ለማንኛውም ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን ለሚመለከቱ ጥያቄና አስተያየትዎ ነፃ የጥሪ መስመራችንን (8118) ይጠቀሙ፡፡
በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን፡ https://bit.ly/3TkrrXD
#Global_Bank_Ethiopia #OurSharedSuccess #CallCenter #CustomerService #CustomerServiceLine #8112

አዲስ መኪና የማሸነፍ እድል እንፈልጋለን? M-PESA ላይ በቀላሉ እንመዝገብ እና በM-PESA ግብይቶችን ፈፅመን አዲሱን መኪና የግላችን እናድርግ
የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether

#ሆሮጉድሩወለጋ
• " ... የተፈፀመው ጥቃት የድሮን ነው። በዚህም በቤተክርስትያኒቱ ግቢ ውስጥ በሚገኝ የበቆሎ እርሻ ውስጥ ምርት በመሰብሰብ በላይ የነበሩ ሰዎች ተገድለዋል " - ፓስተር ተካልኝ ዳባ
• " ተፈፅሟል የተባለው የድሮን ጥቃት ፍጹም ሐሰት ነው " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ባለችው የሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በደረሰ "ድንገተኛ ጥቃት " አባላቶቿ መገደላቸውን አውግዛለች።
ጥቃቱ ታህሳስ 15 የተፈፀመ ሲሆን በጥቃቱ 8 የቤተክርስትያኒቷ አባል የሆኑ ግለሰቦች ተገድለዋል። 5 ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል ይገኛሉ።
የሆሮ ጉዱሩ አካባቢ የሙሉ ወንጌል ኃላፊ የሆኑት ፓስተር ተካልኝ ዳባ ምን አሉ ?
- ታሕሳስ 15 ቀን 2016 በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በቤተክርስትያኒቱ ግቢ ውስጥ በሚገኝ የበቆሎ እርሻ ውስጥ ምርት በመሰብሰብ በላይ የነበሩ ሰዎች ተገድለዋል።
- በጥቃቱ ሁለት የሦስተኛ እና የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ተገድለዋል።
- በድሮን ጥቃቱ የቤተክርስትያኒቷን መሪ ጨምሮ፣ በአጠቃላይ 8 ሰዎች ተገድለዋል።
የተገደሉት ዜጎች ስም ፦
• አቶ ሀብታሙ ንጋቱ - የአጥቢያዋ መሪ
• አቶ በየነ ጥቂ - የአጥቢያዋ ጥበቃ ሠራተኛ
• አቶ ጉደታ ፍጤ - ዲያቆን
• አቶ ታዴ መንገሻ - ዲያቆን
• ወጣት ዳመና ሊካሳ - የኪቦርድ ተጫዋች
• ተማሪ ዱጋሳ ዋኬኔ - የኪቦርድ ተጫዋች
• ተማሪ አብዲ ጥላሁን - ዘማሪ
• ተማሪ ኦብሳ ታረሳ - የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል
ቆስለው በሆስፒታል ያሉት፦
• አቶ ታሜ ንጉሳ - የአጥቢያዋ መሪ አገልጋይ
• አቶ ፋጠኔ ገላና - ዲያቆን
• አቶ ስንታየሁ ታከለ - የጸሎት አገልጋይ
• ወ/ሮ ሽቱ ኢምሩ - የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል
• ወ/ሮ ባጩ ገላና - የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል
በሌላ በኩል ፤ የቤተክርስትያኒቷ ፕሬዝዳንት መጋቢ ላኮ በዳሶ በሰጡት መግለጫ ፤ በአንድ በኩል ድርጊቱ በድሮን መፈፀሙ ሲዘገብ መንግሥት ደግሞ በድሮን የተፈፀመ እንዳልሆነና በአካባቢው ታጣቂዎች መፈፀሙን መግለፁን አስንተዋል።
" ድርጊቱ በየትኛውም አካል በምንም መልኩ ይፈጸም፤. . . .ጉዳዩ በማን እንደተፈጸመ ተጣርቶ ፍትህ እንዲሰፍን " እንፈልጋለን ብለዋል።
ፕሬዜዳንቱ ፤ " በተመሳሳይ በአማራ ክልላዊ መንግሥት በዱር ቤቴ እንዲሁም በቡሬ ከተማ በአባሎቿ ላይ የሞት፥ የስደትና የንብረት ጉዳት " መድረሱን ገልጸዋል።
በምዕራብ ኢትዮጵያም የአማኞችን ንብረት መውረስና መፈናቀል እየደረስ እንዳለ፣ ይህን የሰብዓዊ መብት መጣስና የዜጎችን ጉዳት የሚመለከተው አካል ሁሉ እንዲያጣራ ጠይቀዋል።
መጋቢ ላኮ ፤ " ገለልተኛ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና ሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት ጉዳዩን በአንክሮ በማየት እንዲያጣራ እና እውነቱን ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ " ጥሪ አቅርበዋል።
የመንግሥት የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶ/ር ለገሠ ቱሉ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል፣ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በባሮ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ተፈፅሟል የተባለውም የድሮን ጥቃት " ፍጹም ሐሰት " ብለዋል።
መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት እና የሮይተርስ ነው።
@tikvahethiopia

#ኤዶ
በኦሮሚያ እና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ በምትገኘው በሲዳማ ክልል፣ ወንዶ ገነት ወረዳ የኤዶ ቀበሌ በትላንትናው ዕለት አለመረጋጋት መፈጠሩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከፀጥታ አከላት እንዲሁም ከነዋሪዎች ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
" ኤዶ " በኦሮሚያ እና ሲዳማ አዋሳኝ የምትገኝ ቀበሌ ስትሆን ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ መሰል አለመረጋጋት ፣ መንገድ የመዝጋት፣ ንግድ እና ትራንስፖርት የማስተጓጎል ችግሮች ሲከሰቱ ነበር።
በተለይ አካባቢው ላይ ከዓመታት በፊት ህዝበ ውሳኔ ከተደረገ በኃላ ውጤቱን ተከትሎ አስተዳደራዊ መዋቅር ከተዘረጋ ወዲህ በተለያዩ ጊዜ መንገድ መዝጋቶችና አንዳንድ የብጥብጥ ሙከራዎች ሲደረጉ ይስተዋላል ብለዋል ነዋሪዎች።
በትናንትናው እለትም እንዲህ ያለዉ ሙከራ መሞከሩን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡና የቀበሌዋ እንቅስቃሴ መስተጓጎሉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከነዋሪዎች ለመረዳት ችሏል።
ወቅት እየጠበቀ በሚፈጠረው መሰል ችግር ሰዎች ስራ ወጥተው መግባት፣ መንገድ ሄደው መመለስ እንደሚቸገሩና የንግድ እንቅስቃሴ ክፉኛ እንደሚያስተጓጎል ነዋሪዎች ገልጸዋል።
አንድ የወንዶ ገነት ወረዳ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ፤ " በሲዳማ ክልል በውንዶ ገነት ወረዳ በኤዶ ቀበሌ ታሕሳሰ 19 ከቀኑ 4 ሰአት ጀምሮ መንገድ ዝግ ሆኖ ዛሬም ተዘግቶ ወሏል " ብለዋል።
" ኤዶ " ላይ ችግር መኖሩን ተከትሎ ነዋሪዎች በሻሸመኔ አድረገው ወደ ወንዶ ገነት ለመጓዝ መገደዳቸውን ለመረዳት ተችሏል።
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የወረዳዉ የጸጥታ ጉዳይ ተጠሪ አቶ ሀማሮ ሀይሶ እንደሚገልጹት ፤ በአንድ ትምህርት ቤት ዉስጥ የተጀመረ ረብሻ በመስፋቱ የትራንስፖርት አገልግሎት ከመቋረጡ በላይ አንድ ሞተረኛ #ተጎድቶ ሆስፒታል መግባቱን የገለጹ ሲሆን ምሽቱን የሲዳማ ክልል የጸጥታ ኃይል ቀበሌዋን መቆጣጠሩንና የትራንስፖርት ችግሩ መፈታቱን ገልጸውልናል።
በትምህርት ቤት የተጀመረዉ ረብሻ ወደት/ቤቱ የሄዱ እንግዶች ላይ ተቃዉሞ መሰማቱን ተከትሎ የተጀመረ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ሀማሮ ይህን ችግር የሚያስጀምሩና የሚመሩ ጸረሰላም ወንጀለኞች እንደሚታወቁና በዚህና በሌሎች ወንጀሎች እንደሚፈለጉ ገልጸዋል።
ከዚህዉ ጋር በተያያዘ አስተያዬታቸዉን የሰጡን የአካባቢዉ ነዋሪና የጸጥታ አካል ደግሞ እንዲህ ያለዉ ሙከራ በተደጋጋሚ እየተሞከረ መሆኑን በማንሳት ችግሩን ከስሩ ለመፍታት በዛኛዉ በኩል አጎራባች የሆኑ የኦሮሚያና በዚህኛዉም በኩል ያሉ የሲዳማ ቀበሌ ነዋሪዎች ዉይይት ያስፈልጋቸዋል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

የሹፌሮች ጉዳይ . . .
" በ2 ሳምንታት ብቻ ሰባት ሹፌሮች በታጣቂዎች ተገድለዋል። ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ የተገደሉት ወደ 70 ይደርሳሉ " - ጣና የአሽከርካሪዎች ማኀበር
በጅማና በአዲስ አበባ ከተማ መካከል ‘አስጎሪ’ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሲያሽከረክሩ በነበሩ ሹፌሮችና ተሽከርካሪዎች ላይ ታጣቂዎች ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ/ም ጥቃት ማድረሳቸውን ስሜ ከመጠቀስ ይቆይ ያሉ የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የዓይን እማኙ በሰጡት ቃል፣ “ ዓይኔ እያዬ ነው ሹፌሮቹን የገደሏቸው። ተሽከርካሪዎቹንም አቃጠሏቸው ” ሲሉ የተመለከቱትን አስረድተዋል።
ጥቃቱን የፈጸሙት እነማን እንደሆኑ፣ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ፣ ምን ያህል ተሽከርካሪዎች እንደተቃጠሉ እንዲገልጹ ጥያቄ የቀረበላቸው ታማኝ ምንጩ፣ ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች እንደሆኑ፣ ሹፌሮች ከታጣቂዎቹ በተተኮሰ ጥይት እንደተመቱ፣ አንድ ሹፌር ሕይወት ማለፉን፣ ከ11 በላይ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን አብራርተዋል።
ስለ ሁኔታው ማብራሪያ እንዲሰጥ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት የሹፌሮችን በታጣቂዎች እገታና ግድያ በጥልቀት በየወቅቱ የሚከታተለው ጣና የአሽከርካሪዎች ማኀበር (በማኀበራዊ ትስስር ገጹ “የሹፌሮች አንደበት) በበኩሉ፣ ማኀበሩ ባለው ክትትል መሠረት፣ “በሁለት ሳምንታት ብቻ ሰባት ሹፌሮች በታጣቂዎች ተገድለዋል። ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ የተገደሉት ወደ 70 ይደርሳሉ ” ብሏል።
ይህን ያሉት ማኀበሩን የሚመሩ አንድ ምንጭ አክለውም ሹፌሮች የተገደሉት በሰሜን ጎንደር ማክሰኝት፣ በመተሃራ፣ በቡታጅራ መስመር፣ በደሴ መስመር በኦሮሚያ ልዩ ዞንና በሌሎች አካባቢዎች መሆኑን አስረድተዋል።
“ ከቀናት በፊትም በኦሮሚያ ክልል በቡታጅራ መስመር ከአሥር በላይ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል። አሽከርካሪዎችም በቅድሚያ መንገዱን እያጣሩ መጓዝ አለባቸው ” ሲሉ አሳስበዋል።
የታጣቂዎቹ ዋነኛ ፍላጎት ምን እንደሆነ ተጠይቀው ሲያስረዱም፣ አንደኛ የገንዘብ ፍላጎት፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ሰላምን ማወክ አላማቸው አድርገው በመነሳተቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ምን ቢደረግ መፍትሄ ሊመጣ ይችላል ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ “ አሁን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር አለ። በፓርላማ እየቀረበ ‘ይህን ያህል አጓጓዝን፣ ይህን ያህል አመላለስን’ ይላል የተጓጓዘውን የአገሪቱን ምርት። በፓርላማ ግን ሹፌሮች ተገድለዋል ብሎ መናገር አለበት ” ብለዋል።
አክለውም፣ “ ችግሩ በሚስተዋልባቸው ክልሎች የተከሰቱትን ችግሮች እንዲስተካከሉ መጠየቅ ነበረበት። ያ ሲጠየቅ ግን አይስተዋልም ” ሲሉ ወቅሰዋል። ካልሆነ ግን አሽከርካሪዎች አድማ በምታት ከመንቀሳቀስ ተቆጥበው ሕይወታቸውን ማትረፍ ግድ ይላቸዋል ተብሏል።
በየወቅቱ የሚስተዋለውን ችግር በተመለከተና ለተነሳው ወቀሳ ምን ምላሽ እንዳለው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።
ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

#CBE
የፈረስ ትራንስፖርት የጉዞ ሂሳብዎን
በሲቢኢ ብር በቀላሉ ይክፈሉ!
***
የሲቢኢ ብር መተግበሪን ለማውረድ/ለማዘመን የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
===========
የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• Telegram፡- https://t.iss.one/combankethofficial

#ኢትዮጵያ🇪🇹
ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች ዓለም ዓቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር አሸነፉ።
ባለፈው የታህሳስ ወር 2016 ዓ/ም ሁለተኛ ሳምንት በቻይና “ዩዥን” በተካሄደው “ዊልስ ቦት አለማ ዓቀፍ የሮቦቲክስ” ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው ተወዳደሩ የተባሉ 21 ኢትዮጵያዎያን ታዳጊዎች በሦስት ዘርፍ ማለትም፦
* በቤስት ኦርጋናይዜሽን አዋርድ
* በቤስት ቲም አዋርድ
* በሞስት ዲቨሎፕመንት አዋርድ ማሸነፋቸውን ኢትዮ - ሮቦቲክስ የተሰኘው ድርጅት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በመረጃው መሠረት፣ ሦስት ሮቦቶችን ይዞ ወደ ቻይና አቅንቶ ነበር የተባለው ኢትዮ- ሮቦቲክስ ቡድን በዓለም ዓቀፍ ውድድሩ ከተሳተፉ 27 አገራት 3ኛ ደረጃን ይዟል ተብሏል።
በውድድሩ ተሳተፈዋል ለተባሉት ታዳጊዎች ቅዳሜ ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ/ም በቦሌ ሳፋየር አዲሱ አያ ሆቴል በተደረገላቸው የእውቅና መድረክ መርሀ ግብር
ቡድኑ ኢትዮጵያን በመወከል ላስመዘገበው የተሻለ ውጤት ሦስት #ዋንጫና ሰርቲፊኬት ተሸልሟል።
የኢትዮ ሮቦ ሮቦቲክስ ታዳጊ ኢትዮጵያን መጪውን ዓለም ተረድተው ኢንጂነሮችና ፕሮግራመሮች እንዲሆኑ ላለፉት 14 ዓመታት ስልጠና እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በዓለም ዓቀፍ የሮቦቲክስ ውድድሮች ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ እያመቻቸና አሁንም ከ200 በላይ ታዳጊዎችን እያሰለጠነ እንደሆነ ገልጿል።
በርካታ የአፍሪካ አገራት የሚሳተፉበት 2ኛው የአፍሪካ የሮቦቲክስ ሻምፒዮና በየካቲት ወር 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚዬም እንደሚዘጋጅም ተመላክቷል።
መረጃውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

#መቐለ
የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶች በመቐለ ከተማ እንዲዘጉ እየተደረገ ነው።
በመቐለ የቤቲንግ ቤቶች ከቅዳሜ ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ ተዘግተዋል።
ጨዋታው የፀጥታ አካላት በከተማዋ ሁሉም አከባቢዎች እየዞሩ ነው እንዲዘጋ ያዘዙት።
የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በቤቲንግ መጫወቻ ቤቶች ስለተወሰደው የመዝጋት እርምጃ ምክንያት የተጣራ መረጃ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ለጊዜው አልተሳካም። ጥረቱ ግን ይቀጥላል።
የፀጥታ አካላት በቤቲንግ ቤቶች ላይ የወሰዱት የመዝጋት እርምጃ የህዝቡ አስተያየት ምን እንደሚመስል የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በማህበራዊ የትስስር ገፅ የታዘበው አጋርቷል።
ዮናታን ግዛቸው የተባሉ የመቐለ ነዋሪ የቤቲንግ ቤቶችን መዘጋት በተመለከተ ፅፈው ባሰራጩት ፅሁፍ አንዳንዶች እርምጃውን ሲደግፉ አንዳንዶች ደግሞ ተቃራኒ ሀሳብ ሰጥተዋል።
ገብረሂወት ተኽላይ የተባሉ አስተያየት ሰጪ " ወጣቱ ጊዜው በስራ እንዳያውል ጠምዶ የሚይዝ መጥፎ ሱስ ነው። ስለሆነም የተወሰደው እርምጃ ተቀባይነት አለው " ብለዋል።
ቅዱስ ዜናዊ መለስ የተባለው ወጣት ደግሞ " ወጣቱ ካለበት ችግር ሰርቶ እንዳይለወጥ ቁጭ አድርጎ የሚያስውል መጥፎ ልማድ ነው። ቢሆንም ግን ለወጣቱ የሚሆን የስራ እድል ካልተፈጠ የቤቲንግ ጨዋታን በመዝጋት የሚመጣ ለውጥ አይኖርም። " ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
መሰረት ታደሰ የተባሉ ነዋሪ ደግሞ ፤ " ከመዝጋት ጨዋታው በህጋዊ መንገድ ተነጋግሮ መቀጠል ነው የሚመረጠው " ብሏል።
" አስገደድዶ ተጫወት የሚል አለ ወይ ? " ብሎ በመቃወም የቤቲንግ ጨዋታ እንዲቀጥል አስተያየት የሰጠው ደግሞ ዲጀ ናቲ የተባለ የመቐለ ነዋሪ ነው።
የቤቲንግ ቤቶች በመቐለ ከተዘጉ ዛሬ ሁለተኛ ቀናቸው ይዟል። አጫዋቾች ይከፈታሉ በሚል አሁንም ተስፋ አልቆረጡም።
የፀጥታ አካሉ ቤቲንግ ቤቶቹ ለጊዜው ነው የዘጋቸው ወይስ ለዘላቂ የሚለው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተከታትሎ የሚያቀርብ ይሆናል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እሁድ ሲረዝም፣ ከአምዕሮኣችን የማይጠፋውን እንክፈት እንደሰት - ከ#ሰንቺፕስ 😋 ጋር #ሰኒሞመንትስ .☀️
Sundays can get long and so, let us open up the snack which has been our our minds #SunChips😋 #SunnyMoments .☀️
Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia

#ሶጌ
ከትናንት በስቲያ አርብ ታህሳስ 19/2016 ዓ.ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ካማሺ ዞን ቦሎ ጅጋንፎይ/ምዥጋ ወረዳ ሶጌ ከተማ ጠዋት ታጣቂዎች ወደ ከተማው በመዝለቅ ከፍተኛ ጥቃትና መድመት ማድረሳቸውን የወረዳው አስተዳደር ገልጿል።
በጥቃቱ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በወረዳው የሚገኙ 2 ባንኮች (የአዋሽ ባንክ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) መዘረፋቸውንም ገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ መጠን ያላቸው 8 ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን አመልክቷል።
በወረዳው የነበሩ ጸጥታ አስከባሪዎች ለግዳጅ ወደ ሌላ ስፋራ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ ታጣቂዎቹ በቀላቀሉ ወደ ወረዳው በመግባት ጥቃት ማድረሳቸው ነው የተነገረው።
በዕለቱ ለ3 ሰዓታት ያህል ከተማውን ተቆጣጥረው እንደነበርና በሶጌ ከተማ ውስጥ የሚገኙ አንድ ፖሊስ ጣቢያ መቃጠሉን፣ ሁለት ባንኮችም መዘረፋውንና ሌሎችም በርካታ የመስሪያ ቤት ንብረቶች መዘረፋቸውን ወረዳው አመልክቷል።
በዛሬው እለት በከተማው መረጋጋት መስፈኑን ተከትሎ ከአካባቢው ሸሽተው የነበሩ ነዋሪዎች ሲመለሱ መዋሉ ተመላክቷል።
ቃላቸውን የሰጡ የወረዳው ነዋሪዎች በዕለቱ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ስለነበር አብዛኛው የከተማዋ ነዋሪ አካባቢውን ለቀው ሸሽተው እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በወረዳው አንድ ፖሊስ ጣቢያ መቃጠሉንና የቁም እንስሳትን ጨምሮ የንብረት ዝርፍያ መፈጸሙን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል፡፡
5 ተሸከርካሪዎች በአንድ ስፋራ መቃጠሉን የገለጹ ሲሆን መጠናቸው ያልታወቀ ሌሎች የወረዳው ተሽከርካሪዎች በታጣቂዎች መወሰዱን አብራርተዋል፡፡
ጥቃቱን በመሸሽ ላይ የነበሩ 4 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን እንደሚያውቁም ጠቁመዋል፡፡
በወረዳው በአሁኑ ወቅት የጸጥታ ሐይሎች መግባታቸው የገለጹት ነዋሪዎች በአካባቢው አሁንም ወደ ቤታቸው ያልተመለሱ የሸሹ ነዋሪዎች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡
አርብ ዕለት በሶጌ ከተማ የደረሰውን ጥቃት በወረዳው አቅራቢያ ይንቀሳቀሳሉ ያሏቸው የሼኔ ታጣቂዎች መፈጸማቸውን የወረዳው አስተዳደር ገልጿል።
በካማሺ ዞን ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ከክልሉ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት ላይ ከደረሱ ወዲህ በአካባቢው ሰላም መስፈኑን የክልሉ መንግስት ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል።
ይህ መረጃ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።