TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሶሳ🔝

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግጭት የተጠረጠረን  አንድ ግለሰብ #በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ሰይፈዲን_ሃሩን ዛሬ ለኢዜአ እንዳስታወቁት ፖሊስ ሰሞኑን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ግጭት ለሶስት ተማሪዎች ሞትና በሌሎችም ለደረሰው ጉዳት የጠረጠረውን አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡

ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ “ታምሚያለሁ “ በሚል መድኃኒት ለመውሰድ በጸጥታ ሃይሎች ታጅቦ ወደ መኖሪያ ቤቱ ከሄደ በኋላ በመኖሪያ ቤቱ ያስቀመጠውን መሣሪያ በማቀባበል በጸጥታ ኃይሎች ላይ #ጥቃት ለመፈጸም ሙከራ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡

የግለሰቡ መኖሪያ ቤት ሲፈተሽ የተለያዩ ሀሰተኛ መታወቂያዎች መገኘታቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነር ሰይፈዲን የሚጠቀምበትን ኮምፒዩተር ጨምሮ የጸጥታ ሃይሎች ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረበት ክለሽንኮብ መሣሪያም በቁጥጥር ሥር መዋሉን አስረድተዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ግጭት በተጠረጠሩ ሌሎች ግለሰቦች ላይ ፖሊስ ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቀዋል፡፡

በአሶሳ ዩኒቨርስቲ ባለፈው ማክሰኞ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የሶስት ተማሪዎች ህይወት ማለፉና በሌሎች ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
ፎቶ፦ TIKVAH-ETH(AB)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀሰተኛ መረጃ ጥቃት ደረሰ-አዳማ‼️

ከህገ-ወጥ የህጻናት ዝውውር ጋር በተያያዘ በተከሰተ የተሳሳተ መረጃ ምክንያት #በአዳማ ከተማ የገዛ ልጃቸውን ይዘው ሲጓዙ በነበሩ አባት ላይ #ጥቃት ደረሰ።

ህብረተሰቡ በሃሰተኛ ወሬዎች ምክንያት ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የከተማው ፖሊስ አሳስቧል።

አቶ #ግዛቸው_ወርቁ የተባሉ አባት ታህሳስ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ተኩል ላይ በአዳማ ከተማ ቀበሌ 13  አገር ሰላም ነው ብለው ልጃቸውን ከትምህርት ቤት ለማምጣት ይሔዳሉ።

ሌላ ጊዜ ልጃቸውን ከትምህርት ቤት የሚያመላልሱት ወላጅ እናቷ የነበሩ ቢሆንም ሌላ ስራ ስላጋጠማቸው ነበር አባት ወደ ትምህርት ቤቱ የሔዱት።

ልጃቸውን ይዘው ወደ ቤታቸው ሲያመሩ በአካባቢው ሰዎች ልጅ ሰርቆ እየሔደ ነው በሚል ምክንያት ከባድ ድብደባ እንደተፈፀመባቸውና ለከፋ ጉዳት እንደተጋለጡ ተናግረዋል።

”ልጄ ናት ብዬ መታወቂያ ባሳይም ፣ ህፃኗ ደግሞ  አባቴን አትንኩት ብላ ብትጮህም ያለምህረት ደብድበውኛል ” ሲሉ በምሬት ገልፀዋል።

“ባለቤቴ መጥታ የልጄን አባት ለምን ትድበድቡታላችሁ እያለች ብትማፀንም የታክሲ ሾፌሮችና ፖሊሶች ሳይቀሩ የድብደባው ተሳታፊ መሆናቸው ከልብ አዝኛለሁ” ብለዋል።

የተጎጂው ባለቤት ወይዘሮ ባዩሽ ጥበቡ በበኩላቸው በከተማዋ እየተናፈሰ ያለው አሉባልታ ሰላማዊ ዜጎቸን ለጉዳት እየዳረገ በመሆኑ ህዝቡን አለአግባብ የሚያሸብሩ ወሬኞች እየታደኑ በህግ ሊጠየቁ ይገባል የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።

የአዳማ ከተማ ፖሊሲ አዛዥ ኮማንደር #ደረጀ_ሙለታ ለኢዜአ እንደገለፁት ህፃናት እየተሰረቁ ኩላሊታቸው እየተሸጠ ነው የሚል አሉባልታ በመዛመቱ የገዛ ልጃቸውን ይዘው ሲሄዱ በነበሩ ወላጅ አባት ላይ ከባድ ድብደባ ተፈጽሟል።

በትምህርት ቤትና በእምነት ተቋማት ሳይቀር ህፃናት ልጆች እየተሰረቁ አደጋም እየደረሰባቸው ነው በሚል የሚናፈሰውን ወሬ ሃሰተኛነት ፖሊስ በማረጋገጡ ህብረተሰቡ እንዲረጋጋ ጥሪያቸውን አስተላዋል።

ይሔን ተከትሎ በርካታ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ለትምህርትና ለጨዋታ ከቤት ወጥተው ትንሽ ከዘገዩ ጭምር በድንጋጤ ለፖሊስ የሚቀርቡ ጥቆማዎች ቁጥር በመጨመሩ በስራ ላይ ጫና እየፈጠሩ መምጣታቸውን ኮማንደር ደረጀ ይገልፃሉ።

#አሉባልታው በከፋ መልኩ በደምበላ ክፍለ ከተማ ኢሬቻ ቀበሌ በሚገኘው ጫካና በሌሎች አካባቢዎች የህፃናት አስከሬን ተገኝቷል የሚል በመሆኑ ፖሊስ ለማጣራት በቦታው ድረስ ዘልቆ በመግባት አሰሳ ቢያካሔድም ምንም የተገኘ ነገር የለም ብለዋል።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል #ብርሃኑ_ጁላ

‹‹በውትድርና ዘመኔ በራስ ሕዝብ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ዘግናኝ #ጥቃት ተፈጽሞ #ያየሁት በምዕራብ ወለጋ ነው››

‹‹ለረጅም ዓመታት በውትድርና አገልግያለሁ፣ እንዲህ ዓይነት #ጭካኔ በወለጋ ከተፈጸመው በስተቀር አይቼ #አላውቅም፤››

‹‹በምዕራብ ወለጋ የተፈጸመውን ጭካኔ በቅርቡ #በቪዲዮ ምሥል ጭምር #ታዩታላችሁ፤››

‹‹የመከላከያ ሠራዊቱ ወደ #ወለጋ ሲገባ ያገኘነው #ጉድ ዘግናኝ ነው፤››

https://telegra.ph/በውትድርና-ዘመኔ-በራስ-ሕዝብ-ላይ-ጭካኔ-የተሞላበት-ዘግናኝ-ጥቃት-ተፈጽሞ-ያየሁት-በምዕራብ-ወለጋ-ነው-01-09-2
የአገር መከላከያ ሚኒስቴር‼️

በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተግባር ላይ የነበሩ ወታደሮች ኮንቮይ ላይ #የአልሸባብ ታጣቂዎች #ጥቃት_መፈጸማቸውን የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

#የአገር_መከላከያ_ሚኒስቴር ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ‹‹በሠራዊቱ ላይ ጥቃት የደረሰው ኮንቮዩ ከቡራሃካባ ወደ ባይዶአ በመጓዝ ላይ እያለ ሲሆን፣ ሠራዊታችን ጥቃቱን በጽናት በመመከት ኮንቮዩን ባይዶአ ይዞ ገብቷል፤›› ብሏል፡፡

ሠራዊቱ ካሁን ቀደም በርካታ የአልሸባብ ጥቃቶችን #በመመከት አልሸባብን ያዳከመው መሆኑን ያስታወሰው መግለጫው፣ በአሁኑ ጥቃትም አልሸባብ በቀቢፀ ተስፋ የሠራዊቱን ንቅናቄ ለመግታት ሙከራ እንዳደረገ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ሠራዊቱ የአልሸባብን ጥቃት ተከትሎ ጠንካራ የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ በስምሪት ላይ እንደሚገኝም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ዓርብ ጥር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. የአገር መከላከያ ሠራዊት አራት መኪኖች ላይ ጥቃት ተፈጽሞ በርካታ የሠራዊቱ አባላት ተገድለዋል የሚል ዘገባ የወጣ ቢሆንም፣ የመከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ ጥቃቱ ምን ያክል ጥፋት እንዳደረሰ አልገለጸም፡፡ ሆኖም የመከላከያ ሠራዊት በአሚሶም ተልዕኮ በሶማሊያ ሰላም በማስፈን ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስታውሷል፡፡

ምንጭ:- ሪፓርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ

ዛሬ በሀዋሳ በመንግስት ሀላፊዎች ላይ የተፈፀመው #ድብደባ!

ከደቂቃዎች በፊት አለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከደቡብ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ከሆኑት ከዶ/ር #ጌታሁን_ጋረደው ጋር በስልክ ቆይታ አድርጎ ነበር ስለጉዳዩ ይህ ብለዋል፦

"በመጀመርያ በሶሻል ሚድያ እኔ በወጣቶች #እንደታገትኩ የተገለፀው #ሀሰት ነው። ጠዋት እኔ ስመራው የነበረው ስብሰባ ሌላ አዳራሽ ውስጥ ነበር። ወጣቶች መጥተው ስብሰባው ይቁም ሲሉ confront ሳናረጋቸው አመራሮችን ወዲያው #በትነናል። የወላይታ ዞን ቱሪዝም እና ባህል ቢሮ ሀላፊ አቶ ፀጋ ስምዖን ላይ ግን #ጥቃት ተፈፅሟል። ይህ ስብሰባ ይካሄድበት የነበረው አዳራሽ ውስጥ ከመጡት ወጣቶች ጋር #ግጭት ነበር። ዝርዝሩን አላውቅም። አሁን ሰላም ነው። አቶ ፀጋ ለህክምና ሶዶ ደርሷል። ከትንሽ ደቂቃ በፊትም አናግሬዋለሁ።"

ማነው ድብደባውን የፈፀመው ተብለው በጋዜጠኛው ለቀረበላቸው ጥያቄ፦

"እከሌ ኤጄቶ ነው እከሌ አይደለም ለማለት አልችልም። ግን ሶሻል ሚድያ ላይ ኤጄቶ ስብሰባው እንዲበተን ይፈልጋል የሚል መልእክት ጠዋት ስብሰባ ከመግባቴ በፊት አንብቤ ነበር።"

የሶሻል ሚድያ ምስል: አቶ ፀጋ ስምኦን

Via Elias Mesret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጋምቤላ #የሙርሌ_ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት #ጥቃት አደረሱ‼️
.
.
በጋምቤላ ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት ጥቃት ማድረሳቸውን የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኡቶዉ ኡኮት ገለፁ።

ኃላፊው አክለውም ለኢፌድሪ መከላከያም ድንበር አቋርጦ የገባ የታጠቀ ኃይል እንዳለ በማሳወቅ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው መጠየቃቸውን ይናገራሉ።

አቶ ኡቶዉ እንደሚሉት በጋምቤላ በዚህ ሰዓት በጋ ስለሆነ እና ክልሉን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያጋራው ድንበር ሰፊና ክፍት ስለሆነ የታጣቂዎች የመግባትና የመውጣት አዝማሚያ አለ።

የሙርሌ ታጣቂዎች ባለፈው ወር ድንበር አቋርጠው በመግባት ከኑዌር ዞን ጂካ ወረዳ አንድ ሕፃን መውሰዳቸውን ያስታውሳሉ።

እንዲሁም ከዚሁ ወረዳ 150 ከብት እና 234 ፍየሎችንም ዘርፈዋል ያሉት ኃላፊው ከሳምንት በፊት ጆር በሚባል አካባቢ ከአካባቢው ሚሊሻ ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገው ከእነርሱ ወገን ሰው መጎዳቱን ይናገራሉ።

አቶ ኡቶዉ ክልሉ በአሁኑ ሰዓት ልዩ ኃይሉንና ሚሊሻ በመጠቀም ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ስራውን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በቅርብ የሙርሊ ጎሳ ታጣቂዎች ጥቃት ባደረሱባቸው አካባቢዎች መሄዳቸውን የሚናገሩት ኃላፊው የአካባቢው ነዋሪ ስጋት እንዳለበት መታዘባቸውን ገልፀዋል። ክልሉ የነዋሪውን ስጋት ለማስወገድ እና ቀዬውን ለቅቆ እንዳይሄድ የተለያዩ የማረጋጋት ስራዎችን መስራታቸውንም ተናግረዋል።

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከሁለት ዓመት በፊት፤ በኑዌር ዞን እና አኙዋ ዞኖች ገብተው 234 ሕፃናት አፍነው ሲወስዱ፣ ከአንድ መቶ ሰባ በላይ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል። በወቅቱ ከ2ሺህ በላይ ከብቶች መውሰዳቸውንም ኃላፊው ጨምረው ያስታውሳሉ።

በወቅቱ የኢፌድሪ መከላከያ ኃይል ወደ ደቡብ ሱዳን በመግባትና ታጣቂዎቹ የሚኖሩበት አካባቢ ላይ ጥቃት በመፈፀም ታፍነው ከተወሰዱት ሕፃናት መካከል ከ100 ሕፃናት በላይ ወደ ቤተሰቦቻቸው መልሷል። ቀሪዎቹ ግን የደረሱበት አልታወቀም።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በቢሯቸው በተፈጸመ #ጥቃት ቆስለው በወታደራዊ አውሮፕላን ለሕክምና ወደ ኳታር የተወሰዱት የሞቃዲሾ ከንቲባ አብዲራሕማን ኦማር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
.
.
የሞቃዲሾ ከንቲባ አብዲራሕማን ኦማር በቢሯቸው በተፈጸመ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት መቁሰላቸው ይታወሴ። በወቅቱ ጥቃቱ ሲፈጸም በከንቲባው ቢሮ በጸጥታ ጉዳይ ላይ ውይይት እየተደረገ አይዘነጋም።

Via #Eshete_Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀገር መከላከያ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ 42 ታጣቂዎች ተደመሰሱ !

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት በንጹኃን ዜጎች ላይ #ጥቃት ያደረሱ የታጠቁ ኃይሎች ላይ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ተከታትሎ በወሰደው እርምጃ 42ቱ መደምሰሳቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ከደቂቃዎች በፊት አሰውቋል።

የመከላከያ ሠራዊት በወሰደው እርምጃ ታጣቂዎቹ ለጥፋት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን እና ቀስቶችን በቁጥጥር ስር አዉሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የወረዳ አመራሩ ተገደሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለባቸው አሞኜ በዛሬው ዕለት በቢሮአቸው ውስጥ ተገደሉ።

የክፍለ ከተማው ኮሚኒኬሽን ባሰራጨው መረጃ ፤ " አቶ አለባቸው አሞኜ ቢሯቸው ውስጥ ቁጭ ብለው የህዝብ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ከአንድ #ተገልጋይ በደረሰባቸው #ጥቃት ህይወታቸው አልፏል " ብሏል።

ክ/ከተማው ምንም እንኳን ግድያውን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ ባያደርግም ጥቃት ያደረሰው ተጠርጣሪ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን አመልክቷል።

ተገቢው የምርመራ ሂደት ተከትሎ ተጠያቂነት የማስፈን ስራ ይሰራልም ብላል።

" አቶ አለባቸው በስራ ቁርጠኝነት የሚታወቁ " ናቸው ያለው የቂርቆስ ክ/ከተማ " በበርካታ መንግስታዊና ህዝባዊ ተግባራት አርዓያነት ያለው ስራ የሰሩና ያስተባበሩ አመራራችን ነበሩ " ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኤምባሲ በከባድ መሳሪያ ተመታ።

ሱዳን ካርቱም ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ በተፈጸመ የከባድ መሣሪያ ጥቃት የንብረት ጉዳት መድረሱን ቢቢሲ ዲፕሎማቲክ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ የከባድ መሣሪያ ጥቃቱ የደረሰው ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 22/2016 ዓ.ም. ጠዋት ላይ ነው።

የከባድ መሣሪያ ጥቃቱ በኤምባሲው ሕንጻ እና ንብረት ላይ ውድመት ያደረሰ ሲሆን፣ በሰው ላይ ግን ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱ ተገልጿል።

በካርቱም አል-አማራት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ባለፉት ወራት በተለያዩ ኃይሎች ተደጋጋሚ #ጥቃት እና #ዘረፋ እንዳጋጠመው ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ ዲፕሎማት ተናግረዋል።

በአገሪቱ እየተካሄደ ባለው ጦርነት አንደኛው ተፋላሚ ወገን የሆነው በጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤክስ (ትዊተር) ገጹ ላይ ዛሬ ጠዋት በኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት መድረሱን ገልጿል።

ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ለጥቃቱ ተቀናቃኙን በጄኔራል አብደል ፋታህ አልቡርሐን የሚመራውን የሱዳን ጦር ሠራዊትን ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን፣ በኤምባሲው ላይ በተፈጸመው ጥቃት " በሕንጻው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል " ብሏል።

በኤምባሲው ላይ ጥቃቱ ለምን እንደተፈጸመ እስካሁን የታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን ስለክስተቱ በኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ በጄኔራል አልቡርሐን ኃይሎች በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

በዛሬው ዕለት ጠዋት ላይ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ በተጨማሪ በዩናይትድ አረብ ኤምሬት፣ በሩሲያ እና በደቡብ አፍሪካ ኤምባሲዎችም ላይ ጥቃት መፈጸሙን ቢቢሲ ዲፕሎማቱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia