TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በደቡብ፣ ሐረሪ፣ እና ጋምቤላ ክልሎች የ2013 የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል።

#ሐረሪ

በሐረሪ ክልል 56 በሚሆኑ የግል እንዲሁም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ነው ተማሪዎች ፈተናው እየወሰዱ የሚገኙት ፤ በአጠቃላይ 5160 ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ተገልጿል።

ፈተናውን ለመስጠት 214 መምህራንና 24 የፈተና ጣቢያዎች መዘጋጀታቸው ተነግሯል።

#ጋምቤላ

በጋምቤላ ክልል ለ8ኛ ክፍል ፈተና 10 ሺህ 319 ወንድ እና 7 ሺህ 639 ሴት ተማሪዎች በድምሩ 17 ሺህ 958 የቀንና የማታ ተማሪዎች ተቀምጠዋል።

ፈተናው እየተሰጠ የሚገኘው በ186 የፈተና ጣቢያዎች ሲሆን 523 ፈታኞች ተሰማርተዋል።

#ደቡብ

በደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ዞኖች ከዛሬ ጥዋት አንስቶ እየተሰጠ ቢሆንም ምን ያህል ተማሪ ለፈተናው እንደተቀመጠና በስንት ጣቢያ ፈተናው እየተሰጠ እንደሆነ ይፋዊ መረጃ ማግኘት አልተቻለንም።

መረጃው የየክልሎቹ ትምህርት ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SafaricomEthiopia #Harari ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በሐረሪ ክልል መጀመሩን አሳውቋል። ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት መሆኑን ተገልጿል። በሐረሪ ክልል የደንበኞች…
#Harari #SafaricomEthiopia

በሐረሪ ክልል ፤ የ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " መለያ በተለጠፈባቸው ሁሉም መደብሮች እና ሱቆች ሲም ካርድ እና የአየር ሰዓት መግዛት ይቻላል ተብሏል።

በተጨማሪ በአራተኛ እና በሥላሴ አካባቢ ባሉት ሁለት የሽያጭ ማዕከሎቹ የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች ድጋፍ አገልግሎት በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጥሪ ማዕከል በተለያዩ ቋንቋዎች ፦
- በአማርኛ፣
- በአፋን ኦሮሞ ፣
- በሱማሊኛ፣
- በትግርኛ እና እንግሊዝኛ አገልግሎት የማግኘት አማራጭ ያላቸው ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞችን በ 👉 700 ላይ በመደወል ማናገር ይቻላል።

#SafaricomEthiopia #ሐረሪ #Harari

@tikvahethiopia
#ሐረሪ

" የሽንኩርት ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ወስደናል " - የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ

የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ ፤ " የሽንኩርት ዋጋን ያለቅጥ አንረዋል " ባላቸው የሐረር ከተማ ነጋዴዎች ላይ የእስር ዕርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

በዳቦ ነጋዴዎችም ላይ ተመሳሳይ ዕርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል።

የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ " የሽንኩርት ዋጋን ያላግባብ ያስወድዳሉ " ያላቸውን 3 ዋና ዋና ነጋዴዎችን ጨምሮ 17 የሽንኩርት አከፋፋዮችን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ማድረጉን ገልጿል።

በሽንኩርት ነጋዴዎቹ ላይ ዕርምጃ ከመወሰዱ በፊት ቀደም ብሎ የማወያየት ሥራ መከናወኑን አመልክቷል።

የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ሸሪፍ ሙሜ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፦ " ባቢሌ አካባቢ የተፈጠረውን የአንድ ቀን ግጭትና መንገድ መዘጋት ተጠቅመው በሽንኩርት ላይ የተጋነነ ዋጋ ጨመሩ፡፡

ነጋዴዎቹን ቢሮ ድረስ ጠርተን ከማወያየት ባለፈ ቦታው ድረስ ባለሙያ በመላክ ሁኔታውን ገምግመናል፡፡

በጉዳዩ ላይ በመተማመን ዋጋውን ለማስተካከል ቃል ገብተው ቢሄዱም፣ ዋጋውን ባለማስተካከላቸው ወደ ዕርምጃ ተገብቷል። " ብለዋል።

ዕርምጃ የተወሰደባቸው የሽንኩርት ነጋዴዎቹ በሐረር ከተማ ብቻ ሳይሆን፣ በዙሪያው ባሉ አካባቢዎችም የማከፋፈል ሥራ የሚሠሩ ዋና ዋና ነጋዴዎች መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

ከ110 ብር እስከ 150 ብር አሻቅቦ የነበረው የአንድ ኪሎ የሽንኩርት ዋጋ ከዕርምጃው በኋላ መስተካከሉን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ ፤ ዳቦ ቤቶችን እና ነጋዴዎችን በቀጣይ ሳምንት በቢሮው ሰብስቦ እንደሚያነጋገር አሳውቋል።

የዳቦ ግራምና ዋጋ የሚያጭበረብሩ እንዲያስተካክሉ የአንድ ሳምንት ወይም የአሥር ቀን ገደብ ይሰጣል ብሏል።

ማስተካከያ ባላደረጉ ላይ ግን ልክ እንደ ሽንኩርት ነጋዴዎቹ ሁሉ ዕርምጃ ይወሰዳል ሲል ማስጠንቀቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

#ሽንኩርት ፦ የሽንኩርት ዋጋ በመዲናዋ ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች ዋጋው አልቀመስ ካለ ሰንበትበት ብሏል። በርካቶች በዋጋው ንረት ሸምቶ ለመግባት ማቸገራቸውን ይገልጻሉ። እርሶስ በጉዳዩ ላይ ምን ይላሉ ? በዚህ ይነጋገሩ @BirlikEthiopia

@tikvahethiopia