#ትግራይ
ከገረብ ሰገን ግድብ ለመቐለ ከተማ የመጠጥ ውሃ ለማቅረብ መጋቢ የሆነው ማእከላይ የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ማስተላለፍያ ትራንስፎርመር (ቮልቴጅ KO-9) #ተሰረቀ።
ስርቆቱ የተፈፀመው ታህሳስ 12/2016 ዓ.ም ንጋት ላይ ነው ተብሏል።
ስርቆቱ እስከ አሁን " ማንነታቸው ባልታወቁ ዘራፊዎች " መፈፀሙ ነው የተሰማው።
የትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ግርማይ ግደይ ለሚድያዎች በሰጡት መረጃ ፤ በቅርቡም ወደ ጋምራና ጨለቆት የሚባሉ የመቐለ ዙሪያ አከባቢዎች የኤሌክትሪክ ሃይል የሚያስተላልፍ ትራንስፎርመር ተዘርፏል።
ከገረብ ሰገን ግድብ ለመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ውሃ ለማቅረብ የሚያገለግለው ጨምሮ በወራት ውስጥ 3 ትራንስፎርመር መዘረፋቸውን የተናገሩት አቶ ግርማይ ፤ የአሁኑ የትራንስፎርመር ስርቆት በርካታ የከተማዋ አከባቢዎች ለመጠጥ ውሃ እጦት ይዳርጋል ብለዋል።
የትራስፎርመር ስርቆቱ ከግድቡ አጠገብ የሚገኘው የመለስ ስራ አመራር አካዳሚ የኤሌክትሪክ አግልግሎት እንዲቋረጥ ምክንያት መሆኑም አክለው አስታውቀዋል።
በተደጋጋሚ ጊዜ በኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፍያ ትራንስፎርመሮችና ገመዶች የሚፈፀም ስርቆት የመከላከል ጉዳይ ለፀጥታ ሃይሎች ብቻ የሚተው አይደለም ያሉት ባለሞያው ፤ ህዝቡ ተደራጅቶ አከባቢውንና የመንግስትና የህዝብ ንብረት በንቃት እንዲጠብቅ አሳስበዋል።
በጦርነቱ ጊዜ በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች የነበሩ ትራንስፎርመሮች ላይ በርካታ የስርቆትና የማበላሸት ተግባራት ሲፈፀም እንደነበረ መረጃውን የላከልን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ገልጿል።
ቲክቫህ ትግርኛ @tikvahethiopiaTigrigna
@tikvahethiopia