TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Academic Calendar for 2018-19 Academic Year (JU).pdf
226 KB
#update Jimma University Academic Calendar for 2018/19

© #Murad form JU
@tsegabwolde @tikvahethipia
#DireDawa

" በወንጀል ተግባሩ ላይ የተሳተፉ የፖሊስ አመራር እና አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው ወደ መጠናቀቁ ነው " - ድሬ ፖሊስ

ከሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ አንድ ወጣት በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊስ አባላት ድብደባ መገደሉ በርካቶችን አስቆጥቷል ፤ አሳዝኗል።

በተለይ ገንደቦዬ ዛሬም ድረስ ሀዘን ላይ ናት።

የ1 ልጅ አባት የሆነው ወጣት ሙራድ መሀመድ (አሳዶ) ከሰሞኑን በፖሊስ ድብደባ ለሞት መዳረጉ ተነግሯል።

የቅርብ ወዳጆቹ ፥ " ሙራዴ ከሰው ጋር ተግባቢ ፤ በሚኖርበት አካባቢ ገንደቦዬ ላይም የሚታወቅ ፤ የሚወደድ ወንድማችን የሰፈራችን ድምቀት ነበር። ህግ አለባት በምንልበት ከተማችን ያውም ደግሞ ህግ አስከባሪ ተብሎ ዩኒፎርም በለበሱ ፖሊስ አባላት በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድቦ ተገደለ መባሉ እጅግ በጣም አስደንግጦናል፣ አሳዝኖናል ፣ አስቆጥቶናል " ብለዋል።

" የተፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ሰዎች በፖሊስ እና የህግ የበላይነት ላይ ጥያቄ እንዲያነሱ የሚያደርግ ነው። ሙራድ ሰላማዊ ህይወቱን እየመራ ባለበት ነው ይህ ግፍ የተፈጸመው " ሲሉ አክለዋል።

" ፍትህ ሊሰጥ ፤ እውነት ሊወጣ ፣ ወንድማችንን ለሞት የዳረጉት የሚገባቸውን ቅጣት ሊያገኙ ይገባል " ሲሉ አክለዋል።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፥ " ወጣት ሙራድ መሀመድን በግል ቂም በቀል ተነሳስተው ኢሰብዓዊ በሆነ መልኩ በመደብደብ ፣ ለሞት በመዳረግ አስነዋሪ ተግባር የፈጸሙ አባላቶችን በቁጥጥር ስር አውለን ምርመራ በማጣራት ላይ ነን " ሲል መግለጫ አውጥቷል።

ድርጊቱ " ጥቂት " ሲል በጠራቸው የፖሊስ አባላት መፈጸሙን አመልክቷል።

ወጣት ሙራድ በፖሊስ አባላት ተደብድቦ ለሞት በመዳረጉ እጅግ ማዘኑን ገልጾ " ጠቅላይ መምሪያውን በፍጹም የማይወክል ነው " ብሏል። " አስነዋሪ " ሲል የጠራውን የወንጀል ተግባርም አውግዟል።

አሁን ላይ በወንጀል ተግባሩ ላይ የተሳተፉ የፖሊስ አመራር እና አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው ወደ መጠናቀቁ እንደሆነ ገልጿል።

ወጣቱ ተደብድቦ ለሞት ከተዳረገ በኃላ ስርዓተ ቀብሩ በተፈጸመበት ወቅት የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀር ፤ " ግለሰባዊ የቂም በቀል ጥላቻ ነው የመንግሥትን ልብስ ሽፋን አድርጎ የተፈጸመው " ያሉ ሲሆን ድብደባውን ፈጽመው ሙራድን ለሞት የዳረጉት 3 የፖሊስ አባላት እንደሆኑ ገልጸዋል።

" ጣቢያ አላመጡትም ፤ ከዚራ አላመጡትም እኛም ምንም መረጃ አልነበረንም ፤ ወስደው በድብደባ ነው የሞተው። ማታ ጤና ጣቢያ መልካ ላይ ነው የተወሰደው ከዛ በኃላ ነው መረጃው የደረሰን " ብለዋል።

በሙራድ መሀመድ ህልፈት ሀዘናቸውን ገልጸው " ልጅ አለው፣ ሚስት አለው እናትም አለው ቤተሰቦቹን የማገዝ እና መርዳት ኃላፊነት አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።

#Murad #DireDawa #Police

@tikvahethiopia