TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA " ለመሆኑ ሰላም ሚኒስቴር ሰላም ነው ወይ ? " - አቶ ወንድሙ ኢብሳ " መከላከያ ወንድሞቹን መግደል የለበትም፤ ወንድሞቹም መከላከያን መግደል የለባቸውም " - አቶ ታዬ ደንደአ ሰላም ሚኒስቴር ረቡዕ ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም አዳማ ከተማ አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ የተጋበዙት ጠበቃና የሕግ አማካሪ አቶ ወንድሙ ኢብሳ፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሌሎችም ጋዜጠኞች ፦ °…
" ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ለማባረር ዘግይተዋል " - ጠበቃና የህግ አማካሪ ወንድሙ ኢብሳ
ከቀናት በፊት አዳማ በነበረ መድረክ " ለመሆኑ ሰላም ሚኒስቴር እራሱ #ሰላም_ነው_ወይ ? ሰላም ሚኒስቴር ሰላም መስበክ ሲገባው በመ/ቤቱ ሆነው በስውር አማፂያንን የሚደግፉ ሰዎች አያለሁ " ሲሉ በወቅቱ የሚኒስትር ዴኤታ ለነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ ጥያቄ ያቀረቡት ጠበቃና የሕግ አማካሪው አቶ ወንድሙ ኢብሳ የአቶ ታዬን ከስልጣን መነሳትና በፌስቡክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተናግረው ስለፃፉት ፅሁፍ እንዲሁም አቶ በሕግ የሚያስጠይቃቸው ጉዳይ ይኖር እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ጠበቃና የሕግ አማካሪው አቶ ወንድሙ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?
- ከዚህ በፊት አቶ ታዬ ደንደአ በሚዲያዎች ላይ የሚሰጡት አስተያየት ላይ ተቃውሞ ስላለኝ የዛሬ አመትም " አቶ ታዬ የሰላም ሚኒስቴር እራሱ ሰላም ነው ወይ ? " ብዬ ጠይቄያቸው ነበር። ባለፈውም እንዲሁ ጠይቄያቸዋለሁ።
- በሰላም ሚኒስቴር ውስጥ ሆነው ሰላምን ሲሰብኩ አልነበረም።
- ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ለማባረር ዘግይተዋል። (አንስተዋቸዋል ሳይሆን አባረዋቸዋል ነው የምለው)
- አቶ ታዬ ከስልጣን ከተባረሩ በኃላ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እጅግ በጣም ወራዳ በሆነ ቃላት መናገራቸው ቦዶነታቸውን የሚያሳይ ነው።
- ምን ጊዜም ልዩነት ይፈጠራል ፤ በለማና በዐቢይ መሃከል ልዩነት ተፈጥሯል ተከባብረው ነው የተለያዩት አልተሰዳደቡም ፤ ጉዱም ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር ወይም ከብልፅግና ጋር ልዩነት ፈጥሯል አልተሰዳደቡም ፤ ሌላው ቀርቶ የኦነጉ ዳውድ ኢብሳ ' ትጥቅ ፈቺ ትጥቅ አስፈቺ ማነው ? ' ከማለት ባለፈ ኢትዮጵያዊ ባህል ያልሆነ ስድብ አልተሳደቡም።
- አቶ ታዬ ባለፉት አምስት ዓመታት የብልፅግናን መዝሙር ሲዘምሩ ፣ ስለብፅግና ሲቀሰቅሱ ፣ ብልፅግና ትክክል እንደሆነ ሲሰብኩ ነበር ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲያወድሱ ቆይተዋል ይሄን አቋማቸውን እጥፍ አድርገው " የሚፅፉትን የሚናገሩትን እውነት ነው ብዬ ተሸወድኩኝ " ማለታቸው አቋም የሌላቸው መሆኑን ነው ያሳየኝ።
- ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ሳያባርሯቸው በፊት አስቀድመው ስልጣን በገዛ ፍቃዳቸው ቢለቁ ኖሮ አንድ ነገር ነው። አቶ ለማ በጨዋ ደንብ ' ከብልፅግና ጋር #አልስማማ አልሰራም ' ብለው እንደሄዱት አላደረጉም።
- የአቶ ታዬ ጉዳይ ሰሞኑን ይወራል በቃ ያልፋል።
- በሕግም ይጠየቃሉ፣ ከባድ ማኖ ነው የነኩት።
- እራሳቸው መንግሥት ውስጥ ሆነው " ይሄ መንግሥት ሰላም አይፈልግም ፀረሰላም ነው ፣ ድርድሩ እንዳይሳካ ያደረገው የኔ መንግሥት ነው " ማለታቸውም ያስጠይቃቸዋል።
- እስከ ትላንት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን እስኪያባርሯቸው ድረስ ምንም ሳይሉ ነው የቆዩት። ልክ ከስልጣን ሲባረሩ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ' ጨካኝ ፣ በደም የሚነግድ ' ሆኑ፤ በዚህም ይጠየቃሉ።
- ወይ ለይቶላቸው እንደነ ክቡር ለማ፣ እንደነ ክቡር ገዱ ተቃውሟቸውን በጨዋ በሰለጠነ መንገድ ገልፀው አርፈው አልተቀመጡ። ከእሳቸው ይልቅ ጫካ ያሉት ሰዎች አቋም አላቸው ፤ ለይቶላቸው አቋማቸውን ገልጸው ግልፅ የሆነ ትግል እያደረጉ ናቸው።
- አቶ ታዬ ከብልፅግና " ስልጣን አልፈልግም " ብለው ስልጣን አለቀቁም። ከስልጣን እስኪባረሩ ድረስ ነው የቆየቱ። አቶ ለማ እኮ መከላከያ ሚኒስትርን ነው ለቀው የሄዱት።
- አቶ ታዬን መሳይ ሌሎችም ብልፅግና ውስጥ አሉ።
@tikvahethiopia