TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢንጪኒ

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ አደኣ በርጋ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት የኢንጪኒ ከተማ ባለሥልጣን እና የጸጥታ አስከባሪዎችን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

የከተማው ነዋሪዎች ምን አሉ ?

ስማቸው ለደህንነታቸው ሲባል እንዲገለፅ ያልፈለጉ ነዋሪ ፦

* የሰባት ሰዎች አስከሬን ዛሬ ጠዋት ተገኝቷል።

* ማረሚያ ቤት ተሰብሮ እስረኞች ተለቀዋል።

* ህዳር 28 ቀን ለ29 ቀን 2016 ዓ.ም. አጥቢያ ከሌሊቱ ስድስት ሰኣት ጀምሮ ነው ጥቃት የተፈፀመው።

* የወረዳው ማረሚያ ቤት ተሰብሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ተለቀዋል።

* በታጣቂዎቹ ጥቃት የከተማዋ አስተዳዳሪን (ብርሃኑ ሃብትዬ) ጨምሮ የሰዎች ህይወት አልፏል።

* በተለያዩ ጥበቃ ስራ የሚሰሩ እንዲሁም በማረሚያ ቤት ጥበቃ ላይ ነበሩ የተባሉ ፖሊሶችም መገደላቸውን ሰምተናል።

* ዛሬ ጠዋት ህዝቡ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ወጥቶ አስክረ ሲሰበሰብ ነበር። ቢያንስ ወደ ሰባት አስከሬን ተገኝተዋል፡፡ የተጎዱትም ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

* በግምት ከእኩለ ሌሊት ስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ሰባት ሰዓት ሰምተን የማናውቅ አይነት የተኩስ እሩምታ ነው ስንሰማ ያደርነው።

ሌላኛው ነዋሪ ፦

- በወረዳው የፖሊስ ጣቢያ ላይም ጥቃት ደርሷል።

- የወረዳው መሳሪያ ግምጃ ቤትም ተሰብሯል መባሉን ጠዋት ሰምተናል፡፡

- ሲንቄ ባንክ ላይም ከፍተኛ የመሰባበር ጉዳት ደርሷል፡፡ ሌሎች ባንኮች ግን ምንም አልሆኑም፡፡

- ታጣቂዎቹ በያቅጣጫው ወደ ከተማው መግባታቸው ነው የተሰማው፡፡ እኛ ወጥተን ማየት ፈጽሞ የማይታሰብ ብሆንም ጠዋት እንደሰማነው ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

- የቆሰሉ ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ አንድ ከታጣቂዎች የሞተ ሰው ግን አስከረኑ እስከ ከሰኣት አልተነሳም፡፡ እኛ ጠዋት እንደተመለከትነው ሰባት አስከሬን ቆጥረናል።

ሌላኛዋ ለደህንነታቸው የሰጉና ስማቸው እንዳይጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ ፦

• ታጣቂዎቹ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንደመሆናቸው በከተማው ውስጥ በነበሩ የመንግስት ጸጥታ ሃይል ሚመለሱ አልነበሩም።

• አሁን ከቤት ለመውጣትም ሰግተናል፡፡ ወንድ ወንዱ ብቻ እየወጣ የሞቱትን ማንሳት ለቅሶ መድረስ ነው ያለው፡፡

• ከተማዋ ጸጥ ብላለች፡፡ ሱቆችን ጨምሮ ምንም የተከፈተ ነገርም የለም።

ኃላፊዎች ምን አሉ ?

📞 ሬድዮ ጣቢያው ለወረዳው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ፋና ረጋሳ ቢደውልም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ለኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛም ስልክ ቢመታላቸውም ስልካቸው አነሳም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዴቼቨለ ሬድዮ ጣቢያ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia