TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ፦ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እውቅናና ሽልማት ተበረከተላቸው።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዛሬ  ፤ ' ቀጣይ ምዕራፍ ለሁለንተናዊ ለውጥ! ' በሚል መሪ ቃል የምስጋናና የሰላም ኮንፈረንስ በሚሊኒየም አዳራሽ አካሂዶ ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ " ከለውጡ ወዲህ ለተገኘው ፍትሃዊ አገልግሎት እና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ጥያቄ ለሰጡት ምላሽ " በሚል ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ እና ለከንቲባ አዳነች አቤቤ የእውቅና ሽልማት አበርክቷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በስፍራው ተገኝተው ሽልማታቸውን ተረክበዋል።

በምን ጉዳይ ምላሽ ተሰጠ ተባለ ?

በመድረኩ ላይ ፦

- የህዝበ ሙስሊሙ መሪ ተቋም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ፅ/ቤት ህጋዊ እውቅና ያለው ተቋም ሆኖ እንዲመሰረትና ተቋማዊ አደረጃጀቱ እንዲሻሻል መደረጉ።

- በሸሪያ ህግ የሚመሩ ወለድ አልባ ባንኮች እንዲመሰረቱ መደረጉ።

- በአዲስ አበባ ለህዝበ ሙስሊሙ ለማህበራዊ አገልግሎት የሚውሉ የቦታ ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ በመመለሳቸው የሚሉት ተነስተዋል።

በሌላ በኩል፤ በታላቁ አሊም ሀጅ ሙሃመድ ሳኒ ሀቢብ ስም ማእከል ሊገነባ መሆኑ ተገልጿል።

የማዕከሉ ግንባታ በለሚ ኮራ ክፍለ ከተማ በአራት ሺ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ይሆናል። ማእከሉን በሃላፊነት እንዲያስገነቡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሱልጧን ሀጅ አማን ለኢትዮጵያ  እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሀጅ ኢብራሂም አስረክበዋል።

ፎቶ ፦ የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ቢሮ

@tikvahethiopia
#Tigray

አቶ ጌታቸው ረዳ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ ሪፈረንደም አይታሰብም አሉ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፦

- የትግራይ ግዛቶችን በወረራ የያዙ ኃይሎች ሳይወጡ፤

- ተፈናቃዮች ወደ ቀደመው ቄያቸው ሳይመለሱ ሪፈረንደም የሚባል ነገር #አይታሰብም ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው ይህንን ያሉት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሚስተር ኤርቪን ጆዜ ማሲንጋ ከተመራ የልኡክ ቡድን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ላይ የአሜሪካ መንግስትና ህዝብ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲፈረም ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ ከልኡካን ቡድኑ ጋር አህጉርና ዓለም አቀፍ እንዲሁም አከባቢያዊ የፀጥታ ጉዳዮችና በክልሉ ስላጋጠመው ድርቅ አንስተው መወያየታቸው ታውቋል።

የትግራይ ግዛታዊ አንድነት በህገ መንግስቱ መሰረተ ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት መመለስ አለበትም ብለዋል። 

" የኤርትራ እና የአማራ ሃይሎች በወረራ ከያዙት የትግራይ ግዛት ሳይወጡ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ ለሌላ ስቃይ መዳረግ ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " የሪፈረንደም ጉዳይ መነሳት ካለበት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት በሃይል የተያዘው መሬት ተለቆ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ተመልሰው በምርጫ ህጋዊ መንግስት ከተቋቋመ በኃላ ነው " ብለዋል።   

ከቄየው የተፈናቀለው ህዝብ በቂ የእርዳታ አቅርቦት የማያገኝ በተለይ በአሁኑ ሰዓት በክልሉ የተከሰተው ድርቅ ተጨምሮበት ኑሮው እጅግ አስከፊና ውስብስብ አድርጎታል በማለት የገለፁት አቶ ጌታቸው የአሜሪካ ህዝብና መንግስት የጉዳዩ አሳሳቢነት በመገንዘብ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል። 

አምባሳደር ኤርቪን ጆዜ ማሲንጋ ምን አሉ ?

- የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በጥብቅ እንደሚከታተሉት ገልጸዋል።
- መንግስታቸው ለስምምነቱ ተግባራዊነትና የትግራይ መልሶ ማልማትን እንደሚደግፍና እንደሚሰራ ቃል ገብተዋል።

መረጃውን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት ፅህፈት ቤት መግለጫን ዋቢ በማድረግ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
" የባህል ህክምና እንሰጣለን የሚሉ አጭበርባሪ ግለሰቦች እየተበራከቱ ነው " - የአ/አ ባህል መድኃኒት አዋቂዎች ማህበር

የአዲስ አበባ ባህል መድኃኒት አዋቂዎች ማህበር ፤ የባህል ህክምና እንሰጣለን የሚሉ አጭበርባሪ ግለሰቦች እየተበራከቱ ነው ብሏል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ ፌስ ቡክ እና ቴሌግራም ያሉ ማኅበራዊ መገናኛዎችን በመጠቀም " የባህል መድሃኒት አዋቂዎች ነን " የሚሉ እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡

እነዚህ መድሃኒት አዋቂ ነን የሚሉ ሰዎች መድሃኒት እናዘጋጅላቸዋለን የሚሏቸው ጉዳዮች ያልተለመዱና " መድሃኒት " ይፈታቸዋል የማይባሉ ዓይነት ናቸው፡፡

ለምሳሌ ፦
- ለገበያ፣
- ለስልጣን፣
- ለግርማ ሞገስ፣
- ትዳር እምቢ ላለው፣
- ወደ ውጭ ለሚጓዝ፣
- ሎተሪ እንዲደርሳችሁ
- ለቤቲንግ
- ለእቁብ
- ለድምፅ ወዘተ.  የሚሉ አጓጊ ቃላትን ይጠቀማሉ ተብሏል።

መድሃኒት አዋቂ ነን ከሚሉት ሰዎች " መርጌታ " የሚል መንፈሳዊ ማዕረግን የሚጠቀሙት ብዙዎቹ ሲሆኑ በመቶ ሽዎች ተከታዮች ባሏቸው የማኅበራዊ መገናኛዎች ላይ ስልክ ቁጥሮቻቸውን ከመለጠፍ ባለፈ የሥራ አድራሻቸውን በግልጽ አያስቀምጡም ተብሏል።

ስልክ ሲደወልላቸው " ምን መድሃኒት ትልጋለህ ? " ብለው ይጠይቁና ለማንኛውም ዓይነት ችግር መፍትሔ እንዳላቸው ይናገራሉ ፤ ባለጉዳዩ ክፍያ #በባንክ እንዲያስገባ መድሃኒቱንም በመልክተኛ እንደሚልኩ ይገልጻሉ።

በዚህ መልኩ በርካታ ማጭበርበሮች የደረሰባቸው ሰዎች ስለመኖራቸው ተነግሯል።

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ የአዲስ አበባ የባህል መድሃኒት አዋቂዎች ማህበር ፕሬዝዳንት መሪጌታ መንግሥቱ ፤ እንዲህ ያለ ሥራ የሚሠሩ አጭበርባሪዎች መበራከታቸውን ጠቁመዋል፡፡

" በራሴ ሥም መርጌታ መንግስቱ የባህል መድሃኒት አዋቂ " የሚል ገጽ ተከፍቶ ሰዎች እየተጭበረበሩ ነው ብለዋል፡፡

ከመንግስት ጋር እየተነጋገርን እነዚህን አጭበርባሪዎች ለማስታገስ እየሞከርን ነውም ሲሉ ተናግረዋል።

እነዚህ " መድሃኒት " አዋቂ ነን ብለው የሚያስተዋውቁ ሰዎች እንፈውሳቸዋለን የሚሏቸው በግልጽ መድሃኒት እንደሌላቸው የተነገረላቸው በሽታዎች ለምሳሌ ፦ ኤች አይ ቪ. እና ካንሰር ... ወዘተ. እንዲሁም እንደ በሽታ ሊታዩ የማይችሉ ወይም በሽታ ስለመሆናቸው ያልተረጋገጡ ለሆኑ ነገሮች ለምሳሌ ፦
* ራዕይ ለማዬት፣
* ሌሊት ሽንቱ ለሚያመልጠው፣
* ለወር አበባ፣
* ለንቃተ ህሊና፣
* ትምህርት ለማይገባው፣
* ለሥራ ዕድል፣
* ለመስተፋቅር ወዘተ. የሚሉ አሉ፡፡ ህክምና ፈላጊዎች እንዲህ መሰል በሆኑ አጭበርባሪዎች እንዳይታለሉ ሲሉ መሪጌታ መንግሥቱ (የአ/አ የባህል መድሃኒት አዋቂዎች ማህበር ፕሬዝዳንት) ተናግረዋል።

ይህ መረጃ #ባለቤትነቱ የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬድዮ ' እውነትን ፍለጋ ' የተሰኘ ፕሮግራም / ደሳለኝ ስዩም ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ድሬዳዋ

" ለከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የምንሰጠው #ክብር ትልቅ ነው " - ድሬዳዋ

በመላው ኢትዮጵያ ካሉ ከተሞች ለእንግድነትም ሆነ እዛው በከተማዋ እየሰሩ ለመኖር አስተማማኝ የሰላም እና ፀጥታ ደህንነት ካለባቸው ከተሞች አንዷ ድሬዳዋ ናት።

ከተማይቱ በአንድ ወቅት አጋጥሟት ከነበረው የፀጥታ መንገጫገጭ ከወጣች በኃላ ላለፉት ዓመታት እጅግ አስተማማኝ ደህንነቷና ሰላሟን አስጠብቃ ትገኛለች።

በማታም ሆነ በቀን በከተማዋ ውስጥ ለመንቀሳቀስ እንዲሁም ሰርቶ ለመግባት ያማታሰጋ ሆና ተሰርታለች።

ከዚህ ባለፈም ፤ #የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት በሆነው ዋና መንገድ ላይ በመገኘቷ በርካታ አሸክርካሪዎች በየዕለቱ ታስተናግዳለች።

ብዙ ርቀት በአስቸጋሪ የአየር ፀባይ የሚጓዙ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ደህንነታቸው እንዲጠበቅና ፤ በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚስተዋለው የተንዛዛ የትራፊክ ፖሊስ ጭቅጭቅ እንዳይኖርም እያደረገች ትገኛለች።

የድሬዳዋ ከተማ የትራፊክ ፖሊስም ረጅም መንገድ በረሃና አስቸጋሪ የአየር ንብረት በመቋቋም የሀገሪቱን ገቢ እና ወጪ ንግድ ለሚያፋጥኑ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የሚሰጠው #ክብር ትልቅ መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን ማንኛውም አሽከርካሪ በከተማው ውስጥ ሆኖ ችግር ከገጠመው ለማስተካከል ዘውትር ዝግጁ ነኝ ብሏል።

#ቪድዮ፦ ከወር በፊት የከተማይቱ አመራሮች ረጅም ርቀት ተጉዘው ድሬዳዋ ከተማ የደረሱ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎችን ለማክበር የታሸገ ውሃ ሲሰጧቸው የሚያሳይ ነው።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማይቻለውን የምታስችል . . .  የዕድሜ ልክ መተማመኛ!!
ማን እንደ እናት!
እናት ባንክ
#AddisAbaba

25 የግል ኮሌጆች ለ2016 ዓ.ም ምንም አይነት አዲስ ሰልጣኝ መቀበል እንዳይችሉ እግድ ተጣለባቸው።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ፤ የግል ኮሌጆች የምዝገባ ፍቃድ ለመውሰድ መረጃ እንዲያቀርቡ በደባድቤ የጠየቃቸው ኮሌጆች መረጃ ለማቅረብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው እግድ እንደጣለባቸው አሳውቋል።

በመሆኑም፦

- ኩዊንስ ኮሌጅ ሃና ማርያም ካምፓስ
- ኩዊንስ ኮሌጅ መድሃኒዓለም ካምፓስ
- ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ አቢቹ ካምፓስ
- ሮያል ኮሌጅ ፒያሳ ካምፓስ
- ማይክሮሊንክ ኮሌጅ
- ላየን ኢትየጵያ ሆቴልነና ቢዝነስ ኮሌጅ 4 ኪሎ
- ዩኒየን ቪዥን ኮሌጅ
- ትሮፒካል ኮሌጅ ኦፍ ሚድሲን
- አዲስ ኮሌጅ
- ኩዊንስ ኮሌጅ ቤቴል ዐለም ባንክ ካምፓስ
- ኦርቢት ኮሌጅ
- ባዮስ ኮሌጅ
- ብራይት ኮሌጅ ጀሞ
- ስታንዳርድ ኮሌጅ ዩኒቨርሳል
- አይ ኪዉ ኮሌጅ
- ኬቢ ኢንተርናሽናል የቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
- ካፒታል ሆቴልና ማኔጅመንት ኮሌጅ
- አንድነት ኢንተረናሽናል ኮሌጅ ላም በረት
- ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ፊንፊኔ ካምፓስ
- ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ላንቻ ካምፓስ
- ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ካራ አሎ ካምፓስ
- ኩዊንስ ኮሌጅ መካኒሳ ካምፓ
- ኩዊንስ ኮሌጅ ልደታ ካምፓስ
- ኩዊንስ ኩሌጅ ሜክሲኮ ኬኬር በባለስልጣን መ/ቤቱ በመመሪያ መሰረት የምዘና ግብ ሳያሳኩና የምዝገባ ፍቃድ ሳያገኙ ለ2016 ዓ.ም ምንም አይነት አዲስ ሰልጣኝ መቀበል እንደማይችሉ አሳስቧል።

ተቋማቱ ለመጨረሻ ጊዜ አስፈላጊውን የሰልጣኞች የመረጃ እስከ 30/03/2016 ዓ.ም እንዲያቀርቡ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን ይህ ባያደርጉ በመመሪያ 02/2012 እና 01/2014 መሰረት እውቅና ፍቃዳቸው እንደሚሰረዝ አስጠንቅቋል።

(የእግዱ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የፌስቡክ ገፅን ይወዳጁ፣ በመሳተፍ ይሸለሙ!  https://www.facebook.com/globalbankethiopia

#Global_Bank_Ethiopia #Shared_Success #Bank_in_Ethiopia
#SafaricomEthiopia

ልጆቻችን ትምርታዊ ነገሮችን እንዲማሩ እንዲሁም የሚወዱትን አዝናኝ ቪደዮዎች እንዲመለከቱ ለቤትም ሆነ ይዘነው ለመንቀሳቀስ የሚመቸውን ቅመም MiFi ዛሬውኑ ወደ ሳፋሪኮም ሱቆች ጎራ ብለን በመግዛት ማርሻችንን አንቀይር

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

#SafaricomEthiopia
#FurtherAheadTogether
#ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፦

#አማራክልል

በአዊ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ አምበላ ቀበሌ በዚገም ወረዳ ሶሪት ቀበሌ ከጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ቀናት በተፈጠረው ብሔር ተኮር ግጭት ሞት እና የአካል ጉዳት እንዲሁም በኢንቨስትመንት ቦታዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ፣ ፈጣም ሰንቶም እና በቆጣቦ ቀበሌዎች ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. እና በኅዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም. " ኢመደበኛ " የአማራ ታጣቂዎች መሆናቸው የተገለጸ ቡድኖች በሰነዘሩት ብሔር ተኮር ጥቃት እና ይህንኑ ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት በርካታ ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ደርሷል።

በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ነዋሪዎች ተፈናቅለው በቡሬ ዙሪያ ወረዳ በሚገኙ አጎራባች ቀበሌዎች እና ወደ ኦሮሚያ ክልል ለመሄድ ተገደዋል። የቀንድ ከብቶች ተዘርፈዋል።

#ቤኒሻንጉልጉሙዝ

አሶሳ ዞን፣ ኦዳ ብልድግሉ ወረዳ ሥር በሚገኙ ቤልሚሊ፣ አልከሻፊ እና ቤላደሩ ቀበሌዎች በሚኖሩ የቤኒሻንጉል ብሔር ተወላጆች እና አብረው በሚኖሩት የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ላይ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት አካባቢ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ-ሸኔ) ታጣቂ ቡድን አባላት በተፈጸመ ጥቃት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

በጥቃቱ 17 ሰዎች መገደላቸው ፣ አንድ ሽማግሌ ታፍነው መወሰዳቸው፣ በ7 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ መሆኑን ማወቅ ተችሏል።

በሦስቱ ቀበሌዎች ያሉ መንደሮች በአብዛኛው የተቃጠሉና የወደሙ መሆኑን፣ የእርሻ ሰብልና የቤት እንስሳትን ጨምሮ የንብረት ውድመት ደርሷል።

የቀበሌዎቹ ነዋሪዎች ጥቃቱን በመሸሽ ወደ አጎራባች ቀበሌዎችና በአቅራቢያው ወደ ሚገኘው መነሲቡ ወረዳ (ኦሮሚያ ክልል) ተፈናቅለዋል።

#ኦሮሚያክልል

- በአርሲ ዞን፣ ሸርካ ወረዳ ኅዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም. በጢጆ ለቡ ቀበሌ በግምት ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት በኋላ ማንነታቸው በውል ያልተለየ ታጣቂዎች በፈጸሙት ብሔር/ማንነት ተኮር ጥቃት 7 የአንድ ቤተሰብ አባላት እና 3 ጎረቤቶቻቸው ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ሰዎችን ገድለዋል።

በዚያው ዕለት ታጣቂዎቹ በሶሌ ዲገሉ ቀበሌ ቢያንስ 12 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል።

በሶሌ ዲገሉ ቀበሌ ከተገደሉ 12 ሰዎች መካከል አሥራ አንዱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው።

በኅዳር 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በወረዳው በኮኘ ቀበሌ ታጣቂዎቹ በፈጸሙት ጥቃት የአንድ ቤተሰብ አባላት የነበሩ 8 ሰዎችን ገድለዋል።

ጥቃት አድራሾች ሟቾችን ከቤት እያስወጡ #አሰልፈው_እንደገደሏቸው፣ የተወሰኑትም በቤታቸው ውስጥ እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።

ከሟቾች መካከል #ጨቅላ_ሕፃንን ጨምሮ ነፍሰጡር ሴቶች እና ከ80 ዓመት በላይ የሆናቸው አረጋዊ ይገኙበታል፡፡

ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም ተደጋጋሚ ዛቻ እየደረሳቸው መሆኑን ለኮሚሽኑ ገልጸው፤ መንግሥት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል፡፡

በቄለም ወለጋ ዞን፣ ጊዳሚ ወረዳ፣ የመካነ ኢየሱስ ቤተ-ክርስቲያን አባላት የነበሩት 9 ምዕመናን፣ ሽማግሌዎች፣ የወጣቶች ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ሌሎች አገልጋዮችን ኅዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ከሌሊት 8፡00 ሰዓት አካባቢ እስካሁን ማንነታቸው ባልተለዩ በታጠቁ ቡድኖች ተገድለዋል።

ግድያው የተፈፀመድ መላኮ መናሞ ቀበሌ ባለው ጫካ ውስጥ ሲሆን ገዳዮችን  አስክሬናቸውን መጣላቸው ለማረጋገጥ ተችሏል።

(የኢሰመኮ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia