TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ🔝

ለተማሩና ሐሳብ ላላቸው ዜጎች #የብድር ሥርዓት ሊዘረጋ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አሕመድ ተናግረዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር ዐብይ አህመድ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ባለፉት ጊዜያት ትልልቅ #ሐሳብ ላላቸው ሳይሆን ትልልቀቅ #ሀብት ላላቸው ብቻ ከፍተኛ የብድር አገልግሎት ስትሰጥ ቆይታለች፤ በዚህም የሚፈለገው ለውጥ ሳይመዘገብ ቀርቷል፡፡ ይህንን ችግር በመረዳትም ለተማሩ ዜጎች ሐሳባቸውን በማዬት ብድር ለመስጠት እንዲቻል ፖሊሲዎች እንደሚመቻቹና አነስተኛና መካከለኛ ባለሀብቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

በዓለም ባንክ የአገልግሎት አሰጣጥ መለኪያ መሠረት ኢትዮጵያ 159ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይ 5 ዓመታት የተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ #በማሻሻል በመለኪያው ከ100 በታች ለማድረግ በእርሳቸው የሚመሩ 10 ተቋማት ተለይተው ወደ ለውጥ ሥራ መገባቱን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የአሠራር ፖሊሲዎች፣ የሕግ ማዕቀፎች እና የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት በተቃርኖ የተሞላ አሠራርን መከተላቸው ኢትዮጵያ በቀላሉ ሥራ (ቢዝነስ) የማይሠራባት ሀገር እንድትሆን ማድረጉንም ገልጸዋል፡፡

ካለፈው ወር ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትሩ #የሚመራው እና 10 ተቋትን ያካተተው ልዩ ኮሚቴ (ስትሪንግ ኮሚቴ) አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳደግ የጀመራቸውን የለውጥ ሥራዎች በየወሩ የውጤት ግምገማ እያደረገ ይገኛል፡፡

ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ ዕድገት እንዲመዘገብ ‹‹ያለንን የተፈጥሮ ሀብት #በአግባቡ መጠቀምና ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ አዳዲስ ሐሳብ፣ ዕውቀትና ክሕሎትን በተቀናጀ መልኩ አሟጦ መጠቀም ይጠይቃል›› ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

እስካሁን ያለው አካሄድ በተቃርኖ የተሞላ፣ ዘመናዊ አሠራርን ያልተከተለ፣ ተወዳዳሪነት የሌለውና በአነስተኛ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ዜጎችን በቀላሉ የማይጠቅም በመሆኑ ውጤት ማምጣት እንዳልቻለም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያብራሩት፡፡ ለዚህ ደግሞ ውስብስብ የሆነ አካሄድን መጠቀምና የገንዘብ አቅርቦት ችግር ምክንያቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ከችግሩ ለመውጣት የአሠራር ሥርዓትን ማቅለል፣ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎችን ማድረግና ምቹ አካባቢን መፍጠር እንደሚገባ ነው ያብራሩት፡፡

ለሥራዎች ገንዘብ የማቅረብ ሂደቱን ቀላል ማድረግ፤ እስካሁን ቋሚ ንብረት ይያዝ የነበረበትን የባንኮች አሠራር በቀጣይ ሐሳብን በማስያዝ ወጣቶች ብድር የሚወስዱበት ሁኔታ እንዲፈጥር ማድረግና የግል ተቋማት ውስጥ በቀላሉ ወደ ሥራ ተገብቶ ውጤታማ የሚሆንበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሚገባም ነው የተናገሩት፡፡

‹‹በአዲስ ዕውቀትና ሐሳብ ዕድገታችን ማስቀጠል አለብን፤ ለዚህ መንግሥት ማድረግ የሚገባውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ለግል ዘርፍ መስጠት አለበት፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ ቀላልና ሳይንሳዊ የሆነ የአሠራር ሥርዓትን መዘርጋት ይገባል›› ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስት ዶክተር ዐብይ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ‹‹አይቻልም›› ወይም ‹‹ሕጉ አይፈቅድም›› የሚሉ አመለካከቶችን በመስበር ሁሉም ተቋማት ለሀገር ሲሉ ቀና አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡ ጅምሮቹ ወደ ውጤት እንዲያድጉ አሁንም ተቋማት በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸውም መክረዋል፡፡

በዕለቱ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያለፈው አንድ ወር አፈጻጸም ቀርቦ ተገምግሟል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሐሳብ መድረክ 💬

https://t.iss.one/+01D5gVgONq8yMjE8

" መብቷ ነው / መብቱ ነው ? "

ምንድነው መብቱ ነው ? መብቷ ነው ?

የሌላ ሰዎች ልጆች ሲሆኑ እንደፈለጉ ይሁኑ እድሜዋ/ው ነው ፤ መብቷ ነው / መብቱ ነው ... የእኛ ልጆች ሲሆን የምን መብት ነው ? ስነ-ስርአት ትያዝ / ይያዝ የሚል አመለካከት በማህበረሰባችን ውስጥ ትልቅ ቀውስ ይፈጥራል።

የኛ ልጆች ሲሆኑ ወደ ቤተክርስቲያን / ወደ መስጂድ የሌሎች ሲሆኑ " እድሜያቸው ነው መብታቸው ነው የፈለጉበት ይሂዱ " ማለት ፤ አልፈ ሲልም ከነሱ ጋር ባልተገባ ቦታ ዝቅ ብሎ መለዋል ጉዳቱ የከፋ ነው።

ሁሉም ነገር ገደብ ሲኖረው ጥሩ ነው።

ዛሬ የፈለጉበት ይዋሉ የተባሉ ልጆች ነገ የኛንም ልጆች ይዘው እንደማይጠፉ ምን ያህል እርግጠኞች ነን ?

ሁሉም ታዳጊ ልጆች ልጆቻችን ናቸው ብለን ወደ ጥሩ ቦታ እንምራቸው። ከተሳሳተ መንገዳቸው እናርማቸው። ነግበኔ ነው እንበል !

በናውስ (Nous) የሐሳብ መድረክ...እርሶም በውስጦ የሚመላለሰውን የሚናገሩበት ቦታ ያጡትን ጠቃሚ #ሐሳብ_ያጋሩ👇
https://t.iss.one/+01D5gVgONq8yMjE8

@NousEthiopia