TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

አቶ ጌታቸው ረዳ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ ሪፈረንደም አይታሰብም አሉ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፦

- የትግራይ ግዛቶችን በወረራ የያዙ ኃይሎች ሳይወጡ፤

- ተፈናቃዮች ወደ ቀደመው ቄያቸው ሳይመለሱ ሪፈረንደም የሚባል ነገር #አይታሰብም ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው ይህንን ያሉት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሚስተር ኤርቪን ጆዜ ማሲንጋ ከተመራ የልኡክ ቡድን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ላይ የአሜሪካ መንግስትና ህዝብ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲፈረም ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ ከልኡካን ቡድኑ ጋር አህጉርና ዓለም አቀፍ እንዲሁም አከባቢያዊ የፀጥታ ጉዳዮችና በክልሉ ስላጋጠመው ድርቅ አንስተው መወያየታቸው ታውቋል።

የትግራይ ግዛታዊ አንድነት በህገ መንግስቱ መሰረተ ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት መመለስ አለበትም ብለዋል። 

" የኤርትራ እና የአማራ ሃይሎች በወረራ ከያዙት የትግራይ ግዛት ሳይወጡ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ ለሌላ ስቃይ መዳረግ ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " የሪፈረንደም ጉዳይ መነሳት ካለበት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት በሃይል የተያዘው መሬት ተለቆ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ተመልሰው በምርጫ ህጋዊ መንግስት ከተቋቋመ በኃላ ነው " ብለዋል።   

ከቄየው የተፈናቀለው ህዝብ በቂ የእርዳታ አቅርቦት የማያገኝ በተለይ በአሁኑ ሰዓት በክልሉ የተከሰተው ድርቅ ተጨምሮበት ኑሮው እጅግ አስከፊና ውስብስብ አድርጎታል በማለት የገለፁት አቶ ጌታቸው የአሜሪካ ህዝብና መንግስት የጉዳዩ አሳሳቢነት በመገንዘብ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል። 

አምባሳደር ኤርቪን ጆዜ ማሲንጋ ምን አሉ ?

- የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በጥብቅ እንደሚከታተሉት ገልጸዋል።
- መንግስታቸው ለስምምነቱ ተግባራዊነትና የትግራይ መልሶ ማልማትን እንደሚደግፍና እንደሚሰራ ቃል ገብተዋል።

መረጃውን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት ፅህፈት ቤት መግለጫን ዋቢ በማድረግ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia