢያ ሠነዱ ፦
* የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት ዕውን የሚያደርግ ፣
* የባሕር በር አማራጮቿን የሚያሠፋ
* የሁለቱን ወገኖች የፖለቲካ ፣ የዲፕሎማሲ ፣ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናከር ነው ብሏል።

በተጨማሪም ሠነዱ ሀገራቱ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲው ዘርፍ የሚኖራቸውን ግንኙነት የሚጎለብትበትን አካሄድ የሚያካትት መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በሰጥቶ መቀበል መርኅ እና ሀገሪቷ ለጋራ ጥቅም ከጎረቤቶቿ ጋር የመሥራት ፍላጎት እና አቋሟን መልሶ የሚያጸና እንደሆነም አመላክቷል፡፡

ሠነዱ ፤ አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እና ለአፍሪካ ቀንድ ትሥሥር የላቀ ፋይዳ ያለው መሆኑን ጠቁሟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር…
#Update

የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ፤ ዛሬ በነበረው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ፊርማ ወቅት ፤ ኢትዮጵያ ከስምምነቱ በኃላ " ለሶማሌላንድ ነፃ ሀገርነት እውቅና የምትሰጥ የመጀመሪያዋ ሀገር እንደምትሆን " በምላሹ ደግሞ ሶማሌላንድ ፤ ኢትዮጵያ የባህር በር እና የባህር ኃይል ቤዝ እንዲኖራት በቀይ ባህር በኩል 20 ኪሎ ሜትር የሆነ መሬት ለኢትዮጵያ በሊዝ እንደምትሰጥ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ኢትዮጵያ ግን የሶማሊላንድን የነፃ ሀገርነት እውቅና እንደምትቀበል በይፋ አላረጋገጠችም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሶማሌላንዱ ፕሬዜዳንት ይህን ጉዳይ ሲናገሩ ከጎን ተቀምጠው የነበረ ቢሆንም ንግግራቸውን አልተቃረኑም።

ከዚህ በተጨማሪ የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ፤ በስምምነቱ መሰረት ሶማሌለንድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ እንደሚኖራት ዝርዝር ነገር ሳይገልጹ ተናግረዋል።

አጠቃላይ የዛሬው ስምምነት ዝርዝር ጉዳይ በአንድ ወር ውስጥ ይፋ ይደረጋል።

ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ለሶስት አስርት ዓመታት ዓለማቀፍ እውቅና ማግኘት ያልቻለች ስትሆን ሶማሊያ ደግሞ አንድ አንድ የራሷ ግዛት ነው የምታያት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

የሶማሊያ ካቢኔ በነገው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ እንደተጠራ ተሰምቷል።

አስቸኳይ ስብሰባው ፤ ዛሬ በሶማሌላንድ (ሶማሊያ ሶማሌላንድን እንደ ሰሜናዊ ክልሏ ነው የምትቆጥራት) እና በኢትዮጵያ መካከል ተደርጓል ስለተባለው ስምምነት በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ ለማሳለፍ ነው ተብሏል።

ከዚሁ ከነገው አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ዝግጅት ጋር በተያያዘ #በአሁን_ሰዓት በሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ስብሰባ እየተካሄደ እንደሆነ ተሰምቷል።

ስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ምክትላቸው እና ከፍተኛ የካቢኔ አባላት እንደሚገኙ ታውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር…
#ETHIOPIA 🤝 #Somaliland #RedSea #Port

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ምን አሉ ?

" ... እንኳን የኢትዮጵያ ስብራት ጥገና ቀን በጋራ አደረሰን፤ አደረሳችሁ።

በተደጋጋሚ ለህዝባችን ቃል በገባነው መሰረት ኢትዮጵያ ካሏት ዋና ዋና ስብራቶች መካከል አንዱ የሆነው ቀይ ባህርን #access የማድረግ በዛውም #የማልማት ፍላጎት ከሶማሌላንድ ወንድሞቻችን ጋር በተደረገው የትብብር ስምምነት ዛሬ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመናል።

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንዳነሳነው እኛ ያሉንን ሃብቶች የመጋራት ፣ የመካፈልና በጋራ የመልማት ፍላጎት እንጂ ማንንም በኃይል የማስገደድ ፍላጎት የለንም ስንል የነበረው ሃሳብ በተግባር ዛሬ በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያው ቀን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ የሶማሌላንድ ህዝብና ለሰላም ወዳድ ህዝብ ለልማት ወዳድ ህዝብ የምናበስረው የምስራች ይሆናል።

ስብራቶቻችን ይጠገናሉ፣ ኢትዮጵያ ትበለፅጋለች። በገባነው ቃል መሰረት ሀገራችንን ወደሚቀጥለው ደረጃ እናሸጋግራለን።

ስለሆነው ሁሉ ያደረገልንን ፈጣሪን እናመሰግናለን። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሶማሊያ ካቢኔ በነገው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ እንደተጠራ ተሰምቷል። አስቸኳይ ስብሰባው ፤ ዛሬ በሶማሌላንድ (ሶማሊያ ሶማሌላንድን እንደ ሰሜናዊ ክልሏ ነው የምትቆጥራት) እና በኢትዮጵያ መካከል ተደርጓል ስለተባለው ስምምነት በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ ለማሳለፍ ነው ተብሏል። ከዚሁ ከነገው አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ዝግጅት ጋር በተያያዘ #በአሁን_ሰዓት በሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት…
#Ethiopia 🤝 #Somaliland

" ታሪክ እየተሰራ ነው " - አሊ ሀሰን ሞሃመድ

ኢትዮጵያ እስካሁን በይፋ ከሶማሌላንድ ጋር በተፈረመው የትብብር ስምምነት የባህር በር ለመጠቀም እና የባህር ኃይል ቤዝ እንዲኖራት በምላሹ ደግሞ የ " ሶማሌላንድን " የነፃ ሀገርነት እውቅና እንደምትሰጥ አንዲትም ቃል #አልተናገረችም

የሶማሌላንዱ ፕሬዜዳንት ግን ከስምምነቱ በኃላ ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ የነፃ ሀገርነት ውቅና እንደምትሰጥ በምላሹ የባህር በር እና የባህር ኃይል እንዲኖራት 20 ኪሎሜትር መሬት በሊዝ እንደምትሰጥ ገልጸዋል።

የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ባለስልጣናትም ተመሳሳይ መረጃዎችን ሰጥተዋል።

ለአብነት አሊ ሀሰን ሞሃመድ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ፤ " ታሪክ እየተሰራ ነው " ብለዋል።

ኢትዮጵያ በሊዝ የ20 ኪሎሜትር የባህር በር ተጠቃሚ እንድትሆን በምላሹ ደግሞ #እውቅና እና የኢኮኖሚ እድገት እንደምትሰጥ ገልጸዋል።

" ይህ ጨዋታ ቀያሪ፤ ትልቅ ትርጉም ያለው ስምምነት ነው " ያሉት ባለስልጣኑ " ትልቅና ደፍረትን የሚጠይቅ እርምጃ ነው ፤ ወደፊት ለሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ የብሩህ አድማስ በሮችን የሚከፍት ነው " ብለዋል።

ይህንኑ የአሊ ሀሰን ሞሀመድ ሃሳብን ሞባረክ ታኒ የተባሉት የፕሬዜዳንቱ ዋና ፀሐፊ ተጋርተውታል።

በሌላ በኩል ፤ ሶማሊያ እንደራሷ አንድ ግዛት የምታያት " ሶማሌላንድ " ከኢትዮጵያ ጋር ተፈራረመች ስለተባለው የመግባቢያ ስምምነት በተመለከተ ነገ ካቢኔዎቿ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠው ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሏል።

ለነገው አስቸኳይ ስብሰባ ዝግጅት ዛሬ ምሽት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ምክትላቸው እና ከፍተኛ የካቢኔ አባላት የተገኙበት ሰብሰባ ሲደረግ አምሽቷል።

የሶማሊያ ባለስልጣናትም የመግባቢያ ስምምነቱ ክፉኛ እንዳስቆጣቸው ተነግሯል።

የሶማሊያ የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትሩ አብዲሪዛቅ ሞሀመድ ፤ " ሶማሊያ አትከፋፈልም ፤ በሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነታችን አንደራደርም " ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፤ " ኢትዮጵያ ከግዛት (ክልል) አስታዳዳሪ ጋር ወደብን ለመከራየት / ወታደራዊ ስምምነት (MOU) ማድረግ እንደማትችል በደንብ አድርጋ ታውቃለች ይህ ስልጣን ሙሉ በሙሉ የፌዴራላዊ ሶማሊያ መንግሥት ነው ፤ ኢትዮጵያ የግዛት አንድነታችንን የሚጥስ ተግባር መፈፀም አትችልም " ሲሉ ገልጸዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የዛሬውን " ታሪካዊ " የተባለ የትብብር ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ " ኢትዮጵያ #ቀይ_ባህርን የመጠቀምና በዛውም የማልማት ፍላጎት ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል " ሲሉ አብስረዋል።

ዶክተር ዐቢይ፤ " እኛ ያሉንን ሃብቶች የመጋራት ፣ የመካፈልና በጋራ የመልማት ፍላጎት እንጂ ማንንም በኃይል የማስገደድ ፍላጎት የለንም ስንል የነበረው ሃሳብ በተግባር ታይቷል " ሲሉም ነው ያሳውቁት።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia