TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FoodandAgricultureOrganization #UN

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ  የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸለሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ሽልማት የተሰጣቸው ዛሬ በጣልያን፤ ሮም ከተማ ነው።

በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (FAO) ፤ ሮም ውስጥ ባሰናዳው ዝግጅት ዶ/ር ዐቢይ ፤ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያደረጉ ላለው ጥረት የከበረውን አግሪኮላ ሜዳልያ እንዳበረከተላቸው ተነግሯል።

የፋኦ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኩ ዶግዩ ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፋኦ ከፍተኛ ሽልማት ለሆነው አግሪኮላ ሜዳልያ ሽልማት በመብቃታቸውን " እንኳን ደስ አልዎት ! " ብለዋቸዋል።

ይህ ሽልማት መሪዎች እና ሌሎችም የዓለማችን እውቅ ሰዎች የምግብ ዋስትናናን ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ድህነትን ለመቀነስ ለሚያደርጉት የተሳካ ጥረት የሚሰጥ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በዚህም የአግሪኮላ ሜዳሊያ ለጠ/ ሚኒስትሩ እየተበረከተው ፦
* በኢትዮጵያ ገጠርና ኢኮኖሚ ልማት ላይ ላበረከቱት አስተዋፅኦ
* በተለይም " በስንዴ፤ ምግብ እራስን መቻል ፕሮግራም " ባደረጉት የግል ድጋፍ
* በኢትዮጵያ አረንጓዴ ሌጋሲ (Green Legacy) ስራ መሆኑን አስረድተዋል።

ከዚህ ባለፈ ዋና ዳይሬክተሩ " ባለፉት 5 አመታት ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለችውን አስደናቂ እድገት ተመልክቻለሁ " ማለታቸው ተነግሯል።

ይህ ሊሆን የቻለው " በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተሰጡ ውጤታማ፣ ተጠያቂነት ያለውና የተረጋጋ አመራር ነው " ያሉት የፋኦ ዋና ዳይሬክተር ፤ ተመልክቼዋለሁ ያሉት እድገት የተመዘገበው " ባለፉት ዓመታት በነበሩ አስቸጋሪ ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች ውስጥ ነው ፤... ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን እንደ አህጉር ለአፍሪካም ይልቅ መልዕክት ነው " ማለታቸው ተሰምቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው የተሰጣቸውን ሽልማትና እና እውቅናን ተከትሎ ባሰራጩት መልዕክት ምስጋና አቅርበው ፤ " ከፍ ያለ ጠቀሜታ ባላቸውና የኢንደስትሪ ግብዓት በሆኑ የግብርና ምርቶች ላይ ማተኮራችን ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እያስገኘልን ይገኛል። የምግብ ሉዓላዊነት ጉዟችንን በፅናት እናስቀጥላለን " ብለዋል።

የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያን በተሸለሙበት ወቅት የፋኦ አመራሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ እና የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተው ነበር ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከፋኦ ድረገፅ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia