TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ህጋዊ የቤት መሸጥና ማዘዋወር አገልግሎት ከህዳር 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደገና መጀመሩ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፊርማ ያረፈበት መመሪያ ያስረዳል።

መሬታ በሊዝ ጨረታ የማስተላለፍ አገልግሎትም አርብ ህዳር 28/2016 ዓ.ም በይፋ መጀመሩንና የመቐለ ከተማ አስተዳደር 300 ቦታዎቸ በሊዝ ጨረታ ለፈላጊዎች ማቅረቡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ሰነድ መሸጫው ቦታ ድረስ በመሄድ አረጋግጧል።

የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል እንዳረጋገጠው የመሬት ሊዝ ጨረታ ሰነድ በብር 3 ሺህ መሸጡንና ለአንድ ካሬ መሬት የመነሻ ዋጋ ብር  4,500 መቅረቡ ብዙዎቹ አላስደሰተም። 

በተያያዘ ታግዶ የቆየው የተሽከርካሪ  ሽያጭና ዝውውር ተፈቅዷል።

እስከ አሁን ከአንድ ሺህ በላይ የተሰረቁ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬዎች መኖራቸውንና እነዚህ ለመቆጣጠር የመሸጥና የማዘዋወር አገልግሎት ሳይጀመር ለመዘግየቱ ምክንያት እንደሆነ የገለፁት የትግራይ ትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ ሃላፊ አቶ መንግስቱ ፤ አስፈላጊው የማጣራት ተግባር ከተከናወነ በኃላ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ከህዳር 16/2016 ዓ.ም ጅምሮ አገልግሎቱ እንዲቀጥል መወሰኑን አብራርተዋል። 

የመሸጫና ዝውውር አገልግሎቱ እንዲያከናውኑ የተፈቀደላቸው ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በቢሮው ተመዝግበው ለነበሩ ተሽከርካሪዎች ብቻ እንደሆነ ፤ ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በኃላ የተደረገው የሽያጭና ዝውውር አገለግሎት ህጋዊ እንዲሆን ግን ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልገው አቶ ታደለ አክለው ገልፀዋል ። 

ጦርነቱ ከተጀመረ በኃላ ከሌሎች የአገሪቱ አከባቢዎች ወደ ትግራይ የገቡ ህጋዊነታቸው የሚያጠራጥሩ ተሽከርካሪዎች የማጣራት ስራ እንዲካሄድ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አቅጣጫ ሰጥቶበት ወደ ስራ እንደተገባ ሃላፊው መግለፃቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
                                        
@tikvahethiopia            
#ኢንጪኒ

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ አደኣ በርጋ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት የኢንጪኒ ከተማ ባለሥልጣን እና የጸጥታ አስከባሪዎችን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

የከተማው ነዋሪዎች ምን አሉ ?

ስማቸው ለደህንነታቸው ሲባል እንዲገለፅ ያልፈለጉ ነዋሪ ፦

* የሰባት ሰዎች አስከሬን ዛሬ ጠዋት ተገኝቷል።

* ማረሚያ ቤት ተሰብሮ እስረኞች ተለቀዋል።

* ህዳር 28 ቀን ለ29 ቀን 2016 ዓ.ም. አጥቢያ ከሌሊቱ ስድስት ሰኣት ጀምሮ ነው ጥቃት የተፈፀመው።

* የወረዳው ማረሚያ ቤት ተሰብሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ተለቀዋል።

* በታጣቂዎቹ ጥቃት የከተማዋ አስተዳዳሪን (ብርሃኑ ሃብትዬ) ጨምሮ የሰዎች ህይወት አልፏል።

* በተለያዩ ጥበቃ ስራ የሚሰሩ እንዲሁም በማረሚያ ቤት ጥበቃ ላይ ነበሩ የተባሉ ፖሊሶችም መገደላቸውን ሰምተናል።

* ዛሬ ጠዋት ህዝቡ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ወጥቶ አስክረ ሲሰበሰብ ነበር። ቢያንስ ወደ ሰባት አስከሬን ተገኝተዋል፡፡ የተጎዱትም ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

* በግምት ከእኩለ ሌሊት ስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ሰባት ሰዓት ሰምተን የማናውቅ አይነት የተኩስ እሩምታ ነው ስንሰማ ያደርነው።

ሌላኛው ነዋሪ ፦

- በወረዳው የፖሊስ ጣቢያ ላይም ጥቃት ደርሷል።

- የወረዳው መሳሪያ ግምጃ ቤትም ተሰብሯል መባሉን ጠዋት ሰምተናል፡፡

- ሲንቄ ባንክ ላይም ከፍተኛ የመሰባበር ጉዳት ደርሷል፡፡ ሌሎች ባንኮች ግን ምንም አልሆኑም፡፡

- ታጣቂዎቹ በያቅጣጫው ወደ ከተማው መግባታቸው ነው የተሰማው፡፡ እኛ ወጥተን ማየት ፈጽሞ የማይታሰብ ብሆንም ጠዋት እንደሰማነው ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

- የቆሰሉ ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ አንድ ከታጣቂዎች የሞተ ሰው ግን አስከረኑ እስከ ከሰኣት አልተነሳም፡፡ እኛ ጠዋት እንደተመለከትነው ሰባት አስከሬን ቆጥረናል።

ሌላኛዋ ለደህንነታቸው የሰጉና ስማቸው እንዳይጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ ፦

• ታጣቂዎቹ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንደመሆናቸው በከተማው ውስጥ በነበሩ የመንግስት ጸጥታ ሃይል ሚመለሱ አልነበሩም።

• አሁን ከቤት ለመውጣትም ሰግተናል፡፡ ወንድ ወንዱ ብቻ እየወጣ የሞቱትን ማንሳት ለቅሶ መድረስ ነው ያለው፡፡

• ከተማዋ ጸጥ ብላለች፡፡ ሱቆችን ጨምሮ ምንም የተከፈተ ነገርም የለም።

ኃላፊዎች ምን አሉ ?

📞 ሬድዮ ጣቢያው ለወረዳው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ፋና ረጋሳ ቢደውልም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ለኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛም ስልክ ቢመታላቸውም ስልካቸው አነሳም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዴቼቨለ ሬድዮ ጣቢያ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መፍትሄው_ምንድነው?

በአስሩ አማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ከራቁ ወራት አልፈዋል።

ተማሪዎቹ ሳይጠሩ / የሚጠሩበትን ጊዜ ሳያውቁ የፊታችን ሰኞ የ2016 ትምህርት ዘመን 4ኛው ወር ይገባል።

እስካሁን በእነዚህ ተማሪዎች ጉዳይ በይፋ አንዳች የተባለ ነገር የለም።

ተማሪዎቹም ሆኑ ወላጆቻቸው የትምህርታቸው ጉዳይ ቀን ከሌት ሀሳብ የሆነባቸው ሲሆን መንግሥት አሁንም ጊዜው ከዚህ ሳይረፍድ አለኝ የሚለውን መፍትሄ እንዲያሳውቃቸው በተደጋጋሚ እየጠየቁ ይገኛሉ።

በሌሎች የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሰላም አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን አሁን የመግቢያ ጥሪ ያልተደረገላቸው / መቼ እንደሚደረግላቸው እንኳን የማያውቁ ተማሪዎች በምን አግባብ ከሌሎች ተቋማት ተማሪዎች ጋር እኩል ለሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና እንደሚቀመጡ ከአሁኑ ጭንቀት እንደሆነባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ከምንም በላይ ከእድሜ እኩዮቻቸውና ባቾቻቸው ወደኃላ ቀርተው ቤት መቀመጣቸው ለከፍተኛ የስነልቦና ጫና እንደዳረጋቸው በተደጋጋሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት አስረድተዋል።

ተማሪዎቹ በህይወታቸው መቀለድ እንዲያቆም፣ የትምህርታቸው ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ ፣ ትምህርት ሚኒስቴርም በይፋ ምን እያሰበ እንዳለ በመግለጫ እንዲያሳውቃቸው ድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

በክልሉ ያለው ተላዋዋጭ የሆነ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ተቋማት ተማሪዎችን ለመጥራት ፈተና እንደሆነባቸው ከዚህ ቀደም መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#ተክለሃይማኖት_ጠቅላላ_ሆስፒታል

የሳምባ ህክምና ክፍላችን በዘመናዊ መሣሪያዎች የተደራጀና በሃገሪቱ  አንቱታን ያተረፉ የረጅም ዓመት ልምድ ባካበቱት የሳንባ እና ፅኑ ህሙማን ሰብስፔሻሊስት  ዶ/ር  አምሳሉ በቀለ ጥራቱን  የጠበቀ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡

በክፍሉ የሚሰጡ ምርመራዎች እና ህክምናዎች የአስም ፣ የብሮንካይት፣ የሳንባ ኢንፌክሽን፣ የሳንባ ሽፋን ዉሃ መቋጠር፣ የቲቢ፣ የአየር ቱቦ አለርጂ ህክምና፣ ስፓይሮሜትር (የሳንባን ስራ ለማወቅ እና የጉዳቱን መጠን ለመለየት)፣ ጂን ኤክስፕርት (አስተማማኝ የቲቢ ምርመራና መድሃኒት የተላመደ የቲቢ ባክቴሪያ ለመለየት)

📞 8175 / 0940 33 33 33

Facebook: https://www.facebook.com/teklehaimanothospital
Instagram: https://www.instagram.com/teklehaimanotgeneral

Telegram: https://t.iss.one/teklehaimanothospital1

Twitter: https://twitter.com/TeklehaimanotG4
Website: www.teklehaimanothospital.com
E-mail: [email protected]
#SunChips

ከፓፕሪካ እስከ ቶማቶ፣ ለሁሉም ያማረውን መርጦ ይመቻቻል። ከ#ሰንቺፕስ 😋 ጋር #ሰኒሞመንትስ ☀️ #መክሰስTime
From Paprika to Tomato, everyone gets the flavour they desire  with #SUNChips 😋 and #SunnyMoments.☀️

Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia 
" ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ከተመቱ በኃላ ህክምና ቢደረግላቸውም ሊተርፉ አልቻሉም " - ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በኩረ ትጉኃን ዘርዓዳዊት ኃይሉ ተገደሉ።

ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ11 ሰዓት ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመትተው ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው ሊተርፉ ሳይችሉ ቀርቶ ሕይወታቸው ማለፉን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ አሳውቀዋል።

ብፁዕነታቸው የግድያው ምክንያት እንደማይታወቅ ገልጸው በክስተቱ የተሰማቸውን መሪር ኃዘን ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኢኦተቤ ቴቪ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
#EOTC

ቋሚ ሲኖዶስ ነገ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳወቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ነገ መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫው በምን ጉዳይ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ባይገለፅም #በወቅታዊ_ጉዳዮች ዙሪያ እንደሆነ ተነግሯል።

ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ለሚሰጠው መግለጫ መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ላልሆኑና በቤተክርስቲያኗ ህዝብ ግንኙነት ለተመዘገቡ መገናኛ ብዙሃን በስፍራው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

@tikvahethiopia
ሁለት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወንዝ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አለፈ።

በወላይታ ዞን " ሁምቦ " እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ዳርቻ ፎቶግራፍ በመነሳት ላይ የነበሩ ሁለት ተማሪዎች ተንሸራተዉ ወደወንዙ በመግባታቸዉ ህይወታቸው አለፈ።

ሁለቱም ህይወታቸው ያለፈው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች መሆናቸው ተነግሯል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ለአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በጠየቀዉ ድጋፍ መሰረት የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች የወጣቶቹን አስከሬን ዛሬ ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም አዉጥተዉ አስረክበዋል።

ተማሪዎችና ወጣቶች ፎቶ ግራፍ ለመነሳትና ለመዝናናት በሚል ወንዝ አካባቢ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ መሰል አደጋዎች የሚያጋጥሙ በመሆኑ ወንዝ አካባቢና የመዋኛ ስፍራዎች አካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
ነዳጅዎን
በሲቢኢ ብር እና በነዳጅ አፕ ይቅዱ!
መልካም መንገድ!!
=========
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለመጫን ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
****************
‘ነዳጅ’ መተግበሪያን ለመጫን፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች:
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj
• ለአፕል ስልኮች:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926
* በውጭ ምንዛሪ እጥረት ስራውን ያቆመው ማምረቻ !

የኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር በገጠመው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ ምርት ማቆሙን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ከ20 ዓመታት በላይ ቆርኪና ጣሳ በማምረት የሚታወቀው ይህ ፋብሪካ፣ በጣሳ ምርት ላይ የተሰማሩ 33 ሠራተኞችን ከ2016 ዓ/ም እና ከ2017 ዓ/ም በሚቀነስ የዕረፍት ጊዜ እንዲወስዱ ተደርጎ በቤታቸው እንዲቆዩ መደረጋቸውም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ይደነቅ እልፍነው ምን አሉ ?

* ፋብሪካው ለተወሰነ ጊዜ ነው ሥራ ያቆመው።

* ስራ ያቆመው በውጭ ምንዛሪ እጥረት ነው።

ሰራተኞች ምን አሉ ?

- ፋብሪካው ሥራውን ሙሉ ለሙሉ አቁሟል። ሠራተኞችንም እየበተነ ነው።

- በፋብሪካው የቆርኪ ምርት ላይ ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ 15 ሠራተኞች የአገልግሎት ክፍያ ተሰጥቷቸው ተሰናብተዋል።

- የቀጣይ የሥራ ዕጣ ፈንታችን ምን እንደሚሆን ማወቅ አልቻልንም። ግራ ተጋብተናል።

- የቆርኪና የጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ወደ ግለሰብ ከዞረ ጊዜ ጀምሮ የተሻለ ምርት እያመረተ አልነበረም፤ ሠራተኞችንም ቀስ በቀስ ከሥራ ገበታቸው እንዲወጡ ተደርጓል።

- የቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በመንግሥት ሥር እያለ ከ140 በላይ ሠራተኞች ነበሩ።

- የጊዜ ገደብ ሳይሰጠን ነው ከሥራ የተሰናበትነው።

- ጉዳዩን ወደ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሽን (ኢሠማኮ) ለመውሰድ ቀነ ቀጠሮ ይዘናል።

- ከ15 ሠራተኞች ውስጥ ሁለት የሚሆኑት እስካሁን ድረስ የአገልግሎት ክፍያ አልተሰጣቸውም።

- ከዚህ በፊት በመንግሥት ሥር እያለ የተሻለ ምርት በማምረት፦
* ለቅዱስ ጊዮርጊስ፣
* ለሐበሻ ቢራ፣
* ለሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪና ለሌሎች ድርቶች ምርቶቹን ሲያከፋፍል ነበር።

- በመጀመሪያ አንድ ድርጅት ከስሪያለሁ ካለ ቅድሚያ በመንግሥት ኦዲት እንዲሠራ ከተደረገ በኋላ የ3 ወራት ጊዜ በመስጠት ማባረር አለበት።

- በወቅቱ የኢንዱስትሪው ባለቤት የሆነው ግለሰብ በ2 ቀናት ልዩነት ውስጥ ሠራተኞችን በመጥራት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ ኪሳራ ስለደረሰብኝ የቆርኪ ሠራተኞች ልበትን ነው ያለው።

- በድርጅቱ በበርታ ኤጀንሲ ሥር ሆነው የተቀጠሩ 9 ሴት ሠራተኞች የ1 ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው ሲሆን " ለምን አትከፍሉንም? " የሚለው ጥያቄ ሲያቀርብ " ኤጀንሲው ይክፈላችሁ " የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን። 

ከዚህ በፊት የቆርኪ ማምረቻ በፈረቃ 700,000 ቆርኪዎች የማምረት አቅም ኖሮት ከጀመረ በኋላ፣ በሒደት 1.4 ሚሊዮን ቆርኪ የማምረት አቅም ከፍ እንዲል ተደርጎ ሲያመርት መቆየቱ ይታወሳል፡፡

መንግሥት በኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር ላይ የነበረውን የ75 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ በ130 ሚሊዮን ብር በመሸጥ ሙሉ በሙሉ ይዞታውን ለኩባንያ ማስረከቡ ይታወሳል፡፡

መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray

" ትግራይ ውስጥ 269 አምቡላንሶች ነበሩ ለቅድመ ሆስፒታል ድንገተኛ ህክምና የምንገለገልባቸው አሁን በእጃችን ያሉን 90 ብቻ ናቸው " - አቤኔዘር እጸድንግል (ዶ/ር)

የአምቡላንሶች ቁጥር በጦርነቱ ወቅት መመናመንና፣ ደመወዝ ያልተከፈላቸው የጤና ባለሙያዎች ከቦታ ቦታ መሰደድ በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ ፈተና እንደሆነበት የትግራይ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የጤና ቢሮው የድንገተኛ ሕክምና አስተባባሪ አቤኔዘር እጸድንግል ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

- የድንገተኛ ሕክምና ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ ችግር ነበር። ከሁሉ በላይ ደግሞ የወላድ እናቶች በቂ አገልግሎት ሲሰጥ አልነበረም። ዋነኛው፣ አንደኛውና ቀደኛ ምክንያቱ የአምቡላንስ እጥረት ችግር ነው። ያለ አምቡላንሶች ድንገተኛ ሕክምና የለም።

- ትግራይ ውስጥ 269 አምቡላንሶች ነበሩ ለቅድመ ሆስፒታል ድገተኛ ሕክምና የምንገለገልባቸው፤ አሁን በእጃችን ያሉን 90 ብቻ ናቸው። በጣም ጥቂት አምቡላንሶች ናቸው የቀሩን።

- በአስተዳደራዊ፣ በነዳጂ፣ በበጀት ችግሮችና በተለያዩ ምክንያቶች 90ዎቹ አምቡላንሶችም ራሱ ለሁሉም አካባቢዎች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።

- ኅብረተሰቡ ሊያገኝ የሚገባው አገልግሎት እጅግ በጣም ቀንሶ ነው ያለው። ከዚህ በፊት በአንድ ጊዜ  በኳርተር ኦልሞስት እስከ #500,000 የሚጠጉ ድገተኛ ታካሚዎች ናቸው የነበሩን፤ አሁን በተመሳሳይ ወቅት ወደ ሕክምና ተቋማት የሚመጡት ድንገተኞች #40,000ም አይሞሉም። በጣም በከፍተኛ ሁኔታ ታካሚው ቀንሷል።

- የጤና ባለሙያዎችም ከቦታ ቦታ መሰደድ በሕክምና አገልግሎት ላይ ፈተና ሆኗል።

- የጤና ባለሞያዎቹ የተሻለ ኑሮ ለመኖር ሲሉ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተለያዩ ቦታዎች ማለትም ወደ መሀል አገር ይሰደዳሉ ፤ ይህን የሚያደርጉት ደግሞ #በጀት ስለሌለ #በቂ ደመወዝ ስለማያገኙ ነው።

* ይህ ሁሉ ተደማምሮ የአገልግሎት ጥራት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅእኖ አድርጓል። ለቀጣይ ይሻሻላል፣ ለመሻሻልም ጊዜያዊው መግሥትም ብዙ እየሰራ ነው።

የአምቡላንሶቹ ቁጥር የቀነሰው በጦርነቱ ወቅት ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው አቤኔዘር (ዶ/ር) ፦

" አዎ በጦርነቱ ወቅት በርከት ያሉ አምቡላንሶች ተወስድልውብናል። በርከት ያሉ ደግሞ ተቃጥለዋል። በእኛ እጅ ያሉት 90 ብቻ ናቸው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በትግራይ ክልል በጦርነቱ ወቅት ከ80 በላይ የጤና ተቋማት፣ እንዲሁም የሕክምና መሣሪያዎች ላይ ደረሰ የተባለውን ውድመት ተከትሎ ከፕሪቶሪያው ስምምነት ወዲህ የተሻለ ቢሆንም የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ፈተኝ ችግሮች ማጋጠማቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።

መረጃው አዘጋጅቶ ያቀረበው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ኤክሶደስ_የፊዝዮቴራፒ_ልዩ_ክሊኒክ

በውቢቷ ባህርዳር አዲስ ቅርንጫፍ ከፍተናል ፤ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ለወገብ ህመም
- ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ   ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር
- ለፊት መጣመም
- ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- ለስፖርታዊ ጉዳቶች
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች
አድራሻችን፦ ቁጥር 1_ አዲስ አበባ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን ፤ ቁጥር 2_ ባህርዳር ቀበሌ 14 አልዋቅ ሆቴል አጠገብ ስልክ ቁጥር 0979099909 / 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic